ወዳጄ
በማለዳ ለመነሣት የሚያግዝህ በጊዜ መተኛት ነው ። እንቅልፍህን ሊጋፉ የሚችሉ ስልኮችና ሰው ሠራሽ ዕይታዎችን በጊዜ አቁም ። የምግብ ሰዓትህን ካላከበርህ ብትበላም እንደምትታመም ፣ የእንቅልፍ ሰዓትህን አለማክበርህ ብትተኛም ጤነኛ አያደርግህም ። በማለዳ ተነሣ ። ይህች ቀን ከዛሬ በፊት አይተሃት አታውቅምና አዲስ ቀን ናት ። ፀሐይ በምሥራቅ ስትወጣ ይህን ውበት ለማድነቅ በጠዋት ተነሣ ። የማለዳ ጸሎት አለና ያንን ለማድረስ በጠዋት ተነሣ ። እንቅልፍ የሞት ፣ መንቃትም የትንሣኤ ምልክት ነውና በማለዳ ተነሣ ።
ቅዱሳን አባቶች ሁሉ በማለዳ የሚነቁ ነበሩ ። በዓለም ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጡ ሰዎች የማለዳ ሰዎች ናቸው ። ከእንቅልፍ ለመነሣት ስንፍና ሲጫጫንህ ድሀ ለመሆን ወስነሃል ማለት ነው ። ደግሞም ሌሊቱን በሙሉ ሲያመሰግኑ ያደሩ ካህናትን አስታውስና በማለዳ ተነሣ ። ሌሊት በሙሉ ሲጠብቁ ያደሩ ሠራዊትን አስብና በማለዳ ተነሣ ። ሌሊት በሙሉ ሲጓዙ ያደሩ ፣ ሲያመርቱ ያነጉ መንገደኞችና ሠራተኞችን አስብና በማለዳ ተነሣ ። ይህች ቀን አይተሃት የማታውቃት ብቻ ሳትሆን ላትደገም የምታልፍ ቀን ናት ። ስለዚህ ቀኑን ዋልበት እንጂ አይዋልብህ ። በማለዳ ተነሣ ብዙ ትርፍ ታገኛለህ ። ሱሰኞች ማለዳቸውን ይበላሉ ። በጉልበት ለመነሣት ይቸገራሉ ። ማለዳን ክፉ ባልንጀርነቶች ያበላሹታል ። ማለዳህ እንደ ማታህ ነውና በጊዜ ተሰብሰብ ፣ በጊዜ ንቃ ! ዶሮ ራሱ ሳይነቃ ሌላውን አያነቃምና የበታች ሠራተኞችህን ለማበረታታት በማለዳ ተነሣ ።
እግዚአብሔር ያግዘን
#ዘሰዋስው
https://t.me/ZSewasw