የቀድሞ የዋልያዎቹ አሰልጣኞች ሳይጨባበጡ ወጡ !
የኢትዮጵያ ዋንጫ ተጠባቂ ጨዋታዎች ዛሬ መደረጋቸውን ሲቀጥሉ አፄዎቹ በኢትዮጵያ መድን ሁለት ለዜሮ ተሸንፈዋል።
ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ ውበቱ አባተና የኢትዮጵያ መድን አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ ሰላም ሳይባባሉ ወደ መልበሻ ክፍል ገብተዋል ።
ሁለቱ በአርያነት የሚጠቀሱት የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞች ከፉክክሩ በኋላ የስፖርታዊ ጨዋነት ሰላምታ አለመለዋወጣቸው በስታዲየሙ ያሉትን ተመልካቾች አነጋግሯል።
የዚህ ዜና ዘጋቢ አሰልጣኝ ውበቱ ለሰላምታ ፊታቸውን አዙረው ሲጠባበቁ ቢታዘብም አሰልጣኝ ገብረመድን ረጅም ሰአት ጨዋታው አልቆ ፊታቸውን አዙረው ተጨዋቾችን ሲያበረታቱ ታዝቧል።
ተስፋ የቆረጡ የሚመስሉት አሰልጣኝ ውበቱ ወደ መልበሻ ክፍል ገብተዋል።
ኢትዮጵያ መድን በዳዊት ተፈራና መሀመድ አበራ የመጀመሪያ አጋማሽ ጎል ነው ፋሲል ከነማን አሸንፎ ወደ ተከታዮች ዙር ያለፈው።
[ባላገሩ ስፖርት]
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et