💐ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና
📖“ነገር ግን፥ ነፍሴ ሆይ፥ አንቺ ለእግዚአብሔር ተገዢ፥ ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና።”
መዝሙር 62፥5
ሕይወትን ጣፋጭና ተወዳጅ ከሚያደርጓት ነገሮች አንዱ ተስፋ ነው። ተስፋ የሌለው ሕይወት ካለመኖር ተለይቶ ሊታይ አይችልም። ይህ ተስፋ አሁናዊ ጨለማችን ነገ ላይ በታላቅ ብርሃን እንደሚለወጥ ለውስጣችን ይነግረዋል። ከዛሬ ነገ የተሻለ እንደሚሆንም ያረጋግጥልናል።
ብዙዎች በተለያዩ ነገሮች ላይ ልባቸውን በመጣል ተስፋ ያደርጋሉ። አንዳንዶች ተስፋቸውን ቁሳዊ ነገር ላይ ይተክሉትና ተስፋ ያደረኩት ነገር አልሆን ሲል ለታላቅ የልብ ስብራት ይዳረጋሉ። ሌሎች ደግሞ "ለእኔ ያለሁት እኔው ራሴ ነኝ" በማለት ራሳቸውን ብቻ ታምነው ተስፋ ያደርጋሉ። ነገር ግን የሰው ልጅ ሁሉን ቻይ አይደለምና ያሰቡት ነገር በሙሉ ከመሬት ላይደርስ ይችላል። ታዲያ በዚህን ጊዜ "እኔ ምንም ነገር ማድረግ አልችልም በቃ" በማለት ራሳቸውን ከባድ ጭንቀት ውስጥ ይከትቱታል።
ዳዊት ለነፍሱ እንዲህ ይላታል፦ “ነገር ግን፥ ነፍሴ ሆይ፥ አንቺ ለእግዚአብሔር ተገዢ፥ ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና።” (መዝ 62፥5) እውነተኛውና ዘላቂነት ያለው ተስፋ የሚገኘው ከእግዚአብሔር ብቻ ነው። ማን ነው እርሱን ተስፋ አድርጎ አውላላ ሜዳ ላይ የቀረው? ማንስ ነው በሀዘን ዓይኖቹ የፈዘዘው? ማንም! ስለዚህ ተስፋችንን ከእግዚአብሔር ጋር እናቆራኘው። እርሱ ለተስፋ ቃሉ ታማኝ ነውና።
ይህን ህያው ቃል ለሌሎች አጋሩት🦋
Join Our Channel ⭐
🔥@Urim7🔥