Abrham2319


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Другое


O God, bless my youth and make me what I need, not what I want
@Abrham2319 ️©️
Telegram Channel https://t.me/abrham2319
Telegram Group https://t.me/abrham2319_Group
TikTok Channel https://www.tiktok.com/@abrham2319

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Другое
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: Abrham2319
🙏🙏🙏 ሕማማት🙏🙏🙏

ዕለተ #ዐርብ
ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ «አውቀውስ ቢሆን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት» /1ቆሮ.1-18/፡፡ እንዳለ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለበደል ያለጥፋት ንጹሕና ጻድቅ የሆነውን ጌታ የሰቀሉበት ዕለት ነው፡፡

On Telegram👇
         • https://t.me/abrham2319
         • https://t.me/abrham2319
Share 🙏


Репост из: Abrham2319
#አክፍሎት

«አክፍሎት፦ ዓርብና ቅዳሜን ሁለቱን አንድ አድርጋችሁ ጹሟቸው። ሁለቱን መጾም ያልቻለ ቀዳሚትን ብቻ ይጹም።» — ፍትሐ ነገስት አንቀጽ 15

👉 ዓርብና ቅዳሜ ይሆናል፤ ያልቻለ አንድ ቅዳሜን ያከፍላል። የዚህ አክፍሎት ጾም የተጀመረው በሐዋርያት ነው፡፡ ጌታ በመዋዕለ ትምህርቱ ሳለ ፈሪሳውያን፦ “እኛና የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት እንጾማለን፤ የአንተ ደቀ መዛሙርት የማይጾሙት ለምንድን ነው?” ብለው ጠይቀውት ነበር። እርሱም፦ “ሙሽራ ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎች ሊጦሙ አይገባም። ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣልና ያን ጊዜ ይጾማሉ” ብሎ መለሰላቸው።

በዚህ መሠረት ሐዋርያት ሙሽራው ክርስቶስ ከእነርሱ ከተለየበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ትንሣኤው ድረስ ከሰው ርቀው፣ ከእህል ከውኃ ተለይተው፣ በዝግ ቤት ተወስነው ጹመዋል። ካህናትና ምእመናን የሐዋርያትን ፈለግ በመከተል ሐሙስ ማታ ከበሉ በኋላ እስከ ትንሣኤ ሌሊት ይቆያሉ። ሁለቱን ቀን ያልቻሉ ግን ቅዳሜን ብቻ ያከፍላሉ፡፡

👉 በሌላ መልኩ #አክፍሎት ማለት #ማካፈል ማለት ነው። ይኸውም በዚህ ዕለት ካህናት ምእመናን ካመጡላቸው የትንሣኤ መዋያ በረከት ለድሆች ያካፍላሉና ነው።

              #በትንሣኤው_ለትንሣኤ_ያብቃን!
            

