ይህ ሳምንት የዐብይ ጾም ስድስተኛው ሳምንት ሲሆን እንደሌሎቹ ሰንበታትና ሳምንታት ሁሉ ይህም ሳምንት የራሱ የሆነ መጠሪያ አለው:: ገብር ኄር ይባላል:: ትርጓሜውም በጎ፣ ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው::በዚህ ሳምንት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምታስተላልፈው መልእክት ከባለፈው ሳምንት/ደብረ ዘይት/ የቀጠለ ነው:: የዐብይ ጾም አምስተኛው ሳምንት /ደብረ ዘይት/ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት የሚታሰብበት ሲሆን ይሄኛው ሳምንት ደግሞ ነቢዩ ዳዊት “እስመ አንተ ትፈድዮ ለኵሉ በከመ ምግባሩ/አንተ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ትከፍለዋለህና/ መዝ 61፡12 እንዳለ ጌታ ዳግም ሲመጣ ለሁላችንም እንደ ሥራችን ዋጋችንን እንደሚከፍለን የምናስብበት ሳምንት ነው::
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው ስለ ዳግም ምጽአቱና ስለሚሆነው ምልክት ሲጠይቁት በመጀመሪያ በ70 ዓ ም አካባቢ የሚሆነውን የኢየሩሳሌምን ጥፋት ከዚያም በኋላ እሱ ዳግም ሲመጣ የሚሆኑትን ምልክቶች ከነገራቸው በኋላ ከዚሁ ጋር አያይዞ የእርሱን መምጣት ተከትሎ የሚሆነውን ክስተት በሦስት ምሳሌዎች ለጊዜው ለደቀመዛሙርቱ በመጨረሻ ግን ለሁላችንም እንዲሆን ነግሮናል::
የመጀመሪያው በቤተሰቦቹ ላይ የሾመውን የጌታውን አደራ በሚገባ በመወጣቱ በጌታው ዘንድ በተመሰገነው በልባሙ ባሪያ ምሳሌነት ለመልካም የሚተጉ ሰዎችን አስደሳች ፍጻሜ፣ እንደዚሁም በተቃራኒው የጌታውን አደራ ችላ በማለት የማይገባ ሥራ በመሥራት ጊዜውን ባባከነው ክፉ ባሪያ ምሳሌነት የቸልተኞችን አስከፊ ፍጻሜ የሚያሳየው ነው (ማቴ 24፡45-51)::
ሁለተኛው የሙሽራውን መምጣት በዝግጅት ይጠብቁ በነበሩ በአምስቱ ብልሆች ደናግላን ምሳሌነት የዝግጁዎችን ስኬታማ ፍጻሜ፣ እንደዚሁም ባልተሟላ ዝግጅት የሙሽራውን መምጣት ሲጠባበቁ በነበሩ በአምስቱ ሰነፎች ደናግላን ምሳሌነት ማስተዋልና ጥንቃቄ በጎደለው ሕይወት የሚኖሩ ሰዎችን ፍጻሜ የሚያሳየው ነው ፡፡ (ማቴ 25፡1-13)
ሦስተኛው ደግሞ ከመጀመሪያዎቹ ሁለቱ በተለየ መልኩ በዚህ ሳምንት በይበልጥ የሚታሰቡ ከጌታቸው ዘንድ መክሊትን የተቀበሉ ባሮችን ታሪክ የያዘው ምሳሌ ነው::
