በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ተከስቶ የነበረውን የእሳት አደጋ መቆጣጠር ተቻለ
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ቡልቡላ 40/60 እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ወደ ሌላ ቦታ ሳይዛመት መቆጣጠር መቻሉ ተገለጸ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ፥ የእሳት አደጋው ዛሬ ከቀኑ 11 ሰዓት ከ 10 ደቂቃ አካባቢ ተከስቷል።
በአካባቢው በሚገኘው በአንድ ጅምር ሕንጻ ግራውንድ ላይ የተከማቸ የሕንጻ መሳሪያ ልዩ ልዩ ቁሳቁስ ላይ የእሳት አደጋ አጋጥሞ እንደነበረም ነው የገለጹት።
እሳቱን ለማጥፋት የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ባደረጉት ርብርብ እሳቱ ወደ ሌላ ቦታ እንዳይዛመት በማድረግ መቆጣጠር መቻሉንም ተናግረዋል ባለሙያው፡፡
የእሳት አደጋውን ለማጥፋት ስድስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና 2 የውሃ ቦቴ ከ40 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች መሰማራቱን አንስተው ፥ በአደጋው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩንና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት እየተጣራ መሆኑን አመልክተዋል።