የማንቂያ ደወል / Yemankiya Dewel


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ታላቅ የምሥራች ለተዋህዶ ልጆች በሙሉ የማንቂያው ደወል
በተለያዩ ገዳማትና አድባራት እንዲሁም በመላው ዓለም
የሚያደርጋቸውን መንፈሳዊ ትምህርቶችና ስብከቶች
እንዲሁም ዝማሬዎችን ለመከታተል ትችሉ ዘንድ
ይህን ቻናል ስለተከፈተ ሁላችሁም ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ እንድትሆኑ በፍቅር ቃል ለማሳወቅ እንወዳለን። ይህ በየማንቂያው ደወል ተከታይ ወጣቶች የተከፈተ መሆኑ ይታወቅልን።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ካላንደር ሳይዘጋው መንገድ የዘጋው ሜክሲኮ ልደታ።


ደሴ ከተማ ዛሬ በርዕሰ አድባራት መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን በምዕመናን ተጥለቀለቀ


የማንቂያው ደውል በቦሌ ደ/ሳ/መድኃኔዓለም


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ነገ ሚያዝያ 26 በቦሌ መድኃኔዓለም የሚደረገው ጉባኤ አንድ ቀን ብቻ ቀረው::የደብሩ አስተዳዳሪና የስብከተ ወንጌል ክፍሉ እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና ማኀበራት ዝግጅታቸውን እንዳጠናቀቁ እየነገሩን ነው::ከእኛ የሚጠበቀው በሰዓቱ መገኘት ብቻ ነው::ሼር በማድረግ ህዝበ ክርስቲያኑ እናት ቤተክርስቲያን ወዳዘጋጀችው ድግስ እንዲመጣ ማድረግ በእግዚአብሔር ዘንድ ትልቅ ዋጋ አለውና ሼር እናድርግ::እንደውል:እንጻፍ መልዕክት እንላላክ የምናውቃቸውን ሁሉ እየደወልን እንጋብዝ....የነገ ቀጠሮአችን በእግዚአብሔር ቤት ይሁን::ለዚህም እግዚአብሔር ይርዳን::


ይኸው ነው እውነቱ


የቅዱስ ፓትርያርኩ መልዕክት

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ በሚል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ኃይለ ቃል በመቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ከቅዱስነታቸው ከጎሳ ጠብ ወደ ሃይማኖት አስከፊ ጠብ ተሸጋግረናል ፤ ከእልቂትና ከጠብ የሚያተርፈው ፀላኤ ሠናያት የሆነው ዲያብሎስ ብቻ ነው በማለት ነው መልእክታቸውን ያስተላለፉት።


ሰበር ዜና
በመስቀል አደባባይ የሚደረገው ሕገ ወጥ ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጠየቀ !!!

ሚያዝያ 21 ቀን 2014 ዓ.ም (ተሚማ/አዲስ አበባ)

++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

ከአ.አ ከተማ አስተዳደር ጋር የተደረገው የጋራ ውይይት እልባት ሳያገኝ በቤተ ክርስቲያናችን ታሪካዊ ይዞታ መስቀል አደባባይ ላይ የሚደረግ ማናቸውም ሥነ ሥርዓት ተቀባይነት የለውም ያለው ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ፣ ለሰላም ሚኒስቴር ፣ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ፣ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ፣ ለአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት በጻፈው ደብዳቤ


ጎንደር ላይ ለተገደሉት ሙስሊም ወንድሞቻችን እናዝናለን፣ ድርጊቱንም እናወግዛለን። ነገር ግን ጎንደር ላይ ለተገደሉት ሙስሊሞች አዝነናል ማለታችን ጎንደር ላይ በተገደሉት ክርስቲያኖች ተደስተናል ማለታችን አይደለም። በአንጻሩ የመስጊድ መቃጠልን እናወግዛለን ስንል ደግሞ የቤተክርስቲያንን መቃጠል ለበጎ ነው እያልን እንደግፋለን ማለታችን አይደለም።እንደ ዜጋ ሁላችንም በሀገራችን ላይ እኩል የመኖር መብት አለን።ክርስቲያኑ ሲሞት ለበጎ ነው፣ከጥንት የበረ ነው፣ አዲስ ነገር አይደለም፣ እያሉ ማለባበስ፣የሌላው ወገን ሲሆን ደግሞ ነገሩን ከፍተኛ ትኩረት መስጠትና በመግለጫ ብዛት ጉዳዩን ማጮህ ፍትሀዊ አይደለም።በሁሉም ወገን የሞተው ሰው ነው።ሙስሊሙም፣ክርስቲያኑም፣መገደል የለባቸውም:: መስጊዱም፣ቤተክርስቲያኑም፣መውደም የለባቸውም።ወይብላ ማርያም ላይና አቃቂ ቃሊቲ ላይ ለተገደሉት ክርስቲያኖች እና ጎንደር ላይ ለተገደሉት ሙስሊሞች ሀዘናችን እኩል ይሁን።ሞጣ ላይ ስለተቃጠለው መስጊድ የጮህነውን ያህል፣ዛሬ ወራቤ ላይ ስለተቃጠሉት፣ አንድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንና ሶስት የፕሮቴስታንት ቤተ አምልኮ እኩል መጮህ ካልቻልን፣አሁንም ፍትህ ወዴት ናት ያስብላልና።የአንዱን በኡኡታ የሌላውን በዝምታ፣ማስተናገድ ይቅር።ገዳይም፣አቃጣይም፣የሃይማኖት ጦርነት ቀስቅሶ፣ሕዝቡን ለማጫረስ፣ኢትዮያንም ለማፍረስ፣ወይንም ርካሽ የፓለቲካ ትርፍ ለማግኘት፣ከዛም አልፎ በሃይማኖት ሽፋን ብሄር ተኮር ጥቃት ለመፈጸም ያቀደና የቌመጠ ሁሉ አደብ የሚገዛው፣መልካም የሠራን የሚሸልም፣ጥፋተኛውንና ወንጀለኛውን፣ደግሞ ለህግ አቅርቦ የሚቀጣ፣ፍትህ ሲሰፍንና የህግም የበላይነት ሲረጋገጥ ብቻ ነው።


ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሠላም እምይዕዜሰ፤ ኮነ፤ ፍስሐ ወሠላም፡፡

ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሣ፤ ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍጹም ሰላምና ደስታ ሆነ።

እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም!!!
ማቴ ፳፰፣፮

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ!

የማንቂያ ደወል 🔔🔔🔔


እንዲህ ስንደማመጥ ደስ ይላል።ነገ በስቅለት በዓል ሥራ ግቡ የሚለው መመሪያ ተሽሮአል።ስለዚህ ኦርቶዶክሳውያን ያለምንም ሰቀቀን የስቅለትን በዓል አክብሩ።ፈጣን ምላሽ ለሰጣችሁ የአዋሽ ባንክ አመራሮች እናመሰግናለን።


አዋሽ ባንክ እጅህን ከቤተክርስቲያን ላይ አንሳ! ካላንደር የዘጋውን ኦርቶዶክሳዊ የስቅለት በዓልን ካላንደር ሽረህ የሥራ ቀን ለማድርግ የምታደርገውን ፀረ ኦርቶዶክስ ዘመቻ አቁም!!!!

#ሼር


የብርሃን ማዕበል በጅጅጋ



Показано 13 последних публикаций.

8 923

подписчиков
Статистика канала