"በዳግም ምዝገባው ሒደት በራሳቸው ፈቃድ ሳይመዘገቡ የቀሩ እንጂ እኔ ሔጄ የዘጋሁት ተቋም የለም።" - የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
ባለሥልጣኑ ባወጣው “አዲስ ስታንዳርድ” መሰረት ዳግም ምዝገባ እንዲያደርጉ ባለፈው መስከረም ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል።
በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ሰነዶቻቸውን ያልላኩ ተቋማት ከዘርፉ በራሳቸው ፈቃድ እንደወጡ ይቆጠራል መባሉ ይታወሳል፡፡
በዚህ ሒደት 84 ተቋማት ለዳግም ምዝገባው ሰነዶቻቸውን ሳይልኩ በመቅረታቸው እንደተሰረዙ ተነግሯል፡፡
273 ተቋማት ደግሞ ሰነዶቻቸው ወደ ባለሥልጣኑ ቢልኩም የሚፈለጉትን ሰነዶች በሙሉ ያሟላ አንድም ተቋም አለመገኘቱን በባለሥልጣኑ የፈቃድ አሰጣጥ እና የጥራት ኦዲት ም/ዋና ዳይሬክተር ውብሸት ታደለ ለሸገር ኤፍኤም ተናግረዋል።
እነዚህ ሰነድ ያጓደሉ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ሰነዶቻቸውን እንዲያሟሉ ተጨማሪ 45 ቀን የጊዜ ገደብ እደተሰጣቸውም ገልፀዋል፡፡
ሰነዶቻቸውን ካልላኩ 84 ተቋማት ውጪ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ያገደውም ሆነ የሰረዘው ተቋም እንደሌለ አንስተዋል፡፡
ከእነዚህ መካካል የተለያየ ምክንያት በማቅረብ ድጋሚ ዕድል እንዲሰጣቸው የጠየቁ ተቋማት መኖራቸውንና ጥያቄያቸውም እየታየ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የዳግም ምዝገባ ሥራው በሒደት ላይ ሲሆን፤ በአሁን ሰዓት የሰነድ ማጣራት ሥራ እየተከወነ እንደሚገኝና በመጪዎቹ ሳምንታት ሰነድ ያሟሉ ተቋማት የመስክ ምልከታ በአዲስ አበባ እና በክልል እንደሚደረግ ጠቅሰዋል፡፡ ከመስክ ምልከታው በኋላ የተቋማቱ የመዘጋት ወይም የመቀጠል ዕጣ ፈንታ ይወሰናል ተብሏል፡፡ #ShegerFM
@tikvahuniversity