የሞት ፍርድ‼️
የእንጀራ ልጁን ለ10 ዓመታት አስገድዶ ሲደፍር ቆይቶ የገደላት ግለሰብ ሞት ተፈረደበት!!
ሚካኤል ሽመልስ ጌታሁን የተባለ ተከሳሽ የእንጀራ ልጁ ሆነችውን ሟች አዶናዊት ይሄይስ በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ቦታው 15 ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ከ10 ዓመቷ ጀምሮ አስገድዶ ስደፍራት መቆየቱ ተነግሯል።
ተከሳሹ ሟች አዶናዊት ይሄይስን “ከተናገርሽ እናትሽና አባትሽን እገላለሁ” እንዲሁም “የግብረ ስጋ ግኑኝነት ስንፈፅም በሞባይል ቪድዮ ቀርጨዋለሁ፤ በሚድያና በቴሌግራም እለቀዋለሁ” በማለት እያስፈራራ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ህይወትዋ እስካለፈበት ድረስ በተደጋጋሚ አስገድዶ መድፈር እንደፈጸመ ተነግሯል። ሟች አዶናዊት ይሄይስ ከተከሳሽ ሁለት ጊዜ እርገዛ የነበረ ሲሆን፤ መጀመሪያ የነበረው እርግዝና ቤተሰብ እንዳያውቅበት የሟች ስም ኤፍራታ አለማየሁ በሚልና የሟች ዕድሜም 19 ዓመት እንደሆነ በማስመሰል ሐሰተኛ ስምና ዕድሜ በማስመዝገብ ያረገዘችውን ፅንስ እንድታስወርድ ማስገደዱም በክሱ ተመላክቷል።
መስከረም 19 ቀን 2015 ዓ.ም ተከሳሽ በሟች ላይ በፈፀመው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ምክንያት ፖሊሶች ሊያዙት ወደ ቤቱ መምጣታቸውን ሲያይ አምልጦ ከሄደ በኃላ ፖሊሶች መሄዳቸው ሲያረጋግጥ ተመልሶ ወደ ሟች ቤት በመምጣት ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ወላጅ እናትዋ ፊት ህይወትዋ እንዲያልፍ አድርጓል ይላ ክሱ። ሟች ሕይወትዋ ሲያልፍም ለ2ኛ ጊዜ ከተከሳሽ እርጉዝ እንደነበረችም በክሱ ተመላክቷል።
ክሱን የተመለከተው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሰው ግድያና ውንብድና ችሎት በትናንትናው እለት ታህሳስ 25ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ሚካኤል ሽመልስ ጌታሁን በሞት እንዲቀጣ እንደወሰነ ከፍትህ ሚ/ር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል