#ExitExamCertificate
ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት ቅፅ አዘጋጅቶ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልኳል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብሔራዊ የቅድመ-ምረቃ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል።
በቅድመ-ምረቃ መውጫ ፈተናው የአፈጻጸም መመሪያ መሰረት፥ የመውጫ ፈተና ውጤት በተማሪዎች ሰርተፍኬት (Temporary Degree) ወይም ትራንስክሪፕት ላይ አልፏል (PASS) ወይም ወድቋል (FAIL) በሚል እንዲቀመጥ ሚኒስቴሩ አዟል።
በዚህም የመውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች የሚሰጡ ኮርሶችን ማጠናቀቃቸውን የሚያረጋገጥ ሰርተፊኬት የሚሰጣቸው ሲሆን፤ ጊዜያዊ ዲግሪ የሚሰጠው ተፈታኙ/ተፈታኟ የመውጫ ፈተናውን በድጋሚ ወስዶ/ወስዳ የማለፊያ ነጥብ ሲያስመዘግብ/ስታስመዘግብ ብቻ እንደሚሆን በሰርተፊኬቱ ይገለጻል።
(የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ እና የመውጫ ፈተና የውጤት ሰርተፍኬት ፎርማት ከላይ ተያይዟል።)
@tikvahuniversity