ከረመዷን ቀዷእ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች
---------------
1. የረመዷንን ቀዷእ ወዲያው ማውጣት ግዴታ ነው ወይስ ቀስ ብሎ ማውጣት ይቻላል?
2. የቀዷእ ፆምን ለያይቶ መፆም ይቻላል ወይስ አከታትሎ መፆም ግዴታ ነው?
3. በአሳማኝ ምክንያት ቀዷኡን ሳያጠናቅቅ ቀጣዩ ረመዷን የደረሰበት ሰው ምን ማድረግ ይጠበቅበታል?
4. ያለ ተጨባጭ ምክንያት ቀዷኡን ሳያጠናቅቅ ቀጣዩ ረመዷን የደረሰበትስ ሰው ምን አለበት?
አራቱንም ነጥቦች በቅደም-ተከተል እንመልከት።
ጥያቄ አንድ፡-
የረመዷንን ቀዷእ ረመዷን እንዳለቀ ወይም ያቆምንበት ዑዝር እንደተነሳ ወዲያው ማውጣት ግዴታ እንደሆነ የሚያመላክት ቀጥተኛና ግልፅ (ሶሪሕ) ማስረጃ የለም። ስለሆነም ቀጣዩ ረመዷን እስካልገባ ድረስ እስከ ሸዕባን ድረስ ባለው ረጅም ጊዜ ቀዷእ ማውጣት ይቻላል። ይህ አቋም እንደ ኢብኑ ዐብዲል በር እና መጅድ ኢብኑ ተይሚያ ያሉ ዑለማዎች ኢጅማዕ ያለበት ነው ይላሉ። በርግጥ ኢጅማዑ አጠያያቂ ነው። ምክንያቱም የዟሂሪያው መዝሃብ ኢማም ዳውድ ረመዷን እንደተጠናቀቀ፣ ከዒድ በኋላ ከሸዋል ሁለት ቀጥሎ ቀዷእ ማውጣት ግዴታ ነው። ሳይፆመው ከሞተ ግን ወንጀለኛ ነው ብለዋልና። ሌሎችም ተመሳሳይ አቋም ያንፀባረቁ ዑለማዎች አሉ።
የብዙሃኑ የኢስላም ምሁራን ዐቋም ግን ቀጣዩ ረመዷን እስካልገባ ድረስ ቀዷእ ቢዘገይም ችግር የለውም የሚል ነው። ለዚህ ደጋፊ አድርገው ከሚጠቅሷቸው ማስረጃዎች ውስጥ አንድ ሁለቱን ልጥቀስ፡-
1. አላህ እንዲህ ብሏል፡-
فَمن كَانَ مِنْكُم مَرِيضا أَو على سفر فَعدَّة من أَيَّام أخر
“ከናንተ ውስጥ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የሆነ ሰው ከሌሎች ቀኖች (ተመሳሳይ) ቁጥሮችን መፆም አለበት።” [አልበቀራህ፡ 184]
በአንቀጿ ውስጥ የቀዷእ ጉዳይ ያለምንም የጊዜ ገደብ ልቅ ሆኖ ነው የተቀመጠው። ስለሆነም ቀጣዩ ረመዷን እንዳይደርስ እንጂ በየትኛውም ጊዜ መፈፀም ይቻላል ማለት ነው።
2. እናታችን ዓኢሻም ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ብላለች፡-
كَانَ يَكُونُ عَلَيَّ الصَّوْمُ مِنْ رَمَضَانَ، فَمَا أَسْتَطِيعُ أَنْ أَقْضِيَ إِلَّا فِي شَعْبَانَ
“ከረመዷን ፆም (ያለፈኝ) ይኖርብኝ ነበር። ታዲያ በሸዕባን እንጂ ቀዷ ማውጣት አልችልም ነበር።” [ቡኻሪ፡ 1950] [ሙስሊም፡ 1146]
ይህን ያክል የምታዘገየው በነብዩ ﷺ ሰበብ ነው። ሸዕባን ቀዷ ለሚያወጣ ሰው የመጨረሻው ወር ነው። ምክንያቱም ከሸዕባን ቀጥሎ ያለው ረመዷን ነውና።
ጥያቄ ሁለት፡- የቀዷእ ፆምን ለያይቶ መፆም ይቻላል ወይስ አከታትሎ መፆም ግዴታ ነው?
ከሶሐቦች ውስጥ ከኢብኑ ዑመርና ከዓኢሻ፤ ከነሱ በኋላ ደግሞ ከከፊል ዑለማዎች ማከታተል ግዴታ እንደሆነ ተዘግቧል። መነሻቸው የረመዷንን ወር ንፅፅር በመውሰድ ነው። ልክ ረመዷን ተከታትሎ እንደሚፆመው የረመዷን ቀዷእም እንዲሁ መከታተል አለበት የሚል ነው።
ነገር ግን ሌሎች በርካታ ዑለማዎች ሳያከታትሉ አለያይቶ መፆም ይቻላል ይላሉ። ከሚያጣቅሷቸው ማስረጃዎች አንዱ ከላይ የጠቀስኳት አንቀፅ ነች። አንቀጿ ውስጥ ምንም አይነት የማከታተል ገደብ አለመጠቀሱ የቀዷእ አፈፃፀሙ ክፍት እንደሆነ አመላካች ነው። ስለዚህ ቢፈልግ አከታትሎ ቢፈልግ ለያይቶ ባሰኘው መልኩ መፈፀም ይችላል ማለት ነው።
ይህኛው አቋም ከሶሐቦች የአነስ፣ የሙዓዝ፣ የኢብኑ ዐባስ፣ የአቡ ሁረይራህ፣ የራፊዕ ኢብኑ ኸዲጅ አቋም ሲሆን ከነሱ በኋላ ደግሞ ታቢዒዮችን ጨምሮ የብዙ ዑለማዎች አቋም ነው። እንዲሁም የአራቱ የፊቅህ መዝሀብ አኢማዎች አቋምም ነው።
ማሳሰቢያ፡- ለያይቶ መፆም የሚቻል ቢሆንም ማከታተሉ ግን በላጭ ነው። ኢብኑ ሐጀር ረሒመሁላህ “ለያይቶ ቀዷእ መውጣትን የሚፈቅዱት፥ ማከታተሉ በላጭ በመሆኑ ላይ የተለየ አቋም የላቸውም” ይላሉ።” [ፈትሑል ባሪ፡ 4/189]
ጥያቄ ሶስት፡- በአሳማኝ ምክንያት ቀዷኡን ሳያጠናቅቅ ቀጣዩ ረመዷን የደረሰበት ሰው ምን ማድረግ አለበት?
