"ርእሰ አንቀጽ"
"…ቅድምዬ እንደነገርኳችሁ ወደ ጮቄ ተራራዬ ወደ ማረፊያዬ፣ እስከ መስከረም፣ እስከ እንቁጣጣሽ ድረስ ወደ ምቆይበት ወደ ጎዣም ምድር አልተመለስኩም። እዚያው የስደት ሀገሬ በአጎት ሀገር ከራየን ወንዝ ዳር ደክሞኝ እንዳደርኩ ነው ያለሁት። ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ የዘመዴ ሚዲያን በቅርቡ ዕውን ይሆን ዘንድ እና በአየርም ላይ ይገለጥ ዘንድ ስል ተፍተፍ በትበት ማለት ስለነበረብኝ እዚሁ አውሮጳ ጀረምን ልቆይ ብዬ በመወሰኔ ወደ ጮቄ ተራራ ለመመለስ አልተቻለኝም። ዛሬ ምሽት እመለሳለሁ። ዳመና እየጋለብኩ ነው የምመለሰው። ነገር ግን ከጮቄ ተራራ የቀሩት ወፎቼ ከጎጃም ዐማራ ፋኖ ወፎቼ ጋር እየተናበበ በየሰከንዱ መረጃ መለዋወጣችንን አላቆምንም። ግኑኝነታችንም አልተቋረጠምም። በመንፈስ እዚያው እዚያው ጮቄ ነኝ። ጎጃም ጮቄ ተራራ።
"…ክፉ ጎረቤት ዕቃ ያስገዛል እንዲሉ እኔንም ክፉዎቹ ጠበቃ አስረስ መዓረይና አቶ ግርማ ካሣ በፈጠሩት ያልተቀደሰ ጋብቻ ምክንያት ከምወደውና ስንት ከሆንኩለት ከመረጃ ቴቪ ላይ ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር የተሰኘውን መርሀ ግብሬን ለጊዜው አቋርጬ በመውጣት በቲክቶክ እና በቴሌግራም ገጼ ብቻ ተወስኜ እቀር መስሏቸው የሸረቡት ሴራ ጭራሽ ሌላ ዕቃ አስገዝቶኝ አረፈው። እኔም በሳታላይት እስክመጣ የዘወትር ተግባሬን ሳላቋርጥ በትጋት በቴሌግራምና በቲክቶክ ቀጥያለሁ። እንዲያውም ከበፊቱ ይልቅ ብሶብኝ ነው ያረፍኩት። ቀላል ጨመርኩኝ እንዴ? ከፍ ብዬም ነው እየበረርኩ ያለሁት። እነ አስረስ እና ግርማ ካሳ ዘመዴ ከሳታላይት እይታ እንደምንም ከወረደ እኛ በምድር ላይ ለምንሸርበው ዐማራን የመቅበር ሴራ እንቅፋት አይሆንብንም። በቲክቶክና በቴሌግራም የሚለፈልፈውና የሚሞነጫጭረውም መሬት ላይ እንደ ሳታላይት ቴቪው ተደራሽ አይሆንም። ስለዚህ እንደምንም ከሳታላይት ቴቪው ይውረድልን ባሉት መሠረት እኔም የቀረበልኝን በሳታላይቱ ላይ የመቆየትና የመውረድ ሁለት ምርጫ "የመውረዱን ምርጫ" አክብቤ ክብሬን እንደጠበቅኩ ክፉ ደጉን ከማንም ሳልነጋገር ሹልክ ብዬ ወርጃለሁ። ለጊዜው ኦሮምቲቲው ግርማ እና አስረስ መዓረይ ጮቤ ቢረግጡም ክፉ ጎረቤት ሆነው የሌለ ዕቃ ነው ያስገዙኝ። እኔ ዘመዴን ያለማወቃቸው ነው የጎዳቸው። የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር የምለው ለፉገራ፣ ለፉተታ የሚመስለው መንጋ እኮ ለጉድ ነው።