በሦስቱም ምሳሌዎች ላይ የምናያቸው ተመሳሳይ ነገሮች አሉ:: ልባሙንም ሆነ ክፉውን ባሪያ በቤተሰቦቹ ላይ የሾመው ጌታ ደናግላኑ የሚጠብቁት ሙሽራ እንዲሁም ለአገልጋዮቹ መክሊትን የሰጠው መንገደኛው ሰው እንደሚመጡ በተናገሩት መሠረት ሁሉም መጥተዋል:: እንደዚሁም ከመጡ በኋላ ሁሉም መምጣታቸውን ሲጠባበቁ ለነበሩ ሰዎች የሚገባቸውን ዋጋ ሰጥተዋቸዋል::
በቅዱስ ወንጌል ላይ እንደተገለፀው አንድ መንገደኛ ሰው መንገድ ከመጀመሩ በፊት ለአገልጋዮቹ ነግደው ያተርፉበት ዘንድ እንደየአቅማቸው ለአንዱ አምስት ለአንዱ ሁለት እንዲሁም ለሌላኛው አንድ መክሊትን ሰጥቷቸው ሄደ:: አምስት እና ሁለት መክሊት የተቀበሉት በታዘዙት መሠረት በተቀበሉት መክሊት አትርፈው ጌታቸውን ሲጠብቁት አንድ መክሊት የተቀበለው ግን በተቀበለው መክሊት ለማትረፍ ከመውጣትና ከመውረድ ይልቅ መክሊቱን ቀብሮ ጌታውን ይጠብቅ ነበር::
የአገልጋዮቹ ጌታም ከሄደበት ሲመለስ አገልጋዮቹን የሰጣቸውን መክሊት ምን እንዳደረጉበት ጠየቃቸው:: ሁለቱ አገልጋዮች (አምስት እና ሁለት የተቀበሉት) በተሰጣቸው መክሊት ማትረፋቸውን ሲናገሩ አንድ መክሊት የተቀበለው ግን እንዲሠራበት የተሰጠውን መክሊት እንደቀበረው ተናገረ:: መቅበሩም ብቻ ሳይሆን “አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ፣ ካልበተንህበት የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ ሰለፈራሁም ሄድሁና መክሊትህን በምድር ውስጥ ቀበርሁ” በማለት በጌታው ላይ የማይገባ ንግግርን ተናገረ:: የአገልጋዮቹ ጌታም አደራቸውን ጠብቀው በተሰጣቸው መክሊት ለማትረፍ የደከሙትን አገልጋዮች በጥቂቱ በመታመናቸው በብዙ ሲሾማቸው መክሊቱን የቀበረውን ያንን ሀኬተኛ ባሪያ ግን በተግሳፅ ወደ ውጪ (ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወደ አለ ጨለማ) እንዲያወጡት አዘዘ:: ማቴ 25፡14-30::
በዚህ የወንጌል ክፍል ላይ ሁለት ነገሮችን እናስተውላለን::
1. እነዚያ አገልጋዮች እያንዳንዳቸው ከጌታቸው ዘንድ መክሊትን ተቀብለዋል:: የአገልጋዮቹ ጌታም አስቀድሞ ለአገልጋዮቹ መሥሪያ መክሊትን ሰጥቷቸዋል:: ትርፉን የጠየቃቸው አስቀድሞ ሥራ ለመጀመር የሚጠቅማቸውን መክሊት ከሰጣቸው በኋላ ነው:: አስቀድሞ ምንም ሳያደርግላቸው ድንገት ትርፍ አልጠየቃቸውም:: ነገር ግን ሁሉም እኩል መክሊትን አልተቀበሉም:: ከላይ እንደተገለፀው የተቀበሉት አንደኛው አምስት አንደኛው ሁለት ሌላኛው ደግሞ አንድ መክሊትን ነው:: ይሄም የሆነው ያለ ምክንያት አልነበረም:: የአገልጋዮቹ ጌታ በእንደዚህ ያለ መልኩ መክሊቱን ያከፋፈላቸው አገልጋዮቹ ያለ ጭንቀት መሥራት በሚችሉበት አቅም ልክ ተቀብለው