👉🏽👉🏽👉🏽 የ #ገና #ጾም (የ #ነቢያት ጾም) #ወቅት በ #ቤተክርስቲያን እንዴት ይገለጻል?
(ክፍል 1)
✍በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዘመን አከፋፈል መሠረት
👉ከኅዳር 6 ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ 7 ወይም 13 ቀን ድረስ ያለው ወቅት ዘመነ አስተምሕሮ (አስተምህሮ) ይባላል፡፡
👉ከኅዳር 13 እስከ ኅዳር 19 ቅድስት ይባላል
👉ከኅዳር 20 እስከ ኅዳር 26 ምኩራብ ይባላል
👉ከኅዳር 27 እስከ ታኅሣሥ 3 መፃጉዕ ይባላል
👉ከታኅሣሥ 4 እስከ ታኅሣሥ 6 ደብረ ዘይት ይባላል (ለሦስት ቀናት ብቻ ነው)።
👉ከታኅሣሥ 7 እስከ ታኅሣሥ 13 ዘመነ ስብከት ይባላል
👉ከታኅሣሥ 14 እስከ ታኅሣሥ 20 ዘመነ ብርሃን ይባላል
👉ከታኅሣሥ 21 እስከ ታኅሣሥ 27 ዘመነ ኖላዊ ይባላል
👉ታኅሣሥ 28 እና ታኅሣሥ 29ልደት ተብለው ይጠራሉ።
✍ዘመነ አስተምህ(ሕ)ሮ፦ ስለ እግዚአብሔር ቸርነትና ርኅራኄ እርሱ በደላችንን ሁሉ ይቅር እንደሚለን እኛ ምእመናንም እርስ በእርስ ይቅር መባባል እንደሚገባን ትምህርት የሚሰጥበት ጊዜ ነው፡፡
✍ዘመነ አስተምሕሮ፦
👉ቤተ ክርስቲያን ስለ ልጆቿ ይቅርታ የምትጠይቅበት፣
👉ምእመናንንም ስለ በደላቸው ይቅርታ የሚጠይቁበት፣ስለዚህም በስፋት ትምህርት የሚሰጥበት ዘመን ነው፡፡
✍በዘመነ አስተምሕሮ የሚገኙ ሰንበታት፦ በቅዱስ ያሬድ የዜማ መጻሕፍት እንደተቀመጠው በዘመነ አስተምሕሮ ውስጥ የሚገኙ ሰንበታት (እሑዶች)፦
👉 አስተምሕሮ (ኢተዘኪሮ)፣
👉አስተምሕሮት (ሎቱ ስብሐት)፣
👉ምኵራብ (አምላክ ፍጹም በሕላዌሁ)፣
👉መጻጉዕ (ይቤሉ እስራኤል) እና
👉ደብረ ዘይት (ሠርዐ ሰንበተ ለሰብእ እረፍተ) ተብለው ይጠራሉ፡፡
✍ስለ አስተምሕሮ (አስተምህሮ) ትርጉም የተሰጠ ትምህርት በዚህ ሊንክ ይገኛል👇
✍https://t.me/yeyohannesneseha/160136
✍ሳምንታቱን በዚህ መልክ የከፋፈለውም ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ነው (ድጓ ዘአስተምህሮ)፡፡ ከመጀመሪያው ሳምንት (ከአስተምሕሮ) በቀር የአራቱ እሑዶቹ ስያሜ ከዐቢይ ጾም ሰንበታት ጋር አንድ ዓይነት ነው፡፡
👉የሰንበታቱ ስያሜ ከዐቢይ ጾም ጋር ተመሳሳይ ነውን?
✍የዘመነ አስተምህሮ ሰንበታት (እሑዶች) ስያሜ ከዐቢይ ጾም ሰንበታት ስያሜ ጋር ተመሳሳይ ይሁን እንጂ በእነዚህ ሳምንታት ሌሊት፦
👉 የሚዘመሩ መዝሙራት፣
👉በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ምንባባትና
👉የሚቀርቡ ትምህርቶች ግን በይዘትና በምሥጢር ይለያያሉ፡፡
✍ትምህርቶቹ በምስጢር ይለያያሉ ስንልም በዚህ ወቅት የሚነገረው ምሥጢርና ይዘት በወቅቱ ላይ የሚያተኩር መሆኑን ለመግለጽ ነው እንጂ በየትኛውም ጊዜ በቤተክርስቲያናችን የሚቀርበው ትምህርት አንዱ የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው።
ይቀጥላል (ክፍል 2)
👇
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወለዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር!!!
@Sewsinor