ሙሉ ስሙ ጀምስ ስቲቭ ዶናልድሰን ይባላል። የተወለደው ግንቦት 7/1998 ዩናይትድ ስቴትስ ካንሳስ ውስጥ ነው። በዋናነት ዩቲዩበር ሲሆን ሦስት ዩቱዩብ ቻናሎች ቲክ ቶክን ጨምሮ ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያዎችን ያስተዳድራል።
በተለየ ሁኔታ ሚስተር ቢስት የሚለው ዋናው የዩቲዩብ ቻናሉ 330 ሚሊዮን ተከታይ እና 64.3 ቢሊየን እይታ ያለው ሆኖ ሚስተር ቢስት2 የተሰኘው የዩቲዩብ ቻናሉ 46.5 ሚሊዮን ተከታይ እና 7.07 ቢሊየን እይታ ያለው እና በዓለም ዙሪያ እውቅናን ያገኘባቸው ናቸው።
በሌላ አጠራር ጂሚ ዶናልድሰን በሚል የሚታወቀው ሚስተር ቢስት ጎበዝ የንግድ ሰው ሲሆን ሚስተር ቢስት በርገር የተሰኘው ብራንዱ ተወዳጅ እና ታዋቂ ሆኖለታል፤ በርካታ ሽልማቶችን ያሸነፈ ሲሆን ዩቲዩብ ብቻ አምስት ጊዜ የዩቲዩብ ክሬተር አዋርድን ሸልሞታል።
ከአንድ መቶ የዓለማችን ተፅዕኖ ፈጣሪ ስዎች መካከል አንዱ መሆን የቻለ ሲሆን ፎርቢስ መፅሄትም ከሃብታም ግለሰቦች ዝርዝር ውስጥ አካቶታል።
የመጋፈጥ ቪዲዮዎች (challenge videos) በማዘጋጀት እና በበርካታ የበጎ አድራጎት ድርጅቶቹ እና እገዛው በዓለም ዙሪያ ሁሉ በሰፊው ሊታወቅ የቻለ ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣት ነው።
የዛሬው ስካይ ልዩ ፕሮግራም ይሄን ይመስል ነበር ሰናይ ምሽት!
@Skysport_Ethiopia@Skysport_Ethiopia