ሐሙስ፦ አዳም ሐሙስ ይባላል፦
"…ከጌታ ትንሣኤ በኋላ በአምስተኛው ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አባታችን አዳም እና እናታችን ሔዋን ከትንሣኤው ጋር ተያይዞ ታስበው ይውሉ ዘንድ አዳም ወር በገባ በ6 ከኢየሱስ እና ከእነ ቅድስት አርሴማ ጋር አብሮ የሚከበር የወርሀዊ በዓል ሥርዓት የተሠራለት ቢሆንም የዛሬው ግን አባታችን አዳም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ፣ በሜዳህ ድኼ፣ በእንጨት ላይ ተሰቅዬ ከ5 ቀን ተኩል በኋላ አድንህሃለሁ ተብሎ የተሰጠው ተስፋና የተገባለት ቃል ኪዳን ተፈጽሞ አዳምና ልጆቹ ነጻ የወጣበትን አስበን የምንውልበት ዕለት ነው።
"…አባታችን አዳም በሦስት ነገር ወደቀ። በተዋሕዶ፣ በመብልና በእጽ ምክንያት ወደቀ። ሰይጣን ከቆንጆዋ እባብ ተዋሕዶ፣ እባብን መስሎ፣ እባብንም አሕሎ አዳምና ሔዋንን ሰብኮ፣ ጌታ እግዚአብሔር እንዳትበሉት፣ የበላችሁ ቀን የሞት ሞትን ትሞታላችሁ ብሎ የከለከላቸውን ዕጽ በልተው ሞቱ። በዚህ ምክንያት የሞቱትን አዳምና ሔዋንን ለማዳን እግዚአብሔር ወልድ ወደዚህ ምድር መጣ።
"…ሰይጣን በእባብ ገላ ተዋሕዶ እንዳዋረደው፣ ጌታም ከአዳም የልጅ ልጅ ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆኖ በተዋሕዶ ተገልጦ አዳነው። አዳም በዕፅ ምክንያት እንደ ሞተ የሚያውቅ ጌታም በዕለተ አርብ በ17 ክንድ ዕፀ መስቀል ላይ ተሰቅሎ አዳነው። በመብል ምክንያት የጠፋውን አዳም "ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ… ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ። ዮሐ፥ 6፥ 54-56 በማለት በመብል ምክንያት የጠፋውን አዳምን የራሱን ሥጋና ደም መብልና መጠት አድርጎ አደነው።
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግአዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሐ ወሰላም።