በፀጥታ ችግር ምክንያት በኢትዮጵያ ከ7.2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው አልተመለሱም፡፡ - የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)
በባሕር ዳር በመካሔድ ላይ በሚገኘው የአማራ ክልል የትምህርት ንቅናቄ መድረክ ላይ የተገኙ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፤ በፀጥታ ችግር ምክንያት በኢትዮጵያ ከ7.2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳልተመለሱ ተናግረዋል።
በአማራ ክልልሉ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን 7 ሚሊዮን ተማሪዎችን መዝግቦ ለማስተማር ቢታቀድም፤ በፀጥታ ችግር ምክንያት የተመዘገቡት ተማሪዎች 2.8 ሚሊየን ብቻ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ችግሩን ለመቅረፍ በትምህርት ዘመኑ በሁለት ዙር በተደረጉ ኢ-መደበኛ ምዝገባ 76 ሺህ ተማሪዎች ብቻ መመዝገባቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገልፀዋል።
መድረኩ በክልሉ የትምህርት ዘርፍ በደረሰው ጉዳት ላይ በመምከር ቀጣይ አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል፡፡
@tikvahuniversity