ሀማስ ሁሉንም ታጋቾች መልቀቅ አለበት !
NBC Ethiopia
። ። ። ። ። ። ። ። ።
የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ሙሀመድ አባስ፣ ሀማስ ሁሉንም የእስራኤል ታጋቾች በፍጥነት መፍታ አለበት ማለታቸው ተገለጸ፡፡
በጋዛ ያለውን ቀውስ ያባባሳው እና እስራኤል የተጠናከረ ጥቃት እያደረሰች ያለው ሀማስ አግቶ በያዛቸው ሰዎች ምክንያት ስለሆነ አሁኑኑ ታጋቾችን መልቀቅ እንዳለበት ሙሀመድ አባስ ጥሪያቸውን አሰምተዋል፡፡
አባስ በራማላህ በነበራቸው ስብሰባ "እኔም ህዝቤም ዋጋ እየከፈልን መቀጠል የለብንም" ሲሉም ተደምጠዋል፡፡ አክለውም በየቀኑ ሞት ማስተናገድ ሰልችቶናል፤ በጋዛ ያለውን ህዝብ ሰላም ለመጠበቅ ሀማስ ቀሪ ታጋቾችን መልቀቅ አለበት ብለዋል፡፡
እንናተ ማትረቡ ከጋዛ ህዝብ ላይ እጃችሁን አንሱ በማለት ሀማስን መዝለፋቸውም ታውቋል፡፡
የሀማስ ከፍተኛ መሪ ባሲም ናኢም በበኩሉ፤ የአባስ ዘለፋን በማውገዝ ተቀባይነት የሌለው ሲል አጣጥሎታል፡፡
ቢቢሲ፤ ገልፍ ቶዴይ እና ሮይተርስ ዘግበውታል፡፡
@zenaadis_ethiopia