ወዳጄ....ዲቁና
መጨረሻ
ዲያቆን የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም ። እንደ ውኃ እናት ከውኃ አይለይም ፣ ከውኃ ውጭ አይደፍርም ። አለልክ መብላትም የመስከር ያህል ነው ። ዲያቆን መጥኖ የሚበላ ፣ በምግብ ብዛት ዕድሜውን የማይጐዳ ነው ። ዲያቆን ከብዙ ሴቶች ጋር ወዳጅ የሚሆን ፣ የቆነጃጅት አጃቢና አጫዋች አይደለም ። መፍራት ገደሉን ሳይሆን የሚያዳልጠውን ስፍራ ነው ። አርቆ ማጠር የዲያቆን መገለጫ ነው ። አንድ ዲያቆን እውቀት ፣ ምሥጢር ጠባቂነት ፣ ጠንቃቃነት ያስፈልገዋል ። እንደ ወታደር የሚዘምት ፣ እንደ ሰላይ ለቤተ ክርስቲያት ጆሮ የሆነ ነው ። መጠጥና ሴት የሚወድድ ወታደርም ደኅንነትም መሆን አይችሉም ። ሁለቱም ጎበዙን ሁሉ ወንፊት ያደርጉታልና ። ዲቁና ትልቅ ሥልጣን ነው ። ብሉይ ሐዲስን ነገር መለኮትን ላላወቀ አይሰጥም ። ዲቁና ትልቅ ሥልጣን ነው ። ምእመናን ሊያከብሩት ይገባል ። ቀዳሜ ሰማዕት እስጢፋኖስ ዲያቆን ነበረ።
#ዘሰዋስው
https://t.me/ZSewasw