@Abrham2319


Репост из: Abrham2319


Репост из: Abrham2319
የጉልባን ታሪክ
💦💦💦💦
ጉልባን ከባቄላ ክክ ከሰንዴ ወይም ከተፈተገ ገብስ እና ከሌሎችም ጥራጥሬዎች ጥሬውን ወይም ከክቶ እንደ ንፍሮ ተቀቅሎ የሚዘጋጅ ምግብ ነው ። የዕለተ ሐሙስ ሥርዓተ ጸሎት ከተፈጸመ በኋላ ምእመናን ወደ ቤታቸው ሄደው ጉልባን ሠርተው ይመገባሉ ። ለዚህም ሁለት ትውፊታዊ መሠረት እንዳሉት ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ያስረዳሉ እንመልከት፦ ፩ የኦሪት ምሳሌ ለመፈጸም እስራኤል ለ215 ዓመታት በግብጻውያን በባርነት ተይዘው በግፍ ተጨቁነው መኖራቸው ይታወቃል የእግዚአብሔር ፍቃድ ሁኖ እግዚአብሔር ሙሴን ፈርኦንን ህዝቤን ልቀቅ ብሎሀል ብለህ ንገረው ብሎት ነበር ። ሙሴም ፈርኦንን እግዚአብሔር ህዝቤን ልቀቅ ብሎሀል አለው ፈርኦንም እስራኤል እለቅ ዘንድ እግዚአብሔር ማነው ? እግዚአብሔርን አላቅም እስራኤንም ደግሞ አለቅም በማለት አሻፈረኝ ብሎ ነበር ። እግዚአብሔርም የኃይል ስራውን በሙሴ አሳየ በመጨረሻም እምቢ ሲል እግዚአብሔር ከእንስሳትም ከሰውም ወገን በመልአክ በሞተ በኩር ግብጽ ተቀሰፈች በዚህም ፈርኦን ደንግጦ ሕዝበ እስራኤል ለመልቀቅ ተገዷል ። በዚህ ጊዜ ህዝቡ ለመውጣት ስለቸኮሉ በቤት ያለውን እህል ያልተፈጨውን ንፍሮ ቀቅለው የተፈጨውን ቂጣ ጋግረው በልተው ነው ጉዞ የጀመሩት ። እስራኤልም ከግብፅ ከወጡ በኋላም የነጻነት በዓላቸውን ሲያከብሩ ያልቦካ ኪጣ ጋግረው ንፍሮ ቀቅለው በግ አርደው ከባርነት በወጡበት ዕለት የነበረውን ሁኔታ ያስቡ ዘንድ ታዘዋል ። (ዘጸ ፲፫ ፥፩) ፋሲካ የሚለውም '' ፓሢሕ '' ከሚለው ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ማለፍ መሻገር ማለት ነው ። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሴተ ሐሙስ በአልዓዛር ቤት ተገኝቶ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ይህን በዓል አክብሯል ። እኛም አሰቀድሞ በሙሴ ላይ አድሮ ሕገ ኦሪትን የሠራ ሕዝቡንም መርቶ ከነዓን ያደረሰው እርሱ ራሱ እግዚአብሔር የሰውን ስጋ ለብሶ ክርስቶስ ተብሎ መገለጡን በማመን ፤ ክርስቶስ ራሱ አዲሱን ሕግ ከመሥራቱ አሰቀድሞ ከደቀመዛሙርቱ ጋር በዓለ ፋሲካን እንዳከበረ ሁሉ እኛም አዲስ ኪዳን ጥላ /ምሳሌ/ የሆነውን ሥርዐት እኛ ጉልባን በመመገብ ለመታሰቢያ እናደርጋለን ።
፪ የኀዘን ሳምንት መሆኑን ለማጠየቅ ፦ እንደ ሀገራችን ባሕል ንፍሮ እንባ አድርቅ ይሉታል ። ብዙ ጊዜም ለለቀስተኞች ይሠራል ። አንድም ሞት ተናግሮ አይመጣምና ሞት በድንገት ሲመጣ ለእንግዳ መሸኛ ቶሎ ሊደርስ የሚችል ምግብ ንፍሮ ስለሆነ በተለይም በገጠራማ አካባቢዎች ለልቅሶ ቤት ንፍሮ የመቀቀል ልማድ አለ ።
➛ በሰሙነ ሕማማት ወቅት ምዕመናን በጌታችን መከራ ፣ ሞት እና በድንግል ማርያም ኀዘን ምክንያት ኀዘንተኞች ስለሆኑ ይህንኑ ለማመልከት ጉልባን ይመገባሉ ። የጉልባን ክርስቲያናዊ ትውፊት ይህንን ይመስላል እኛ ምዕመናን በቤተችን እንዲሰራ በመጠየቅ በመስራት ይህን ትውፊት ማስቀጠል ይኖርብናል ።


Репост из: Abrham2319
ሐዋርያቲሁ ከበበ እግረ አርዳዒሁ ሐጸበ ኮኖሙ አበ ወእመ ወመሐሮሙ ጥበበ
       


Репост из: Abrham2319
                         †                         

🕊    †    ሰሙነ ሕማማት   †    🕊

▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬

[      በእንተ ጸሎት ሐሙስ     ]

" ተራሮችን በኃይሉ የሚያስታጥቃቸው ለማገልገል ማበሻ ጨርቅ ታጠቀ፡፡ የባሕርን ውኃ እንደ አቁማዳ የሚሰበስበው በቀላያትም መዝገቦች የሚሾማቸው ርሱ ከወዳጁ ከአልዓዛር ቤት የውኃ ማድጋ አንሥቶ እግሮችን ለማጠብ ያገለግልባት ዘንድ ወደ  ኩስኩስት አፈሰሰ፡፡ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በሚታጠቡበት ገንዘብ የናስ ኩስኩስት ሠርቶ በደብተራ ኦሪት ደጃፍ እንዲያኖራት ሙሴን ያዘዘው ውኃውን በኩስኩስት ሞልቶ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሊያጥብ ጀመረ፡፡ የተረከዞቻቸውንም እድፍ በታጠቀው ማበሻ ጨርቅ አሸ፡፡" 