ውጤታማ እንዲሆኑ ነበር:: ስለዚህ የአገልጋዮቹ ጌታ“ለአያንዳንዱ እንደ ችሎታው” ማቴ 25፡15 ተብሎ እንደተገለጸ ለአገልጋዮቹ የአቅማቸውን ያህል እንጂ ከአቅማቸው በላይ የሆነ መክሊትን አልሰጣቸውም:: ጠቅለል ባለ መልኩ እነዚያ አገልጋዮች በመጀመሪያ ከጌታቸው ዘንድ በአቅማቸው ልክ መክሊትን ተቀብለዋል:: የተጠየቁትም ትርፍ እንደ አቅማቸው በተቀበሉት መክሊት መጠን ሊያተርፉት የሚችሉትን ያህል ብቻ ነው::
2. በዚህ የወንጌል ክፍል የምንመለከተው ሌላው ነገር የአገልጋዮቹ ጌታ ከሄደበት ሀገር ሲመለስ አገልጋዮቹ በመክሊቱ ምን እንደሰሩበት ጠይቋቸዋል:: መክሊቱን ለአገልጋዮቹ ካከፋፈለ በኋላ ረስቶት አልቀረም:: እያንዳንዳቸውን ጠይቋቸዋል:: መጠየቁም በመክሊቱ ምን እንዳደረጉበት ሰምቶ ብቻ ለማለፍ አልነበረም:: ነገር ግን መጀመሪያም ቢሆን ለአገልጋዮቹ መክሊቱን የሰጣቸው እንዲያተርፉበት እንጂ ተቀብለው የትም እንዲጥሉት ባለመሆኑ በሰጣቸው መክሊት ምን እንደሰሩበት የጠየቃቸው የመክሊቱን ውጤት ለማየት ካለው ጥልቅ ፍላጎት ነው:: ምክንያቱም የመክሊቱ ባለቤት ለአገልጋዮቹ በፈቃዱ የራሱን ሀብት የሰጣቸው እንደተጠቀሰው እንዲያተርፉበት ነው:: በዚህም ምክንያት ከሄደበት ሀገር ሲመለስ የእያንዳንዳቸውን ትርፍ ጠየቃቸው::
የዚህ ምሳሌያዊ ታሪክ ዋና ዓላማ ከጌታ ዳግም ምጽአት በኋላ የሚሆነውን ለእኛ መጠቆም ስለሆነ በዚሁ መልኩ መረዳት ይኖርብናል:: በመክሊቱ ባለቤት ጌታ የተመሰለው እግዚአብሔር ነው:: ከጌታቸው ዘንድ መክሊትን የተቀበሉ አገልጋዮች ደግሞ የእኛ የሰው ልጆች ምሳሌዎች ናቸው:: እነዚያ አገልጋዮች በኋላ የሚጠየቁበት መክሊትን በአቅማቸው ልክ ከጌታቸው እንደተቀበሉ እኛም ጌታ ዳግም ሲመጣ የምንጠየቅበት በአቅማችን ልክ ከጌታችን የተቀበልነው መክሊት (ጸጋ) አለ::
የአንዱ ጸጋ ማሰተማር ሲሆን የሌላኛው ደግሞ መማር ሊሆን ይችላል እንደዚሁም የአንዱ ጸጋ መቀደስ ሲሆን የሌላኛው ማስቀደስ ይሆናል ወዘተ:: ምንም እንኳን የእያንዳንዳችን ጸጋ የተለያየ ቢሆንም ከእግዚአብሔር ጸጋን ያልተቀበለ ሰው ግን የለም::ስለዚህ ሁሉም እንደተሰጠው ጸጋ መጠን ኃላፊነት አለበት:: ስለዚህ ጌታ ዳግም ሲመጣ እያንዳንዳችንን በሰጠን ጸጋ ምን እንደሰራንበት ይጠይቀናል::
እዚህ ላይ እያንዳንዳችን በተሰጠን ጸጋ ምን እንደሠራንበት ጌታ ዳግመኛ ሲመጣ እንደሚጠይቀን ማስተዋል ይገባናል:: በተሰጠው ጸጋ ያልሠራበት ሰው በምንም ዓይነት ምክንያት ከተጠያቂነት አያድነውም:: ምክንያቱም ከአምላካችን የተቀበልነው ጸጋ ውጫዊ ተጽእኖዎችን መቋቋም የምንችልበት ኃይላችን ነው::