"ርእሰ አንቀጽ"
"…አሳዛኝ‼️… በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ቱመት ቀበሌ 23 ሰላማዊ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል። አብዛኞቹ ለቀን እና ለጉልበት ሥራ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ሲሆን የተወሰኑት ደግሞ የአካባቢው ተወላጅ የሆኑ ነጋዴዎች ናቸው። ከቤት ተወስደው በወላጆቻቸው ፊት የተረሸኑ መኖራቸውን ለማወቅ ተችሏል። ይሄ አሰቃቂ ጭፍጨፋ የተፈጸመው የካቲት 6/2017 ዓም በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ነው። 17 የሚሆኑት አስክሬኖች በጅምላና በተናጠል በከተማዋ ነዋሪዎች ተቀብረዋል። ስድስት አስክሬኖች እስከ ምሽት ድረስ ሳይነሱ መንገድ ላይ ወድቀው ይታዩ ነበር ሲሉ የዓይን እማኞች ተናግረዋል። በእሳት የተቃጠሉ አስክሬኖች መመልከታቸውን የዓይን እማኞቹ ጨምረው አስረድተዋል።
"…ይሄ ዜና ትናንት በዐማራ ፔጆች ላይ ያነበብኩትና ያስቀረሁት ዜና ነው። 23 ሰላማዊ ዜጋዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል ነው የሚለው ዜናው። ዜናው ሲሠራ እንኳ እንዴት እንደሚፈሩ ተመልከቱ። ጎንደር ውስጥ የተጨፈጨፉ ዐማሮችን ዐማራ ሞተ ማለት፣ ተገደለ፣ ተጨፈጨፈ ማለት የማን ሥራ ነው? ይህን ዜና የዘገቡት ጋዜጠኞች ወይ ኢዜማ ናቸው። ግንቦት 7 ናቸው። አልያም የእስክንድር ነጋ አሕፋድ፣ የአርበኛ ደረጀ በላይ ጠቅላይ ግዛት ናቸው። አብዛኞቹ ለቀን እና ለጉልበት ሥራ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ሲሆን የተወሰኑት ደግሞ የአካባቢው ተወላጅ የሆኑ ነጋዴዎች ናቸው። ከቤት ተወስደው በወላጆቻቸው ፊት የተረሸኑ መኖራቸውን ለማወቅ ተችሏል፣ በእሳትም ተቃጥለው የሞቱ አሉ ነው የሚለው ዘጋቢው። ይሄ አረመኔያዊ ድርጊት የተፈጸመው የት ነው? ኢትዮጵያ ውስጥ። ማነው የፈጸመው? አገዛዙ። የት ነው የተፈጸመው? ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ቱመት ቀበሌ ውስጥ፣ ስንት ሰዎች ተጨፈጨፉ? 23 ሰላማዊ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል። ነገዳቸው ከወዴት ነው። ኢትዮጵያውያን ናቸው ይልልሃል ዐማራው ራሱ ዜናውን ሲሠራ።
"…ይሄ ነገር የተፈጸመው ኦሮሚያ ውስጥ ኦሮሞ ላይ፣ ትግራይ ውስጥ ትግሬ ላይ ቢፈጸም ራሱ ይሄን ዜና የሚዘግቡት እነ በለጠ ካሣ መኮንን ዜጎች ሞቱ፣ ተጨፈጨፉ አይሉም። ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው ሲጨፈጨፍ ዜጋ የሚሆነው ዐማራው ብቻ ነው። በቁሙ ያጣውን፣ የተነፈገውን የኢትዮጵያዊነት ክብርና መብት የሚያገኘው ከሞተ በኋላ ነው። ዐማራ በፖለቲከኞቹ ዘንድ የለም። ዐማራ መኖሩ የሚታወቀው ሊገድሉት፣ ሊያጸዱት፣ ሊያጠፉት ሲፈልጉ ብቻ ነው። ዐማሮች የት ናቸው? ብለው ይጠይቃሉ። ይገድሉታል፣ ይዘርፉታል፣ ያፈናቅሉታል፣ ከዚያ ዜናው ሲሠራ ዜጎች ሞቱ፣ ተገደሉ፣ ጥቃት ደረሰባቸው፣ ተፈናቀሉ ተብሎ ይሠራል። በሰፈር ጸብ ተጣልተው ጉዳት የደረሰበት አንድ ኦሮሞ ከተጎዳ ግን ዓለሙ ሁሉ ድብልቅልቁ ነው የሚወጣው። በጣም ገራሚ ጉዳይ ነው።