"…ላንቃዬ እስኪሰነጠቅ፣ ጉሮሮዬ እስኪደርቅ፣ ልቤ ዝቅ አስኪል ድረስ ላቤ እንደ ውኃ በጀርባዬ ወርዶ መቀመጫዬን እስኪያርሰው፣ ዋና ገብቼ በውኃ ርሼ፣ ዝናብ እንደወቀጠው ሰው በላቤ በስብሼ የመረጃ ሳታላይት የአየር ሰዓት ክፍያ እንዲፈጸም እና ዐማራ ድምፁ በዓለም እንዲሰማ አኩፋዳዬን ይዤ ምንተ ስሟ ለማርያም፣ ስለ እመ አምላክ ብላችሁ፣ ለዐማራ ሕዝብ ብቸኛው ድምጹ የሚሰማበት ሚዲያ ነውና መረጃ ቴቪን እርዱ፣ አግዙ፣ እያልኩ የመረጃ ቴቪ አየር ላይ እንዲቆይ ከሌሎች በበለጠ መልኩ እንደ ብራቅ እየጮህኩ መክረሜን አስረስ መዓረይና ግርማ ካሣ ለምን እንደሆነ፣ ለምን እንደዚያ እንደማደርግ ግን አልገባቸውም። አልተረዱትምም። የራሴን ወንድሞች፣ አባቶች፣ እህቶችና ቤተሰቦች መረጃ ቴቪ አየር ላይ እንዲቆይ፣ ለዐማራ ድምጽ እንዲሆን እየደወተወትኩ ስለምን እንደነበር አይረዱም፣ ወይም ቢረዱም ለማመን አልፈለጉም። ስለዚህ ግርማ ካሣና አስረስ መዓረይ ሳንካ በመፍጠር እኔን ከመረጃ ቴቪ የምርቅበትን መንገድና ሁናቴ በመፍጠር የተሳካላቸው መስሏቸው ከነ ሰጥ አርጌና ከእነ አልማዝ ባለጭራዋ ጋር ሆነው አሽካኩ፣ አሽኮለኮሉ።
"…አብዛኛው በሚባል መልኩ ብዙ ሰው ለጥቅም፣ ለገንዘብ፣ ለሆዱ ብሎ በሚገረድበት በዚህ በአሁኑ ዓለም እኔም መረጃ ቴቪ ላይ እንደዛ የምጮኸው ለሆዴ፣ ለከርሴ የሚመስለው ነፍ ሰው ነበር። ከዓይንህ ላይ አዋራ እፍ ብሎ ለማውጣት፣ የጠፋህን መንገድ አቅጣጫ ስለጠየቅከው ብር ስጠኝ፣ ገንዘብ ክፈለኝ፣ የላቤን ዋጋ አምጣ ብሎ ግብግብ በሚፈጥርበት በዚህ ዘመን በሳምንት አንድ ቀን በዕለተ እሁድ አራት እና አምስት ሰዓት ሙሉ በላብ ተጠምቄ፣ ጉሮሮዬ እየደረቀ፣ በኩባያ ውኃ እየጠጣሁ እንደዚያ ዋይ ዋይ ስል ለሚያየኝ መንጋ ሚልዮን ዶላር እየተከፈለኝ እንዲህ የማንቋርር እንጂ እንዲህማ በጤናው፣ በብላሽ ያለምንም ክፍያ፣ ያለ ቁጢ በነፃ አይቀውጠውም የሚሉ ቢኖሩም እኔ በበኩሌ አልፈርድባቸውም። በድፍረት የምናገረው ግን እኔ ዘመዴ የዐማራ ድምጹ እንዲሰማ ከመፈለጌ የተነሣ ብቻ እንጂ ሌላ ቤሳቤስቲን ክፍያ የለውም። የምኮራውም ለዚህ ነው። እኔ በዚህ ዘመን ዐማራ ነኝ ከሚሉት አሞሮች የበለጠ በነፃ በብላሽ ለዐማራ ድምፅ በመሆኔ የሌለ ኩራት ነው የሚሰማኝ። ያለ ምንም ምድራዊ ጥቅም በመቆሜ የህሊና እረፍት፣ የውስጥ ሰላም ነው የሚሰማኝ። ሃላስ።
