ለዛሬ የመጨረሻ መልእክቴ…
"…ነገ ሰኞ የእረፍት ቀኔ ነው። ከእግዚአብሔር ሰላምታው በኋላ 1ሺ ሰዎች አመስግነው ሲጨርሱ የቤቴንም በር የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁንም እቆልፈዋለሁ። የምንገናኘው ማክሰኞ ጠዋት በርእሰ አንቀጻችን ነው። ከመሰነባበታችን በፊት ግን አፋጎን ምክር ልለግሰው።
"…ወዳጆቼ የእኔ ጎጃም መግባት ቢጠቅማችሁ እንጂ አይጎዳችሁም። እኔ እንደሌላው በውሸት ፕሮፓጋንዳ ሕዝብን ማደንዘዝ አልፈልግም። ሸዋ፣ ወሎና ጎንደር ገብቼ ኮሶ እንደጋትኳቸው እናንተ ጋር ጎጃም ገብቼ ማር አልግትህም፣ ወተትም አላስጎነጭህም። እንዲያሽርህ አድርጌ መቅመቆ ነው የማጠጣህ የምግትህም። ምን ታመጣለህ?
"…የፎቶ ቦለጢቃ ይብቃ። የውሸት ሰበር ዜና ይብቃ። የሕዝቡን መከራና ሰቆቃ አታራዝሙ። በውስጣችሁ የተሰገሰጉትን የትሪፕል ኤ፣ የብአዴን፣ የኢዜማ፣ የግንቦት ሰባት፣ የብልፅግናና የወያኔ ኤጀንቶችን በቶሎ አጽዱ። ሠራዊቱ የወታደር ቁመና ይኑረው። በካምፕ ጠርንፉት። ሞባይል ጠርንፉ። የመዋጋት አቅም፣ መሳሪያ፣ ወኔና ጀብዱ መሥራት የሚችል ሕዝብ ይዛችሁ በተኩላ አታስበሉት። ጀግኖቹን የበላይ ዘለቀና የእጅጉ ዘለቀን የአንበሳ መንጋ በበጎች መንጋ አትምሩት። አንበሳን መምራት ያለበት አንበሳ ብቻ ነው።
"…እስቲ ጨክናችሁ ድርጅታዊ ጉባኤ ጥሩ። ራሳችሁን ገምግሙ። የደከመውን ቀይሩት። ገና ምኑም ላልተያዘ ሥልጣን በቤተሰብ በጓደኛ ተቋሙን አትሙሉት። የሚሞትላችሁ አልጠፋ፣ እንዴት ሌባና ዘራፊን መሪ አድርጋችሁ ታስቀምጣላችሁ? እንዴት የትግሬ ምርኮኛን የሚሸጥ ፋኖ ታፈራላችሁ? ነውር እኮ ነው።
"…በፌስቡክ፣ በቴሌግራም፣ በዩቱዩብ፣ በቴሌቭዥን የሚበዙት የጎጃም ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች ናቸው። እንዴት ሕዝቡ በራሱ ልጆች ሲዘረፍ፣ ሲገደል አስችሏቸው ባዶ ዲስኩር ሲደሰኩሩ ይውላሉ?
• ስደበኝ ተንጫጫ እኔ ግን አልፋታህም።