✏የደረሰን ጥብቅ መረጃ
(ግንቦት 20/ 2016 ዓ.ም ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ)
👉ሲኖዶሱ በመንታ መንገድ ፦
✍️ እነ አቡነ ገብርኤል፣አቡነ ሳዊሮስ፣አቡነ ኤዎስጣቴዎስ፣አቡነ ሩፋኤል፣ወዘተ..አቡነ ሉቃስ ተወግዘውና አቶ ተብለው ከቤተክርስቲያን እንዲለዩ፣ሲኖዶሱ ነገሩን ቀለል ለማድረግ የሚሞክር ከሆነ ወይም አቡነ ሉቃስን በተግሳጽ ሊያልፋቸው ከሞከረ በጽኑ እንደሚታገሉና በአቋማቸው ጸንተው በልዩነት እስከ መውጣት የሚደርስ አቋም በመያዝ ሲኖዶሱን ለሁለት እስከመክፈል ድረስ ለመታገል በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ።
✍️ ይህንን ዓላማቸውን ለማስፈጸም አቡነ ፋኑኤል፣አቡነ ቀሌምንጦስና አቡነ ኤርምያስን በአጋዥነት ለመጠቀም አቅደው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። በተጨማሪም ዓላማቸውን ለማስፈጸም ይረዳቸው ዘንድ አጀንዳ አርቃቂ ውስጥ አቡነ ሳዊሮስን ወይም አቡነ ሩፋኤልን ወይም አቡነ ኤዎስጣቴዎስን ወይም አቡነ ገብርኤልን ለማስገባት አቅደው እየሰሩ እንደሚገኙ ።
✍️ የሲኖዶስ ጸሐፊውን አቡነ ጴጥሮስን በተመለከተ በምትካቸው በሕጉ መሰረት ሁለተኛ የወጡትን ጳጳስ መተካት ይገባል በሚል አቡነ ሩፋኤል አቡነ ጴጥሮስን እንዲተኩ በማድረግ በቀሪ የሥራ ዘመናቸው አቡነ አብርሃምን በቅርበት በመከታተል መግለጫ እንዳይሰጡ፣ሕዝበ ክርስቲያኑን በተለይም ወጣቱን ትውልድ እንዳያስተባብሩና እንዳይመሩ እጆቻቸውን አስሮ ማቆየትና ፓትርያርኩ ላይ ጥቃት የሚፈጠርበትን ሁኔታ በመፍጠር የኦሮሞ ፓትርያርክነትን እውን የማድረግ ተልእኳቸውን በአጭር ጊዜ ተፈጻሚ ለማድረግ አቡነ ሩፋኤል ተልዕኮ ወስደው እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ፦
✍️ ሌላኛው ቡድን ወይም ከእነ አቡነ ሩፋኤል በተቃራኒው የሚገኙት ጳጳሳት ደግሞ በአቡነ ጴጥሮስ ምትክ ጳጳስ ከመመደብ ይልቅ ተወካዩ ወይም ምክትል ጸሐፊው ሥራውን እየሰሩ እንዲቆዩ የቅዱስ ሲኖዶስ አጀንዳ አጭርና ውዝግብ የሌለበት በማድረግ ጉባኤው በአጭር ጊዜ ሊቋጭ ይገባል ብለው የሚንቀሳቀሱ ሲሆኑ ፦
✍️ እነዚህ ጳጳሳት ማንንም ማውገዝ አያስፈልግም የሚል ዓላማ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ሲሆኑ አቡነ ሉቃስ ተወግዘው መለየት አለባቸው የሚል ጠንካራ አቋምና የመንግስት ተልዕኮ የተቀበሉ ጳጳሳት ደግሞ አቡነ ሉቃስን ለማውገዝ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን የከዚህ ቀደም ንግግርና የአቡነ ዮሴፍን የፓትርያርኩ ንግግር የግላቸው እንጂ የሲኖዶስ አቋም አይደለም ያሉትን መግለጫ በመጥቀስ መርጦ አልቃሽ አትሁኑ የሚል አቋም ይዘው ውግዘቱን ለመተግበር በቆራጥነት እየተንቀሳቀሱ ናቸው።
✍️ በአጠቃላይ የዘንድሮ ሲኖዶስ አቡነ ጴጥሮስን አጀንዳ ያለማድረግ፣አቡነ ሉቃስን በጽኑ ማውገዝ፣ከውጭ ወደ አገር ውስጥ መግባት የተከለከሉ አባቶች ጉዳይ አጀንዳ የማይሆንበት ፣አገዛዙም አቡነ ሉቃስ እንዳይወገዙ የሚጥሩ አባቶች ማንነት ተለይቶ ዝርዝራቸው እንዲደርሰው አቅጣጫ ያስቀመጠበት ፣አብላጫው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አቡነ ሉቃስ እንዳይወገዙ ውሳኔ ካስተላለፈ የሥርዓቱ ደጋፊዎች በልዩነት ወጥተው የሥርዓቱ አቀንቃኝነታቸውን በይፋ ለማረጋገጥ ቃል ኪዳን የገቡበት በአይነትና በይዘቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ልዩ የሆነ መንፈሳዊ ይዘት የሌለው ጉባኤ እንደሚሆን የውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን ለኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ አጋርተውናል ፦
©️ Ethio beteseb media