የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በራሳቸው ላይ ግለ ግምገማ እንዲያካሒዱ የሚደነግግ ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጀ፡፡
ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የጥራት ኦዲት ስታንዳርድ መሠረት፣ በየጊዜው በተቋም ወይም በፕሮግራም ደረጃ ግለ ግምገማ ማካሔድ እንዳለባቸው የሚደነግግ ረቂቅ መመሪያ ለግምገማ ቀርቧል፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ግለ ግምገማውን የሚያደርጉት ባለሥልጣኑ በሚያዘጋጀው የግለ ግምገማ መመሪያ መሠረት እንደሚሆን የተገለጸ ሲሆን፤ የማንኛውም ተቋም የግል ግምገማ ሪፖርት ተቀባይነት ባገኘ በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ የጥራት ኦዲት ግምገማ መደረግ ይኖርበታል ተብሏል፡፡
በረቂቅ መመርያው እንደተገለጸው ተቋማዊም ሆነ የፕሮግራም ጥራት ኦዲት በተቋም ደረጃ የሚደረግ ሆኖ፣ ተቋሙ ከአንድ በላይ ካምፓሶች የሚኖሩት ከሆነ በተመረጡ ካምፓሶች የጥራት ኦዲት መደረግ አለበት፡፡
ረቂቅ መመሪያው በኢትዮጵያ ውስጥ በሚንቀሳቀስ በማንኛውም የመንግሥት እና የግል እንዲሁም ከውጭ ለሚመጣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋምና የትምህርት ፕሮግራም ላይ፣ በተጨማሪም በፌዴራል ደረጃ ለተቋቋመና ከውጭ አገር ለሚመጣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም ላይ ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል፡፡
የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ሁሉም የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በፌዴራል መንግሥት በጀት የሚተዳደሩና በውጭ አገር ባለሀብቶች በፌዴራል ደረጃ ፈቃድ የወሰዱ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ረቂቅ መመርያውን አስመልክቶ ያላቸውን አስተያየት እንዲያቀርቡ ጠይቋል፡፡ #ሪፖርተር
@tikvahuniversity