✅ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሂም
👉👉 እንቁጣጣሽ መጨረሻው ጣጣ
እንዳይሆን ጥንቃቄ ያስፈልጋል!!!
❌ የኢትዮጵያ ሙስሊም ግንዛቤ የሚፈጥርለት በማጣቱ ምክንያት የካፊሮችን ክብረ በዓል እንዴ እንቁጣጣሽ፣ ገና፣ መስቀል፣ ጥምቀት፣ የግንቦት ልደታ፣ ኢሬቻ፣ ቡሄ፣... የመሳሰሉትን የኩፍር በዓላት ሲያከብር ይስተዋላል። በአላህ ፍቃድ በጥቂት የአላህ ባሪያዎች ሰበብ እና ጥረት በጣም በተሻለ መልኩ ለውጥ አለ። ቢሆንም በአሁኑ ጊዜም ግንዛቤ የሚፈጥርላቸው ያጡ ወይም በአንዳንድ ሰዎች መዘናጋት ምክንያት የተሸወዱና በነዚህ የኩፍር በዓላት ላይ የሚሳተፉ አይጠፉምና በየአጋጣሚው ወገኖቻችንን ከዚህ ጥፋት ልናነቃ ይገባል።
⭕️ሙስሊሞች አመታዊ የሆኑ ሁለት በዓሎች ብቻ አሉን፤ እነሱም ዒባዳዊ በዓሎቻችን ናቸው። ክርስቲያኖች፣ አይሁዶችና ሌሎች ጣኦታዊያንም የራሳቸው ብቻ የሆኑ ሀይማኖታዊ በዓሎች አሏቸው። የኢስላም ሊቃውንቶች ከቀድሞ ዘመን ጀምሮ የቁርኣንና የሀዲስ እንዲሁም የሰለፎችን መነሻ መሰረት በማድረግ ሙስሊሞች የራሳችንን በዓሎች እንጂ የሌላ ሀይማኖት ተከታዮችን ወርሃዊም ይሁን አመታዊ በዓሎቻቸውን በጋራ ማክበርና እንኳን አደረሳችሁ በማለት ማስደሰት በኢስላም በጥብቅ የተከለከለና የተወገዘ ተግባር መሆኑን ገልፀውልናል።
قال ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ
وَالَّذِينَ لَا يَشْهَدُونَ الزُّورَ وَإِذَا مَرُّوا بِاللَّغْوِ مَرُّوا كِرَامًا
አላህ እንዲህ ይላል፦
«እነዚያም በውሸት የማይመሰክሩ ወይም ውሸት እና መሰረት የሌለው ነገር ላይ የማይጣዱ(የማይገኙ)፤ ውድቅ ቃልም (በሚናገር ሰው አጠገብ) ባለፉ ጊዜ የተከበሩ ኾነው የሚያልፉ ናቸው፡፡»
[ሱረቱ አል-ፉርቃን፣ - 72]
❌ከዚህ ባስ ሲልም እንደኢኽዋንና መሰል አስተሳሰብ የተሸከሙ ሰዎች በፖለቲካ ideology ዲንን እናገለግላለን በሚል አጉል መንጠራራት የካፊር በዓሎችን ማክበር የሚቻል እስኪመስል ድረስ የማክበሪያ ቦታ በማፅዳት በየሚዲያዎቻቸው በመቅረብ ድምቀት ይሆናሉ። ይህም ተገቢ አይደለም።
قال ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ
وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ
አላህ እንዲህ ይላል:–
"በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡"
[አልማኢዳህ: 2]
⭕️እነዚህ የሙስሊም ተወካይ ነን እያሉ የካፊሮችን በዓል የሚያደምቁ ሰዎች እየነደፉ ያሉት ክፉ የሆነ ሱና ነው። እነሱን አይቶ በሚሰራው ሰው ሁሉ ጥፋት ሁሉ ተጠያቂ ናቸው።
ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:–
وَمَنْ سَنَّ فِي الْإِسْلَامِ سُنَّةً سَيِّئَةً كَانَ عَلَيْهِ وِزْرُهَا وَوِزْرُ مَنْ عَمِلَ بِهَا مِنْ بَعْدِهِ مِنْ غَيْرِ أَنْ يَنْقُصَ مِنْ أَوْزَارِهِمْ شَيْءٌ
"በኢስላም ውስጥ መጥፎ ፈለግን የነደፈ ሰው ወንጀሉ በሱ ላይ አለበት። ከሱ በሁዋላ የሰሩበት ሰዎችም ወንጀል አለበት፣ ከነሱ ወንጀሎች ምንም ነገር ሳይቀንስ።"
[ሙስሊም: 1017]
እንዲህም ብለዋል:–
وَمَنْ دَعَا إِلَى ضَلَالَةٍ كَانَ عَلَيْهِ مِنَ الْإِثْمِ مِثْلُ آثَامِ مَنْ تَبِعَهُ، لَا يَنْقُصُ ذَلِكَ مِنْ آثَامِهِمْ شَيْئًا
"ወደ ጥመት የተጣራ የተከተሉት ሰዎች አምሳያ ወንጀሎች አሉበት። ይህም (በሱ ላይ መታሰቡ) ከወንጀሎቻቸው ምንም አይቀንስም።"
[ሙስሊም: 2674]
❌በየትኛውም መልኩ አድሉን ካገኘን ሙስሊሞችን ከመጥፎ ነገሮች ማስጠንቀቅ እንጂ ወደ ጥመት መጣራት ተገቢ አይደለም። በፍፁም!
⭕️ አንዳንድ ወንድሞች አላህ ይዘንላቸውና ሚዲያዎችን ወይም ሌሎች አማራጮችን ተጠቅመው እንቁጣጣሽ የሁሉም ህዝብ በዓል ነውና ሁላችንም እናክብር የሚል አደምታ ያለው መልዕክት ያስተጋባሉ። ከዚህ ድርጊታቸው መቆጠብ አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው። ከላይ ያየናቸው ሀዲሶችም ዋና ምስክር መሆን ይችላሉ።
❌ከአላዋቂ ወንድሞቻችን ይህንን አስቀያሚ ጥፋት ባየን ጊዜ ልንቃወም ይገባል። ዝምታ ለሁሉም የሚተርፍ መከራ አለው። በመሆኑም ዝም ከማለት ይልቅ የምንችለውን አድርገን ሙስሊሞችን ከጥፋት መታደግ ይገባል።
አላህ እንዲህ ይላ፦
(لُعِنَ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ بَنِي إِسْرَائِيلَ عَلَىٰ لِسَانِ دَاوُودَ وَعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ ۚ ذَٰلِكَ بِمَا عَصَوْا وَكَانُوا يَعْتَدُونَ * كَانُوا لَا يَتَنَاهَوْنَ عَنْ مُنْكَرٍ فَعَلُوهُ ۚ لَبِئْسَ مَا كَانُوا يَفْعَلُونَ)
[سورة المائدة 78 - 79]
"ከእስራኤል ልጆች እነዚያ የካዱት በዳውድና በመርየም ልጅ በዒሳ ምላስ ተረገሙ፡፡ ይህ ትእዛዝን በመጣሳቸውና ወሰንን የሚያልፉ በመሆናቸው ነው፡፡ ከሰሩት መጥፎ ነገር አይከላከሉም ነበር፡፡ ይሰሩት የነበሩት ነገር በእርግጥ ከፋ!"
[አልማኢዳህ: 78–79]
⭕️ካፊር ጓደኞቻችን፣ ዘመዶቻችን፣ ጎረቢቶቻችን፣ የስራ ባልደረቦቻችን፣ የሰፈራችን ሰዎች ወዘተ እንዳይከፉብን እያልን በካፊሮች በዓል መታደም ትልቅ ስህተት ነው።
ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:–
(مَنِ الْتَمَسَ رِضَى اللَّهِ بِسَخَطِ النَّاسِ ، رَضِيَ الله عَنْهُ ، وَأَرْضَى النَّاسَ عَنْهُ ، وَمَنِ الْتَمَسَ رِضَا النَّاسِ بِسَخَطِ اللَّهِ ، سَخَطَ اللَّهُ عَلَيْهِ ، وَأَسْخَطَ عليه الناس)
"ሰዎች እየተከፉም ቢሆን የአላህ ውዴታ የፈለገ ሰው አላህ ይወደዋል። በሰዎችም ያስወድደዋል። አላህን በማስቆጣት የሰዎችንም ውዴታ የፈለገ ሰው አላህ ይቆጣበታል። ሰዎችንም ያስቆጣበታል።"
[ኢብኑ ሒባን ዘግበውታል።]
❌ስለዚህ እኛ ነቅተን ሌሎችንም ማንቃት አለብን። ከቤተሰብ ርቀን የምንገኝ ሁሉ ደውለን እናብራራላቸው። ይህ ዘመን መለወጫ የሚሉት ወይም እንቁጣጣሽ የሚሉት በዓል የማይፈቀድ ነገር ፈፅመን ከባድ ጣጣ እንዳያመጣብን መጠንቀቅ እና ማስጠንቀቅ ይገባል እላለሁ !
አቡ ሷሊሀ አብዱል ከሪም ደሴ
https://t.me/Tuaifetul_mensura