[    አባ  ጊዮርጊስ ዘጋስጫ      ]

†                       †                         †

" በወገቡ የታጠቀውን ማድረቂያ አይተው መላእክት አደነቁ ፤ ስሙ ከፀሓይና ከጨረቃ በፊት የነበረ ርሱ አገልጋይ ኾነ ፤ ሕያው ጌታን ሱራፌል ያመሰግኑታል ፤ ቦታውን ግን አያውቁም ፤ ሱራፌልን የፈጠረ ርሱ በራት ጊዜ ወገቡን ዘርፍ ባለው ዝናር ታጠቀ ፤ እንዳያቃጥል በመፍራት የማይታይ እሳት ለሐዋርያት አገልጋይ ኾኖ አብነት ይኾናቸው ዘንድ የትሕትና ሥራን የሚሠራበትን ውሃ በኩስኩስት ቀዳ የደቀ መዛሙርቱን አለቃ ጴጥሮስንም እግሩን ሊያጥበው ጠራው"

[   @abrham2319   ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬


Репост из: Abrham2319
#ዕረቡ

በማቴዎስና በማርቆስ ወንጌል መሠረት በዚህ እለት ሦስት ነገሮች ተደርገዋል።

1. የካህናት አለቆች ጸሀፍትና ፈሪሳውያን በጌታ ላይ ተማክረዋል ሊያስገድሉትም ወስነዋ።
2. ጌታችን በስምኦን ዘለምጽ ቤት ተገኝቶ አንዲት ሴት(ማርያም እንተ ዕፍረት) ዋጋው የከበረ የአልባስጥሮስ ሽቱ ቀብታዋለች።
3. ይሁዳ ጌታን ለመሸጥ ወደ ጸሀፍት ካህናት ጋር በመሄድ ተዋውሏል።

በአይሁድ ዘንድ 72 አባላት የነበሩት ሸንጎ ነበር። "ሲናድርየም " ይባላል።አብዛኛዎቹ ሰዱቃውያን ሲሆኑ ጥቂቶቹ ጸሀፎችና ፈሪሳውያን ነበሩ። የተሰበሰቡትና ጌታን እንዴት እንደሚይዙት የተማከሩት በካህናቱ አለቃ በቀያፋ ግቢ ነበር።

በዚ ጊዜ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ የነበረው ያስቆሮቱ ይሁዳ ወደ ስብሰባው በመሄድ "ምን ትሰጡኛላችሁ እኔ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ" በማለት ጌታን ለመሸጥ ተዋዋለ።ይህን ያደረገው በስምኦን ዘለምጽ ቤት እያሉ አንዲት ሴት ጌታን የከበረ ሽቱ ስትቀባው ለድሀ አዛኝ በመምሰል "ይህ ሽቱ ተሽጦ ለድሆች ቢሰጥ መልካም ነበር "ሲል ጌታ የልቡን መሻት አውቆ ስለተቃወመው አኩርፎ ሄዶ ተዋውሎ በ30 ብር የተስማማ። ከዛም ሊያስገድሉት ወስነዋል። እንዲሁም ሐሙስ በአል ስለነበር በአሉን አክብረው ውለው ማታ ላይ አስይዘው አርብ ጠዋት ሸንጎ ሊያቆሙት ተስማምተው ተለያዩ (ማቴ 26÷3.. ማር 14÷1-11 ሉቃ 22÷1-6)

በዚህ እለት በቤተክርስቲያን የሚሰበከው ምስባክ

- አንድ ሰአት መዝ 83÷5
- ሦስት ሰአት መዝ 41÷6
- ስድስት ሰአት መዝ 41÷5
- ዘጠኝ ሰአት መዝ 83÷2
- አስራ አንድ ሰአት መዝ 6÷2
@abrham2319


