👆② ✍✍✍ …
"…ከዚያ በተራው መከላከያ በሚኒሻና በዐድማ ብተናው እየተመራ ፋኖዎቹ በቁጥጥራቸው ስር አድርገው ባቆዩአት ከተማ፣ ወይ ወረዳ ይገባል። ሰተት ብሎ ነው የሚገባው። ከዚያ በፊት ግን በዐማራ አክቲቪስቶች ሰበር ዜና ይሠራል። የዐማራ ፋኖ በእንትን እዚህና እዚህ ቦታ እየተናነቀ፣ የጁላን ሠራዊት እየደመሰሰ ነው። ሆስፒታሎች በቁስለኛ ተሞልተዋል፣ አሸባሪው አገዛዝ ገሚሱ ፈርጥጦ የተቀረው ሬሳውን በዚህን ያህል መኪኖች ጭኖ ተመልሷል የሚል ዜና ይለቃሉ። ማኅበራዊ ሚዲያው ይጥለቀለቃል። እውነታው ግን እሱ አይደለም። የአገዛዙ ጥምር ኃይሎች ከተማውን ይቆጣጠራሉ። ከዚያስ? ከዚያማ በተራቸው የበቀል ዱላ ማሳራፍ ይጀምራሉ። ፋኖዎቹ በከተማዋ ውስጥ በነበሩ ጊዜ ከፋኖዎቹ ጋር ጤናማ ግኑኝነት የነበራቸው በሙሉ አለቀላቸው። ተለቅመው ተራ በተራ ይረሸናሉ። ይጨፈጨፋሉ። ልክ እንደ ፋኖዎቹ መከላከያውም ገንዘብ ስብሰባ ይጀምራል። እምቢ፣ የለኝም ያለውን አንተማ ፋኖ ነህ፣ የፋኖ አደራጅ ነህ ተብሎ ይገደላል። ወይ ሀብት ንብረቱን ይወረሳል። እነዚያ የዝንጀሮ ባል ከምን አያስጥሌዎች ለዚህኛው አረመኔ አሳልፈው ሰጥተውት ለመከራ ዳርገውት እነሱ ሌላ ከተማ ሰፍረው ተመሳሳይ ሥራና ተግባር ይፈጽማሉ። ተመልከቱ ምስኪኑ ዐማራ፣ ንፁሑ ሕዝብ በፋኖም፣ በአገዛዙ ጥምር ኃይሎችም በየተራ ይደቅቃሉ። በፋኖ የአስተዳደር ሳምንት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች መከላከያ ሲመጣ ዋነኛው ተበቃይ ሆነው ይገኛሉ። መከላከያው ሲወጣ ደግሞ በመከላከያ ተጎድተው የነበሩ ዐማሮች በተራቸው ከፋኖው ጊዜአዊ አስተዳደር ጋር ሆነው ቂምበቀላቸውን ይወጣሉ። በመሃል ዐማራ ርስ በርሱ ተፋጀ፣ አለቀ።
"…ለዚህ መፍትሄው ምንድነው ያልን እንደሆነ መጀመሪያው አንድነት ነው። ከዚያስ? ከዚያማ ወታደራዊ ዲሲፕሊን። ወታደራዊ ሥልጠና ነው። እንደ አስረስ መዓረይ ክላሽ ይዞ ፎቶ እየተነሡ የዐማራን አንድነት ጀግና ጀግና እየተጫወቱ አፈር ከደቼ ማብላት ሳይሆን ለዚህ ከከተማ፣ ከትምህርት ቤት ግርር ብሎ ጫካ ለገባ ወጣት ልክ እንደ ሳሚ ባለድል ፋኖዎች ነገ ሀገርን እንደሚረከቡ አምነው እውነተኛ የወታደር ባህሪን መላበስ ነው ያለባቸው። ከጎጃም ከእነ አስረስ፣ ከሸዋ ከእነ መከታው፣ ከወሎ ከእነ ሙሀባው፣ ሲሳይ ሳተናው፣ ከጎንደር ከእነ ጌታ አስራደ በቀር ቲክቶክ ላይ ተጥዶ፣ ትዊተር ስፔስ ተጥዶ፣ ዩቲዩብና ፌስቡክ ላይ ተጥዶ የሚውል የፋኖ አደረጃጀት ሰምታችኋል? አይታችኋል? ድሮን እንደማይመታቸው፣ በአይፒ አድሬሳቸው ጥቃት እንደማይደርስባቸው ዐውቀው ከመሳይ መኮንን፣ ከሞገስ ኦሮምቲቲ፣ ከወያኔ አፈቀላጤዎቹ ጋዜጠኞች ጋር አፍ ሲካፈቱ የሚውሉ ሌሎች አደረጃጀቶች መኖራቸውን አላውቅም። ባርች የእስክንድርና የመከታው፣ እነ ማርሸት ከአዝማሪዋ ጋር፣ ሌሎችም እንዲሁ ነው የሚታዩት። ጭራሽ ከሞጣ ጋር ጌም ሁላ ይጫወታሉ። ታብታብ አድርጉኝም ብለው ይማጸናሉ። የቁስ ሰቀቀናቸው ያልለቀቃቸው፣ የዐማራ ፋኖ ትግል ሳይገባቸው ጫካ የገቡትን እነዚህን ይዘህ አታሸንፍም። ለዚህ ሁሉ መፍትሄው ወታደራዊ ዲሲፒሊን ይኑር። ጓደኞቻቸው ክላሽ ይዘው ፎቶ ስለተነሡ ያንን ዓይቶ እኔም እንደነሱ ልሁን ብሎ ለሾው ጫካ የገባው ሁሉ በአስቸኳይ ይጠርነፍ። ያለበለዚያ መከራ ሰቆቃው ይቀጥላል።
"…እኔ እንደዚህ ብዬ የምጽፈው እውነት ለዚህ ለፌስቡክ አርበኛ፣ ለአስመሳይ፣ ቀጣፊ፣ ሂሊኮፍተር በድንጋይ መትቼ ጣልኩ ለሚል ቀጣፊ አልመቸውም። ይሄ በፋኖ ስም ፋኖነትን መጦሪያው፣ እንጀራው ላደረገው አውርቶ አደር አልመችም። ይሄ ሳይተኩስ ወሬ፣ ሳይገድል ጎፈሬውን አሳምሮ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ለሚጎሻመረው አስመሳይ አልመችም። ጦርነቱ ካለቀ ምን በልቼ አድራለሁ፣ አሁን ቶሎ ቶሎ ልዝረፍ ብሎ ለዘረፋ የገባ ይሄን የእኔን ሲያነብ አይመቸውም። በሃሰት ዜና፣ በሕዝብ ሰቆቃና መከራ ላይክና ሼር የሚሰበስብ፣ ሳንቲም የሚለቃቅም ሆድአደር የእኔ መራር እውነት አይመቸውም። ይጠንነዋል። ያንጎፋልለዋል። ይጎፈንነዋል። በጭራሽ እኔ አልመቸውም። ለፋኖ የተላከ ብር ኡጋንዳ በዶላር፣ ወደ ካናዳና ወደ አሜሪካ ጭምር ለሚያሸሽ ወንበዴ የወንበዴ ልጅ የእኔ ጦማር አይመቸውም። ተመቸው አልተመቸው ግን እውነቱ ይሄው ነው። በወሬ የለም ፍሬ። ትታያለህ፣ ትመዘናለህ፣ ከዚያ ቀለህ ስትገኝ ትዋረዳታለህ። አለቀ።