"…እኔ መረጃ ቴቪ ላይ ሆኜ እየለመንኩ እኮ ስኳድ በለጠ ካሣ እዚያው እኔ ለምኜ ባቆምኩት ቤት ላይ ዐማራን የሚያፈርስ፣ ስኳድን የሚያነግሥ ፕሮግራም ይሠራበታል። ሀገር ቤት ካለ ዲኤምሲ ከሚባል ሪል እስቴት ማስታወቂያ ተቀብሎ ዶላሩን እየሞዠለቀ ወደ ኪሱ እያስገባ አሱ ግን የብልፅግና ተቃዋሚ መስሎ በመረጃ ቴቪ ላይ በነፃነት ይገማሸራል። ሌሎችም እንደዚሁ። የመረጃ ቴቪ ፕላት ፎርሙ የማንንም የመናገር ነፃነት ስለማይገድብና ስለሚፈቅድ እኔ ዘመዴ ተቃውሞ የለኝም። ሊኖረኝም አይችልም። ይሄን ግርማ ካሣና አስረስ መዓረይም አሳምረው ያውቁታል። ዘመዴን በቦሌም በባሌም ከመረጃ ቴቪ ማስወረዱ እንጂ የታያቸው የእኔ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ለሁለቱ ሾተላዮች በፍጹም አልታያቸውም። ግርማ ካሣ በጀርባ የሚጨቀጭቀኝን ጭቅጨቃ አንድም ቀን ለሌሎቹ የጋራ ወዳጆቻችን ነግሬም አላውቅም። ረጅም ጊዜ አብረው የኖሩ ወዳጆች መሆናቸውን ስለማውቅ ጊዜው ሲደርስ በራሱ መንገድ ይገለጣል በማለት ተንፍሼውም አላውቅ። የተነፈስኩትም ግርማ ካሳና አስረስ መዓረይ የአሸናፊነት ስሜት ተሰምቷቸው በአደባባይ ሲንበጫበጩ ባየሁ ግዜ ነው።
"…ወዲያው ነበር ግርማ ካሣ መረጃ ቴቪ ላይ ወጥቶ ለእኔ በሚገባኝ መልኩ በአሸናፊነት ስሜት የማልደራደርባቸውን "ከእንግዲህ የፋኖ መሪዎችን መንካት፣ መተቸት አይቻልም" የሚል ሕግ አስረስ መዓረይ ሰጥቶት ሲያነብ ሳየው ዳግም ወደ መረጃ ቴቪ የመመለሴ ጉዳይ እንዳከተመለት ሳውቅ ለምን ሌላ መንገድ፣ ሌላ አማራጭ አንመለከትም በማለት ከዚህ በፊት ጀምረነው ወዳቋረጥነው ወደ ዘመዴ ሚዲያ ሓሳብ የተመለስነው። የመጀመሪያው ጸሎት በአባቶች ማስያዝ ነው። ከአባቶች አረንጓዴ መብራት መብራቱ ሲነገረኝ በቀጥታ ወደ ሥራ ነው የገባነው። ጥቂት ወዳጆቼን አማከርኩ። እነርሱም ሰሙኝ ቆሞ የነበረው የዘመዴ ሚዲያ እንዲንቀሳቀስ ተደረገ። ወዲያውም አለቀ። እግዚአብሔር ይመስገን። ደግሞ ደጋግሞ አሁንም ትናንትም፣ ነገ ከነገ ወዲያም እስከ ዘላለሙ ድረስ እግዚአብሔር ይመስገን። የአባቶቻችን አምላክ፣ የአብርሃም፣ የይስሐቅ የያዕቆብ አምላክ ስሙ የተባረከ ይሁን። አሜን።
"…በዚህ ዘመን የትኛውም ተቋም ሲመሠረት ታማኝ የሆኑ ሰዎችና ገንዘብ እጅግ አስፈላጊ ናቸው። ታማኝ የሆኑ ባለሙያ፣ ዐዋቂ ሰዎች አግኝተህ ሥራውን ለመሥራት ግን ገንዘብ ከሌለህ አባዬ ፈቅ ማለት አትችልም። ስለዚህ ብዙዎች ይሄን ችግር ለመፍታት በብዙ ይደክማሉ። አንዳንዴም ገንዘቡን ለማግኘት ሲሉ የማይፈልጉትን ለመፈጸም ይገደዳሉ። ይሄን የምትፈጽምልኝ ከሆነ፣ እገሌን ከአጠገብህ የምታርቀው ከሆነ፣ ስለ እገሌና ስለዚህ ጉዳይ የማትተነፍስ፣ ጭጭ ምጭጭ የምትል ከሆነ ገንዘቡን እሰጥሃለሁ ብለው በሸምቀቆ አስረው፣ በ18 ቁጥር ሚስማር ጠርቅመው ቆለፈው።👇①✍✍✍