Репост из: Abrham2319
ጥያቄዎቹ በቁጥር አምስት ናቸው። እነዚህም:-
   ፩. ሥልጣኑን የተመለከተ ጥያቄ ቀርቦለታል።(ሉቃ፳:፪) ለክፋት የቀረበ ጥያቄ በመሆኑ ጥያቄውን በጥያቄ መልሶታል።
   ፪. በወይን አትክልት መስሎ ጥያቄ አቅርቦላቸዋል። (ሉቃ፳:፱)ይህ ምሳሌ
በቀጥታ ከእነርሱ ጋር እንደሚገናኝ ተረድተውም ነበር።
   ፫. ግብርን የተመለከተ ጥያቄ ቀርቦለታል። (ሉቃ፳:፳፪) ይህንንም በድንቅ ጥበቡ የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ብሎ መልሶላቸዋል።
   ፬. ትንሣኤ ሙታንን የተመለከተ ጥያቄ ቀርቦለታል። (ሉቃ፳:፴፫) ከጋብቻ ጋር
በተገናኘ ምድራዊ አስተሳሰብ ሰማያዊውን ኑሮ አውርደው ለጠየቁት ለሰዱቃውያን ከሞት በኋላ እንደ መላእክት ያለን ኑሮ የመኖር ዕድል እንዳለው የሰው ልጅ መልሶላቸዋል።
   ፭. ክርስቶስን የዳዊት ልጅ ለምን ይሉታል የሚል ጥያቄ አቅርቦላቸዋል።(ሉቃ፳:፵፩)
መልስ ላጡበት ጥያቄ ራሱ በመመለስ እርሱ የዳዊት ጌታ መሆኑን አስተምሯቸዋል።
፪. የትምህርት ቀን ትባላለች
በዚህ ዕለት ደቀ መዛሙርቱን ሰፊ ትምህርትን ስለ መጨረሻው ዘመን ምልክቶች አስተምሯቸዋልና የትምህርት ቀን ተብላ ትጠራለች። (ሉቃ፳:፵፬-፵፯) ያስተማራቸው ትምህርቶች
፩. የአምልኮ መልክ ካላቸውተጠንቀቁ
፪. ታይታን ከሚወዱ ተጠንቀቁ
፫. ለራሳቸው ክብርን ከሚሰጡ ተጠንቀቁ
፬. የባልቴቶችን ገንዘብ ከሚበሉ ተጠንቀቁ
፭. በምክንያት ጸሎት ከሚያረዝሙ ተጠንቀቁ
ሌላው በግብረ ሕማማት ካህናት በዚህች ዕለት ስለሚያከናውኗቸው ስራዎች እንዲህ ተብሎ ተገልጿል:-"ከዚህ በኋላ በከበረች ቤተክርስቲያን ማክሰኞ ከሌሊቱ መጀመሪያው ሰዓት ካህናት ይሰብሰቡ። ተዘከሮ እግዚኦ የሚለውን የዳዊት መዝሙር ወአሰሰልኩ ዕለተ እስከሚለው ድረስ ጸልዩ። ውዳሴ ማርያምም የቀዳሚትን ይድገሙ።" ግብረ ሕማማት (ገጽ፪፻፴፪)
የመዝሙረ ዳዊት ምንባባት
በ፩ ሰዓት (መዝ፴፬:፬-፭)
በ፫ ሰዓት (መዝ፻፲፰:፻፶፬)
በ፮ ሰዓት (መዝ፲፯:፲፯)
በ፱ ሰዓት (መዝ፳፬:፩)
በ፲፩ ሰዓት (መዝ፵፬:፮)


Репост из: Abrham2319
#ማክሰኞ ✞
*  #የጥያቄ_ቀን በመባል ይታወቃል። ምክንያቱም ሹመትን ወይም
ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን
ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተ መቅደስ ምክንያት በዚህ ዕለት ስለ
ስልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና።
* ጥያቄውም ከምድራውያን ነገስታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ
ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታት በማን ስልጣን ታደርጋለህ ? የሚል ነበር . ይህንስ ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ። የዮሐንስ
ጥምቀት ከወዴት ነበረች ? ከሰማይ ወይስ ከሰው ? አላቸው።
እነርሱም ከሰማይ ነው ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም ? ይለናል።
ከሰው ነው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል፤ እንደ
መምህርነቱም ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን ተባብለው ወዴት
እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት። እርሱም በማን ሥልጣን
እነዚህን እንደማደርግ እኔም አልነግራችሁም አላቸው። ይህንንም
መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸውን ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንዲያደርግ
አጥተውት አልነበረም። ልቦናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ ነው
እንጂ። ከዚህ የምንማረው የእነሱን ክፉ ጠባይና ግብር መከተል
እንደማይገባን ነው።
* በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስም ረጅም ትምህርት ስላስተማረ
የትምህርት ቀንም ይባላል። ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን፣ ከፍቅረ
እግዚአብሔር የተለዩትን አስተምሮ ማቅረብ፣ መክሮ መመለስ
እንደሚገባ ሲያስተምር ነው።


