ዓባይ ባንክ ከፌደራል የስነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለባንኩ አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በኢንተር ላግዠሪ ሆቴል አካሄዷል፡፡
በስልጠናው መክፈቻ ላይ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠ እንደተናገሩት፣ ስልጠናው ሰራተኞች በስነ-ምግባር ታንፀው ሙያዊ የሥራ ዲሲፒሊን በመላበስ የማገልገል ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የማድረግ ዓላማን እንዳነገበ አመላክተዋል፡፡
ለሁለት ቀናት የሚሰጠው ስለጠና “ሥነ ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት” በሚል መሪ ሐሣብ የተዘጋጀ ነው፡፡
ባንኩ በቀጣይም ለመላው ሠራተኞቹ ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ስልጠናዎች፣ ውይይቶችና የምክክር መድረኮች ከኮሚሽኑ ጋር በመተባበር ተደራሽ እንደሚያደርግ ተጠቁሟል፡፡