ለምሳሌ፡-
- ለረጅም ጊዜ ጉዞ ላይ በመሆን የተነሳ ወይም ህመም ላይ በመሰንበት የተነሳ ቀዷእ ሳያጠናቀቅ ቀጣይ ረመዷን የደረሰበት ሰው፤
- በእርግዝናና በማጥባት ተደራራቢነት የተነሳ፣ ወይም በመርሳት የተነሳ ቀዷእ ሳታወጣ ቀጣዩ ረመዷን የደረሰባት ሴት፣…
እነዚህን በተመለከተ በጉዳዩ ላይ ያለውን ሃሳብ ጨመቅ አድርጌ ሳቀርበው የሚጠበቅባቸው የደረሱበትን ረመዷን ከፆሙ በኋላ ቀዷእ ማውጣት ብቻ ነው። ከዚህ ባለፈ ላለፈው ረመዷን ምስኪን ማብላት አይጠበቅባቸውም። ይሄ የአራቱም አኢማዎች ምርጫ ነው። ይሄው በቂ እንደሆነ ስላመንኩ ኺላፉን ወደጎን ትቼዋለሁ።
ጥያቄ አራት፡- ያለ ተጨባጭ ምክንያት ቀዷኡን ሳያጠናቅቅ ቀጣዩ ረመዷን የደረሰበት ሰውስ ምን አለበት?
እዚህም ላይ ከዑለማዎች ሶስት የተለያዩ ሃሳቦች ተንፀባርቀዋል። እነሱም፡-
1ኛ፡- ቀዷእና ፊድያ አለበት፡-
ማለትም የደረሰውን ረመዷን ፆም ከፆመ በኋላ ያለፈውን ቀዷእ ማውጣት ያለበት ሲሆን በተጨማሪም ለእያንዳንዱ ላለፈው ቀን ምስኪን የማብላት ግዴታ አለበት የሚል ነው። ይሄ ከሌሎች ዑለማዎችም ባሻገር የማሊክ፣ የሻፊዒይና የአሕመድ አቋም ነው።
2ኛ፡- ቀዷእ ብቻ ነው ያለበት፡-
በዚህኛው ሃሳብ መሰረት ደግሞ የሚጠበቅበት የደረሰውን ረመዷን ፆም ከፆመ በኋላ ያለፈውን ቀዷእ ማውጣት ብቻ ነው የሚል ነው። እንጂ ለእያንዳንዱ ቀን ምስኪን ማብላት አይጠበቅበትም።
3ኛ፡- ምስኪን ማብላት ብቻ ነው ያለበት
ይህኛው ሃሳብ ደግሞ የደረሰውን ረመዷን ከመፆም ባሻገር ያለፈውን ረመዷን መፆም አይጠበቅም። ይልቁንም ስለባለፈው ረመዷን ምስኪን ማብላት ብቻ በቂ ነው የሚል ነው።
የትኛው ነው ሚዛን የሚደፋው?
እንደምታዩት ጉዳዩ ውዝግብ አለበት። በውዝግብ ጊዜ ደግሞ የታዘዝነው ወደ ቁርኣንና ወደ ሐዲሥ እንድንመለስ ነው። እንደሚታወቀው በህመም ወይም በጉዞ ምክንያት ፆም ያለበት ሰው በሌላ ጊዜ ቀዷእ እንዲያወጣ በቁርኣን ታዟል። አንቀጿን መግቢያ አካባቢ አሳልፌያለሁ። እዚህም ላይ ቀዷኡን ሳያወጣ በፊት ሌላ ረመዷን ከመድረሱ ውጭ ጉዳዩ ተመሳሳይ ነው። ስለዚህ የሚጠበቅበት ስላለፈው ፆም ቀዷእ ማውጣት ብቻ ሲሆን፤ ቀጣዩ ረመዷን እስከሚደርስ ድረስ ለማዘግየቱ ደግሞ ተውበት ብቻ ነው። እንጂ ፊድያ ማለትም ለእያንዳንዱ ቀን ምስኪን የማብላት ግዴታ አለበት የሚለው ማስረጃ ይፈልጋል። ይህንን የሚያመላክት ግልፅ ማስረጃ ደግሞ የለም። ይሄ ሃሳብ ከላይ ከቀረቡት ውስጥ ሁለተኛው ነጥብ ማለት ነው።
ይሄ ሃሳብ እንደ ሐሰኑል በስሪ፣ አቡ ሐኒፋ፣ አልሙዘኒይ፣ ዳውድ አዝዟሂሪይና ኢብኑ ሐዝም ያሉ ዑለማዎች አቋም ነው። አዋቂው አላህ ነው።
https://t.me/IbnuMunewor