ከወጋችን በፊት…6 ሰው ይፈለጋል።
"…ዘመዴ ሚዲያ ለሚፈልጋቸው 300 ሠራዊተ ጌዴዎን ዘ-ኢትዮጵያ መሥራች አባላት ምልመላ ጥሪ አድርጎ ነበር። በተደረገው ጥሪ መሠረትም 300 ሠራዊተ ጌዴዎን በሰዓታት ውስጥ በፍጥነት ተመዝግበዋል። በዚህ መሃል ግን ከ300ው በተጨማሪ 12 ሰዎች ቁጥራቸው ከ300 ው ሠራዊት ሆኖ በትርፍ በተጠባባቂ ተመዝግበውም ነበር። ነገር ግን ይህን ያዩ ንስር ዓይኖች "…ዘመዴ 312 ሠራዊተ ጌዴዎን ከምትሆኑ ሦስት መቶው እንዳለ ሁኖ አሥራ ሁለቱ ላይ ስድስት ጨምራችሁ 318 ብትሆኑ በብዙ ነገር ምስጢር ይገጥማል።" የሚል ሃሳብ አቀረቡ። እኔም ሓሳቡን ገዛሁት።
"…ስለዚህ 300 ሠራዊተ ጌዴዎን ቢሉ ወይም ሠለስቱ ምዕት ለ318ቱ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን መታሰቢያቸው ይሆናል ማለት ነው።" ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።" ማቴ 18፥20። ለ318ቱ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ዘመን በኒቂያ ለመሰብሰባቸው ዋነኛው ምክንያት የአርዮስ የክህደት ትምህርት ነበር። በመጀመሪያ ደጋግመው በቃል መከሩት፣ አስተማሩት እምቢ ብሎ በክህደቱ ሲጸና አልመለስም ሲል ጉባኤ ሠርተው አወገዙት። ለዩት።
"…ኋላም ሠለስቱ ምዕት ከጉባኤ ኒቂያ በኋላ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን በሚገባ አደራጁ። ጸሎተ ሃይማኖትን ለመንግሥቱም ፍፃሜ የለውም እስከሚለው ድረስ ጽፈው ዐወጁ። በስማቸው የሚጠራም ሥርዓተ ቅዳሴ አዘጋጁ። እንዲያው በየሰበባ አስባቡ፣ በየምክንያቱ የቀደሙ አባቶችን እናስታውስ፣ እነዘክራቸው ብዬ እንጂ የእኛ ስብስብ እንደ ኒቅያ ጉባኤ አባቶች ያለ ስብስብ ነው ማለት አይደለም። አይሆንምም። በረከታቸው እንዲያድርብን ግን ሠለስቱ ምዕትን ከሠራዊተ ጌዴዎን ጋር ብናስታውስ ምን ይለናል? ምንም። በሉ 6 ሰዎች አለሁ በሉን። ሠራዊቱንም ተቀላቀሉ።
• ፍጠኑ።