ስልጣን በይፋ የተረከቡት ትራምፕ "የአሜሪካ ወርቃማ ዘመን አሁን ይጀምራል" ሲሉ ተናገሩ ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው
በዩናይትድ ስቴትስ ካፒቶል ሮቱንዳ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።የአሜሪካ ወርቃማ ዘመን አሁን ይጀምራል በማለት በንግግራቸው ላይ "ሰላም እና አንድነት" በሀገሪቱ "ያብባል እናም አሜሪካ ትከበራለች ሲሉ ትራምፕ ገልፀዋል። ትራምፕ የባይደን አስተዳደርን በተመለከተ የስደተኞችን ቀውስ በመፍጠር በመንግስቷ ላይ “የመታመን” ችግር በህዝበ ዘንድ አስከትሏል ሲሉ ተናግረዋል ።
የቴክኖሎጂ ቢሊየነሮች፣ የካቢኔ ተሿሚዎች እና የቀድሞ ፕሬዚዳንቶችን ጨምረው በዩናይትድ ስቴትስ ካፒቶል በተካሄደው የበዓለ ሲመት ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል። ትራምፕ ቃለ መሃላ ከመፈፀማቸው ጥቂት ደቂቃዎች በፊት ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ተከትሎ ለቤተሰቡ አባላት ይቅርታ ሰጥተዋል። ቤተሰቤ እኔን ለመጉዳት ባለው ፍላጎት ብቻ የማያባራ ጥቃቶች እና ዛቻዎች እንዲሁም ክስ ደርሶባቸዋል ሲሉ ባይደን ተደምጠዋል። ከሁሉ የከፋው የወገንተኝነት ፖለቲካ መሆኑን ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ባይደን በመግለጫቸው ገልፀዋል።
አክለውም እንደ አለመታደል ሆኖ እነዚህ ጥቃቶች ያበቃል ብዬ ለማመን ምንም ምክንያት የለኝም ብለዋል። የባይደን የስልጣን ዘመን የመጨረሻ የይቅርታ እድል ያገኙት የባይደን ሁለት ወንድሞች ጄምስ እና ፍራንሲስ ይገኙበታል። እንዲሁም በዝርዝሩ ውስጥ የባይደን እህት ቫለሪ እና ባለቤቷ ጆን ይገኙበታል።ሳራ የተባለችው የጄምስ ባይደን ሚስት በተመሳሳይ የይቅርታ እድሉ ተጠቃሚ ናቸው።ትራምፕ ስልጣን መረከባቸውን ተከትሎ የአስፈፃሚ ትዕዛዞች አካል በመሆን "ብሄራዊ ድንገተኛ አደጋ" ለማወጅ ተዘጋጅተዋል።
ትራምፕ ዳግም ወደ ስልጣን መመለሳቸውን ተከትሎ ለአሜሪካ ህዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል። አንድ ነገር ማድረግ የማይቻልን ነው ብሎ ማመን እንደሌለባችሁ ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ በፊታችሁ ቆሜያለሁ ሲሉ ተደምጠዋል። በአሜሪካ ውስጥ የማይቻለውን ማድረግ እንደምንችል አሳይተናል ብለዋል ። ከዚህ ቀን ጀምሮ ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ሉዓላዊ እና ነጻ ሀገር ትሆናለች በማለት አክለዋል። "መጪው ጊዜ የእኛ ነው፤ እናም ወርቃማው ጊዜያችን ገና ጀምሯል ብለዋል።ተቃዋሚዎች ባነሮችን እያውለበለቡ እና የመጪውን የትራምፕ አስተዳደር ፖሊሲዎችን በማውገዝ በኋይት ሀውስ ተቃውሞ አሰምተዋል።
https://t.me/Tamrinmedia