ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ደግሞ እንድህ ይላል " ዮሐንስ 5:26 አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው፥ ለልጁም በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቷል።
በአንድ ነጥብ ብቻ ፍጹም መመሳሰልን እንደሚያመለክት ታያለህን? አንዱ አባት ሌላው ልጅ በመሆኑ ነው። “ሰጥቷል” የሚለው አገላለጽ ይህን ልዩነት ብቻ ያስተዋውቃል፥ ነገር ግን ሌላው ሁሉ እኩልና በትክክል አንድ እንደሆነ ይገልጻል። ስለዚህም ወልድ እንደ አብ በብዙ ሥልጣንና ኃይል ሁሉን ነገር እንደሚያደርግና ከሌላ ምንጭ ሥልጣን እንዳልተሰጠው ግልጽ ነው፥ እርሱ እንደ አብ ሕይወት አለውና። ስለዚህም፥ ሌላውንም እንድንረዳ የሚከተለው ወዲያውኑ ተጨምሯል። ይህ ምንድን ነው? እርሱ፥ ዮሐንስ 5:27 የመፍረድ ሥልጣን ደግሞ ሰጥቶታል። ስለ ምንስ ስለ ትንሣኤና ስለ ፍርድ ዘወትር ይናገራል? እርሱ እንዲህ ይላልና፥ አብ ሙታንን እንደሚያነሣ ሕያውም እንደሚያደርጋቸው ወልድም ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣል ይላልና፤ ደግሞም አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም፤ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ፤ ደግሞም፦ ለአብ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ። ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው በራሱ ሰጠው ”፤ ደግሞም፥ “የ[የእግዚአብሔር ልጅን ድምጽ] የሰሙት በሕይወት ይኖራሉ”፤ እዚህም ደግሞ፥ “የመፍረድ ሥልጣን ሰጥቶታል” ይላል። ስለ ምንስ ስለ እነዚህ ነገሮች ዘወትር ይናገራል? ማለቴም ስለ ፍርድና ስለ ሕይወትና ስለ ትንሣኤ? እነዚህ ጉዳዮች ግትር የሆነውን አድማጭ እንኳን ከማንም በላይ ለመሳብ ስለሚችሉ ነው። ይነሣ ዘንድ ለክርስቶስም ስለ ኃጢአቱ መልስ ይሰጠው ዘንድ የተረዳ ሰው፥ ሌላ ምልክት ባያይም፥ ይህን አምኖ ለፈራጁ ለማማለድ በእርግጥ ወደ እርሱ ይሮጣል።
"