Репост из: Abrham2319
#ሰሙነ_ሕማማት ❖

ሰኞ እስከ ቅዳሜ ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት፤ ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሠልስት፣ በስድስት፣ በተሰዓት /ዘጠኝ /ሰዓት፣ በሰርክ /በዐስራ አንድ/ ሰዓት እየመላለሱ የሚሰግዱበትና የሚጸለዩበት ልዩ ሳምንት ነው ከሆሳዕና ማግስት እስከ ትንሳኤ።

በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭ ሺ ፭ መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው። የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም በጽኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው። ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው፦

#ሰኞ ❖
#መርገመ_በለስ_የተፈጸመበት_ሰኞ_ይባላል፦
በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል።

#አንጽሖተ_ቤተ_መቅደስ_ይባላል፡-
ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” ማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና።

#ማክሰኞ ❖
#የጥያቄ_ቀን_ይባላል፦
ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል።

#የትምህርት_ቀን_ይባላል፡-
በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪።

#ረቡዕ ❖
#ምክረ_አይሁድ_ይባላል፦
ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ሉቃ ፳፪፥፩-፮ ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል።

#የመልካም_መዓዛ_ቀንም_ይባላል፡-
ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮-፯ የመዓዛ ቀን ይባላል።

#የእንባ_ቀን_ይባላል፡-
ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል።

#ሐሙስ ❖
#ጸሎተ_ሐሙስ_ይባላል፦
ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል።

#የምስጢር_ቀን_ይባላል፡-
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል።

#የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል፡-
መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።

#የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል፡-
ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል።

#ዓርብ ❖
#የስቅለት_ዓርብ_ይባላል፦
ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል።

#መልካሙ_ዓርብ_ይባላል
ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።

#ቅዳሜ ❖
#ቀዳም_ስዑር_ትባላለች
ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል።

#ለምለም_ቅዳሜ_ይባላል፡-
ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል።

#ቅዱስ_ቅዳሜ_ይባላል
ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል።



#በሰሙነ_ሕማማት_የሚፈጸሙ_ሥርዓቶች

#ስግደት
በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል።

#ጸሎት
በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም
ከጠዋቱ 1 3 6 9 11 ሰዓት እንዲሁም
ከምሽቱ 1 3 6 9 11 ሰዓት ናቸው።

በእነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ

#ጾም
በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት/ አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች አይበሉም። በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ #አንድ_ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም ቆሎ,ዳቦ,ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል

#አለመሳሳም
አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ.3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29

#አክፍሎት
እመቤታችን ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው

#ጉልባን
ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው

#ጥብጠባ
ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው ይህም የጌታ ምሳሌ ነው

#ቄጠማ
ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን።








Репост из: Abrham2319
ደብረ ዘይት የዐብይ ጾም አምስተኛ ሳምንት


ደብረ ዘይት ማለት ቃሉ “ደብር” ሲል ተራራ ሲሆን “ዘይት” ሲል የወይራ ዛፍን ያመለከታል።

ባጠቃላይ ደብረ ዘይት የወይራ ዛፍ (የዘይት ዛፍ) የበዛበት ተራራ ማለት ነው። ቦታው በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ከጎለጎታ (ቀራንዮ) ተራራ በስተምስራቅ በግምት ፪ ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ታላቅ ተራራ ነው።
በሁለቱ ተራሮች መካከል ጌቴሴማኒ የሚባለው ለምለም ስፍራ ይኸውም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የመቃብር ስፍራ ይገኛል።

የደብረ ዘይት ተራራ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ የሚያድርበት፣ የሚያስተምርበት፣ ውሎ የሚያርፍበት ሥፍራ ነው። ሉቃ ፳፩፥ ፴፯፣ ሉቃ ፳፪፥ ፴፱፣ ዮሐ ፰፥ ፩

ከዚሁ ተራራ ላይ ነው ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያረገው። ኋላም በዳግም ምጽአት እዚሁ ተራራ ላይ ነው ለፍርድ የሚመጣው። /ሐዋ ፩፥፲፫/። "
" በዚህ ቀን ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ወደ ምድር ስለመምጣቱ (ዳግም ምፅአቱ ) ይሰበካል።