"…ዐማራ አንድ ካልሆነ ሞቱ፣ ጭፍጨፋው፣ ውድመቱ ይቀጥላል። በወለጋ፣ በአሩሲ፣ በባሌና በሀረር፣ በጅማ ይሰማ ይታይ ይፈጸም የነበረው እልቂት ጭፈጨፋ ከደጃፉ ከገባ ቆየ። ከቀዬው ከገባ ቆየ። ከደጁ የደረሰውን ጠላት በሕዝባዊ ንቅናቄ ገትቶ ዓለሙን ሁሉ አስደንግጦ፣ አስገርሞም የነበረውን ሕዝባዊ የትግል ንቅናቄ ተማርን፣ ፊደል ቆጠርን፣ ታዋቂና ዐዋቂ ነን የሚሉ፣ አፈ ጮሌ ባንዳ ነጋዴዎች መጥተው ትግሉን ጠልፈው ሽባ አደረጉት። በሕዝቡ መነሣሣትና መነቃቃት ላይ ቀዝቃዛ ውኃ በረዶ ቸለሱበት። አኮላሹት። ከአገዛዙ ጋር እየተናበቡ፣ እየተመጋገቡ ዐማራን መዐዓት አወረዱበት። እነርሱ አይርባቸው፣ አይጠማቸው፣ አይበርዳቸው ሕዝቡን ግን ፍዳውን አበሉት። መከራውን አረዘሙበት። ያለ አንድነት፣ ያለ ኅብረት እንደማያሸንፉ እያወቁት አንድነቱን በታተኑት። ተስገበገቡ። ተሻሙም። ተንሰፈሰፉ። በዚህ ምክንያት በዐማራ ክልል ወንድ የተባለ፣ ገበሬ ይሁን የቀን ሠራተኛ እንደ እባብ በተገኘበት አናቱን ይቀጠቀጣል። ይጨፈጨፋል። እደግመዋለሁ አንድነቱን የሚያፈርሰውን የአገዛዙን ደላሎች፣ ፋኖ ውስጥ ያሉ ጉዳይ አስፈጻሚዎች ጫፋቸውን አይነካቸውም፣ አጠገባቸውም አይደርስም። እነርሱ ምንም አይሆኑም፣ የሚጎዳው ተራው ምስኪኑ ዐማራው ነው።
"…ፋኖ አንድ ከተማ ይቆጣጠራል። ወዲያው የመንግሥት ሰዎች ናቸው የሚላቸውን በሙሉ ይበቀላል። ይረሽናል፣ ወይም ዘመድና ገንዘብ ያለው ሰው ከሆነ ደግሞ መረሸኑ ቀርቶለት በከባድ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል። ከተማዋን የተቆጣጠሩት ፋኖዎች ወታደራዊ ዲሲፕሊን ስለሌላቸው፣ አብዛኛዎቹም በከምፕ የተጠረነፉም ስላልሆነ፣ በቀጣይ ምን እናድርግ ብለው እቅድ አውጥተው አይንቀሳቀሱም። ለሽ፣ ለጥ ነው የሚሉት። መዋቅር የመሥራት፣ መንግሥት የመሆን ሕልም ያላቸው ሁላ አይመስልም። እንዳይርባቸው፣ እንዳይጠማቸው ብቻ በማሰብ ትኩረት የሚያደርጉትና ለአፍታም የማይዘነጉት የማይረሱትም ነገር ሳንቲም ከማኅበረሰቡ ላይ መሰብሰብ ብቻ ነው። ለዲሽቃ መግዣ፣ ለብሬን መግዣ እያሉ ይሰበስባሉ። ሕዝቡም ያለ የሌለውን አውጥቶ ይሰጣል። ብሬኑም፣ ጥይቱም ይገዛል። ነፃ አውጪዎቹም ተዘልለው ይቀመጣሉ። ከረንቦላ፣ ፑል፣ ጆተኔ ይጫወታሉ። ቢንጎ ቤት ይውላሉ። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁላ ይመለከታሉ። ይጠጣሉ፣ ይሰክራሉ፣ ይማግጣሉም። አርደው ሲበሉ፣ ሲጠጡም ይከርማሉ።
"…ይመሻል፣ ይነጋል። በሆነ ቀን መከላከያ ተብዬው በታጥቦ አይጠሬው ሚሊሻና በፀረ ዐማራው ዐድማ ብተና እየተመራ ወደዚያ በፋኖ ቁጥጥር ስር ወዳለች ወረዳ፣ ወይ ከተማ ያመራል። ገና መከላከያው መምጣቱ እንደተሰማ ከሕዝቡ በፊት እግሬ አውጪኝ ብሎ የሚፈረጥጠው ይሄው ኮሮምቦላ ሲጫወት የከረመው ኃይል ነው። በሕዝቡ ገንዘብ ከመከላከያ ላይ የተገዛው ብሬን ዲሽቃም አብሮ ይሰደዳል። እንደ አርበኛ ዘመነ ካሴ አይነቶቹ የጦር መሪዎች ደግሞ መከላከያ ጠላት ሲመጣባችሁ አትተኩሱበት፣ ሩጡ፣ ሽሹ ብለው መመሪያ ስላወረዱ እንኳንም ዘንቦብሽ እንዲሁም ጤዛ ተሆነው ዓላማ የሌለው ፀረ ዐማራ ፋኖ ቀነኒሳን፣ ሁሴን ቦልትን አስንቆ ይፈረጥጣል። በዚህ መሃል ኧረ እንዋጋቸው፣ እንደምስሳቸው፣ በጣም ቀላል እኮ ናቸው የሚል ሓሳብ የሚያነሣ ደፋር የዐማራ ፋኖ ካለ አለቀለት። ወይ ይገደላል፣ አልያም በከባድ ጥቁር መዝገብ ውስጥ ስሙ ይሰፍራል። ነገርየው እንዲህ ነው እየሆነ ያለው።…👇 ① ✍✍✍