#አማራ
መከላከያ ሰራዊት በአማራ ክልል ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ ኦፕሬሽን መጀመሩን
የመከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ኮለኔል ጌትነት አዳነ ተናግረዋል።
ሰሞኑን በርካታ የመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች ወደ አማራ ክልል ገብተዋል።
የክልሉ ሰላም ሙሉ ለሙሉ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እስኪመለስ ድረስ መከላከያ ሰራዊት ከክልሉ እንደማይወጣ ገልፀዋል።
በአማራ ክልል በፋኖ ሀይሎች እና በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች መካከል ከአንድ አመት በላይ ውጊያ ውስጥ እንዳሉ ይታወቃል።
በዚህም ጉዳዩ እስካሁን በድርድር ይፈታል በሚል ብዙ ጥረት እንደተደረገ ገልፀው መከላከያ ሰራዊት ከዚህ በኋላ አይታገስም፣እርምጃ ወደ መውሰድ ገብቷል ብለዋል።
በዚህም ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ ከፋኖ ሀይሎች ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ በርካታ ሰዎች እና አመራሮች መታሰራቸውን ገልፀዋል። ኦፕሬሽኑ ይቀጥላል ብለዋል።
በተመረጡ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ከትናንት በስተያ ጀምሮ የስልክ አገልግሎት እንዲቋረጥ ተደርጓል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የፋኖ ሀይሎች ከነገ ጀምሮ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዲቆም ትዕዛዝ እያስተላለፉ ይገኛሉ።