በፌዴራል ተቋማት ላይ በተደረገ ፍተሻ የ129 የመንግሥት ሠራተኞች የትምህርት ማስረጃ ሐሰተኛ ሆኖ ተገኘ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የተቋማቸውን የዘጠኝ ወር ሪፖርተር ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባቀረቡት ወቅት እንደገለፁት፥ ትምህርት ሚኒስቴር የፌዴራል መስሪያ ቤት ሠራተኞችን የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ሥራ እያከናወነ ይገኛል።
በመጀመሪያ ዙር ከ280 የፌዴራል እና ተጠሪ ተቋማት መስሪያ ቤቶች ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተላከ መረጃን መሠረት በማድረግ የ32,815 ሰራተኞች የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛነት መጣራቱን አብራርተዋል።
በዚህም 129 ሐሰተኛ የትምህርት ማሰረጃ የተገኘ ሲሆን፤ የ469 ሰራተኞች መረጃ ያልተሟላ በመሆኑ ለሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተመላሽ ተደርጓል ብለዋል።
ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች የዲግሪ ሰርተፊኬት ህትመት በአንድ ማዕከል ማለትም በትምህርት ሚኒስቴር እንደሚታተም መገለፁ ይታወቃል። #ኢፕድ #GazettePlus
@tikvahuniversity