ይህን ዓለምንም አሳልፎ ለመረጣቸውና ላከበራቸው ዘላለማዊ መንግሥትን ሊያወርሳቸው እንደሚመጣ ይነገርበታል። ይህ ቀንም እኩለ ፆም በመባል የሚታወቅ ሲሆን በዚህች በተለየች ቀንም ሁሉም እንደ የሥራው ፍርዱን ከአምላክ የሚቀበልበት መሆኑ፤ መልካም ላደረጉ መልካም እንደሚመለስላቸ ክፉም ላደረጉ የክፋታቸውን ዋጋ እንደሚያገኙ ይሰበካል።

ጌታም የአባቴ ቡሩካን የተዘጋጀላችሁን የክብር ቦታ ውረሱ በማለት ወዳጆቹን እንደሚጠራ ይነገራል።
" እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም እሳት በፊቱ ይቃጠላል " ማቴ.፳፬፡፩-፴፮ ኢየሱስም ከመቅደስ ወጥቶ ሄደ፥ ደቀ መዛሙርቱም የመቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ቀረቡ።

እርሱ ግን መልሶ፦ ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አላቸው። እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።

ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ። ብዙዎች። እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ። ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።

ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው። በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።

በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤ ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች። እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። "

" እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ ወአምላክነሂ ኢያረምም እሳት ይነድድ ቅድሜሁ "
               መዝ.፵፪÷፱

" እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል፡፡
አምላካችንም ዝም አይልም  እሳት በፊቱ ይነድዳል፣  በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ፡፡ "
https://t.me/abrham2319




Репост из: Abrham2319
​​​​የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት መጻጒዕ

እንኳን አደረሳቹ የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት መጻጒዕ
ለ 38 ዓመት በአልጋ ላይ ተኝቶ የሚኖር አንደ ሰው ነበረ እርሱም #መጾጒዕ ይባላል።

((ዮሐ5፥1-11)) ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነበረ ኢየሱስም ወደ አየሩሳሌም ወጣ በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ "ቤተ ሳይዳ" የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች አምስትም መመላለሻ ነበረባት

በእነዚህ ውስጥ የወኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞችና፣ ዕዉሮች፣ አንካሶችም ሰውነታቸውም የሰለለ በዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር አንደንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና እንግዲህ ከወኃውን መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ የገባ ከማናቸውም ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር።

በዚያም "ሠላሳ ስምንት" ዓመት ያህል ይታመም የነበረ አንድ ሰው ነበረ ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ ልትደን ትወዳላህን? አለው

ድውዮም፦ አዎ ጌታ ሆይ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያው ወስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም! ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳላሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለስለት፣

ኢየሱስም ፦ ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው፣ ወዲያውም ሰውየው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ።

ያም ቀን "ሰንበት" ቀን ነበረ ስለዚህ አይሁድ የተፈወሰውን ሰው "ሰንበት" ነው አልጋውን ልትሸከም አልተፈቀደልህም አሉት እርሱ ግን ያዳነኝ ያ ሰው "አልጋውን ተሸክመህ ሂድ" አለኝ ብሎ መለሰላቸው።

((ማቴ9÷1)) በታንኳም ገብቶ ተሻገረና ወደ ገዛ ከተማው መጣ እነሆም በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ ኢየሱስ እምነታቸውን አይቶ ሽባውን አንተ ልጅ አይዞህ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ አለው

((መዝ 40፥3)) እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳላ ይረዳዋል መኝታውንም ሁሉ ከበሽታው የተነሣ ይለውጥለታል።

አቤቱ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ በየጸበሉ በሆስፒታሉ የታመሙትን ምህረትህን ለሚናፍቁ የምህረት እጅህን ዘርጋላቸው እኛንም የመጣብንን መቅሰፍት በቸርነትህ ያዝልን!

የሐዋሪያት የነብያት የቅዱሳን አበው ጸሎት ልመና የተቀበልክ አምላክ የእኛንም ተቀበል! አሜን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን

#ሼርርርርርርርርርርር
አቅራቢ ፦ አብርሃም ፳፫ ፲፱

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
@Abrham2319
@Abrham2319_group
@Abrham2319_bot









Показано 20 последних публикаций.