💐በፊትህ
📖“አቤቱ፥ ረድኤቴ መድኃኒቴም፥ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን።”
— መዝሙር 19፥14
ዳዊት የፀሎት መዝሙሩን እንደቀጠለ ነው። በዚህ ክፍል ላይ ደግሞ እንዲህ በማለት በአምላኩ ፊት ፀሎቱን ይዞ ይቀርባል፦ “አቤቱ፥ ረድኤቴ መድኃኒቴም፥ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን።” (መዝ 19፥14)
ከዚህ ከዳዊት የፀሎት መዝሙር በመነሳት በምድር ላይ ያሉ ሰብዓዊያንን በአምስት ክፍሎች መመደብ እንችላለን። አንደኛው ምድብ፣ ከአንደበታቸው የሚያወጡት ቃላቶች ውሸት የሞላባቸውና ልባቸው በትዕቢት የተወጠረ ነው። በሁለተኛው ምድብ የሚገኙ ሰዎች ደግሞ በምላሳቸው ውሃን የሚጠብሱ ደላዬች ከመሆናቸው በተጨማሪ ልባቸው በክፋት የሰከረ መሰሪዎች ናቸው። ለአፋቸው ቃል ለከት የማያበጁ፣ ነገር ግን ልባቸው ንፁህ የሆኑ ሰዎች በሶስተኛው ምድብ ሲመደቡ የአፋቸው ቃልና የልባቸው ሀሳብ "በሰዎች" ዘንድ ያማረ የሆኑት ሰዎች ደግሞ አራተኛውን ምድብ ይይዛሉ። በመጨረሻው ምድብ የሚገኙት ሰብዓዊያን የአፋቸው ቃልና የልባቸው ሀሳብ "በእግዚአብሔር ፊት" ያማረ የሆነ ነው። ምን አልባት "ለምን በእግዚአብሔር ፊት ብቻ? በሰዎችስ ፊት መልካም መሆን የለበትም?" ብለን ጥያቄን ልናነሳ እንችል ይሆናል። በእግዚአብሔር ፊት ያማረ ቃልና የሰመረ የልብ ሀሳብ በሰዎች ዘንድ ክፉ ሊሆን ከቶ አይችልም።
ምድቤ ከመጨረሻው ይሆን ዘንድ ናፍቆቴና መሻቴ ነው። እናንተስ? የዳዊት መሻት ራሱን ከመጨረሻው ክፍል ማግኘት ነበር። ወገኖቼ፣ የአፋችን ቃል በእግዚአብሔር ፊት ያማረ ይሆን ዘንድ ያስፈልጋል። ያዕቆብ ይህንን ሀሳብ እንዲህ በማለት ያፀናዋል፦ “አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፥ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፥ በገሃነምም ይቃጠላል።” (ያዕ 3፥6) ለዚህ ነው አንደበቶቻችንን ልንገራ የሚያስፈልገው። ነብዩ ኤርምያስ ደግሞ የሰው ልጅ ልብ የአመፅ ስፍራ እንደሆነ ይናገራል። “የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው፤ ማንስ ያውቀዋል?” (ኤርም 17፥9)
ወገኖቼ፣ ዛሬ የለውጥ እርምጃን ልንራመድ ያስፈልጋል። ምን አልባት እስካሁን አንደበታችንን ባለመግራት ብዙ ጥፋቶችን ሰርተን፣ ሰዎችንም አሳዝነን ሊሆን ይችላል። የልባችንም ሀሳብ ከፍቶ እግዚአብሔርንና ሰዎችን በድለን ይሆናል። እንመለስ! ከሁሉ ይልቅ የበደልነው እግዚአብሔርን ነውና አስቀድመን በንሰሃ ፊቱ እንቅረብ። በመቀጠል ደግሞ የበደልናቸውን ሰዎች በመፈለግ ይቅርታን እንጠይቃቸው። ይህን ስናደርግ ሰማይ በታላቅ ደስታ ይሞላል።
🔥@Urim7🔥