38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ መካሄድ ጀመረ።
38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በአህጉሪቱ መዲና በሆነችሁ በአዲስ አበባ ዛሬ በይፍ መካሄድ ጀምሯል።
ጉባኤው ከ35 በላይ የሀገር መሪዎች፣ አንድ ንጉስ፣ 19 ቀዳማዊት እመቤቶች፣ ሁለት ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ሁለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በአዲስ አበባ በአፍሪካ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት በጀመረው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ተገኝተዋል።
የአፍሪካ ህብረት አባልነታቸው የታገደባቸው 6 ሀገራት ሱዳን፣ኒጀር፣ጋቦን፣ጊኒ፣ቡርኪናፋሶና ማሊ በጉባኤው ያለተሳተፍ ሀገራት ናቸው።
የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት '' ተለዋዋጭ ከሆነው የዓለም ፖለቲካና ኢኮኖሚ ጋር በፍጥነት ለመራመድ አፍሪካዊያን በጋራ መቆም እንደሚገባቸው '' ገልፀው ገባኤውን የመክፈቻ ንግግር በማረግ አስጀምረውታል።
በዛሬ ውሎውም የአንጎላ ፕሬዝዳንት ዧው ማኑኤል ጎሳዌስ ሎሬንሶ የሞሪታንያ መሀመድ ኦልድ ጋዙዋንን በመተካት የአፍሪካ ህብረት አዲሱ ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል።
አፍሪካ ''በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ተገቢ ቦታ እንድታገኝ በተለይ በተመድ በቂ ውክልና እንድታገኝ በትብብር እንደሚሠሩም '' አዲሱ ሊቀመንበር ቃል ገብተዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ እንደተናገሩት"አፍሪካ በፀጥታ ምክር ቤት ሁለት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት ተመድ ግፊት ማድረጉን ይቀጥላል'' ሲሉ ተናግረዋል።
የአፍሪካ ህብረት እ.ኤ.አ. በ2030 አህጉሪቱ ላይ የትጥቅ ግጭቶችን ለማስቆም ያለመውን "ጠመንጃዎችን ዝም የማሰኘት" እቅድ የሁለት ዓመት ሪፖርት ላይ ይመለከታል ተብሎ ይጠበቃል።
ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚመክረው ጉባዔው መሪዎች ለባርነት እና ለቅኝ ግዛት ካሳ አዲስ ግፊት በመጀመር ከገንዘብ ካሳ፣ ያለፉትን ስህተቶች መደበኛ እውቅና መስጠት እስከ ፖሊሲ ማሻሻያዎች ድረስ የባርነት ካሳው ጉዳይ ምን ሊመስል እንደሚችል "የተዋሃደ ራዕይ" ለመቅረጽ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።
ሌላው ቁልፍ አጀንዳ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምርጫ ሲሆን እጩዎች ለሊቀመንበር እና ለምክትል ሊቀመንበርነት ይወዳደራሉ።
የኬንያውን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋን፣ የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍን እና የማዳጋስካርውን ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶ የወቁቱን የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ መሐመት ለመተካት ይወዳደራሉ።