"…ከመሬት የምሰማውን ደግሞ ልጻፍላችሁ። "…ዘመዴ እውነት ለመናገር አንተ ጎጃምን ከጎበኘህ በኋላ በጎጃም ፋኖዎች ላይ መሻሻል ታይቷል። አሁን ፋኖ ሲያሻሽል የድሮ ጥጋቡ የተመለሰበት ብአዴን ነው። ለምሳሌ እኔ ሰምኑን ሥራዬ ብዬ የጎጃምን መስመር ለማየት ከባሕር ዳር መሸንቲ፣ መርአዊ፣ ቢኮሎ፣ ዱርቤቴ፣ ዳንግላ አዲስ ቅዳም፣ ኮሶበር፣ ከሳ፣ ቲሊሊ፣ ቡሬ፣ ማንኩሳ፣ ፍኖተ ሰላም ድረስ በመኪና ሂጃለሁ። ከባሕር ዳር ፍኖተ ሰላም እስክንደርስ ድረስ በመሀል ያሉትን ከተሞች እንድታውቃቸውና የት ላይ ችግር እንዳለ ላስረዳህ ፈልጌ ነው። እናም እኔ ባየሁት መሠረት ከዚህ ቀደም ከባህር ዳር ደጀን ድረስ ፋኖ የማይቀርጥበት ቦታ አልነበረም። አሁን ግን ከባሕር ዳር ፍኖተ ሰላም እስክገባ ድረስ የፋኖ ቀረጥ የለም። ቆሟል። አሁን በምትኩ ሕዝብን ከወረዳ እስከ ከተማ ድረስ ምርርርርር ያደረጉት እጥፍ እጥፍ ውሻ ሆነው ተደራጅተው የተነሡት በየዞንና ወረዳ ከተምችና የገጠር ቀበሌዎች ድረስ የብአዴን ካድሬዎች፣ ሚሊሻና አድማ ብተናውን ይዘው የማያስከፍሉትን ጠይቀኝ። ለድሀ ድሀ እርዳታ፣ ለጤና መድን፣ ለምናምን የማይጠይቁት ገንዘብ የለም። የለኝም ያለ ነጋዴ ከኮንቴነር እስከ ጉልት ገበያ ያለ ቀጥል ወደ መከላከያ ካምፕ ነው ሚባል። ይታሰራል። አፍንጫውን ተይዞ ተገዶም ይከፍላታል። በምትኩ ግን በመንገድ ላይ ባሉ ኬላዎች ላይ በሙሉ ፋኖ መቅረጥ አቁሟል።
"… አሁን በምትኩ ሹፌሮችን የመንግሥት ገቢዎች ደረሰኝ ይዘው ከከተማ መውጫና መግቢያ ላይ ያስከፍሏቸዋል። ከከተማ ወጣ እንዳሉ ከዚህ ቀደም ፋኖ ይቀርጥባቸው ከነበሩበት ኬላዎች ላይ ሚኒሻ ያስከፍላል። ለሚኒሻ ከፍለህ እንዳለፍህ መከላከያው ያስከፍልሃል። ለመላከያ ከፍለህ 10 ሜትር ሳትጓዝ አድማ ብተና አስቁሞ ያስከፍልሀል። ጉድ ጉድ ነው የምትለው። በዚህ ደረጃ ሹፌርን ማማረር በቃ ሹፌር ኧረ ብር ጨርሻለሁ ከዚህ እስከዚህ ከፍዬ ካለ ምን አባክ ውረድ። ይሄኔ ፋኖ ቢጠይቅህ ሳትከራከር በሞባይል ባንኪንግ አስልከህ ትከፍል ነበር። በማለት ሹፌሮችን የመንግሥት ኃይሎች ካድሬ ሚሊሻ አድማ ብተናና መከላከያ ተናበው አሳራቸውን እያበሏቸው ነው። የጎጃም ፋኖ እማ እኔ እንዳዬሁት በዚህኛው ከባሕር ዳር መርአዊ ዳንግላ ቡሬ ፍኖተ ሠላም ድረስ መመሪያ ተላልፏል። አንድም ፋኖ መንገድ ላይ ኬላ ዘርግቶ ቁሞ እንዳይቀርጥ ተብሎ ተወስኗል ብለው አሁን አይቀርጡም። በዚህ ትችትህን ሰምተው የጎጃምን ፋኖ አማራሪ ቀረጥን በማስቀረቱ አንተም በሚዲያ ልታመሰግናቸው ይገባል። ይሄን የምነግርህ ዘመዴ በዓይኔ ስላየሁ ነው ያሉኝ ወዳጄ ናቸው።…👇 ② ✍✍✍