ቆንጅዬ፣ ዓሊም እና የዓሊም ልጅ የተዳረችበት: ማራኪ እና እውነተኛ ታሪክ!!
ሰዒድ ኢብኑ ሙሰይብ ብርቅዬ ከሆኑ የኢስላም ቀደምት ምሁራኖች ውስጥ አንዱ ነው። የዕውቀት ማዕዱ በጣም በርካታ የሆኑ የዲን ተማሪዎች ተሰብስበው ይጣዱት እንደነበር ታሪክ ያረጋግጣል። ከዕለታት በአንዱ ቀን ተማሪዎቹ ሲመለከት ከመሃል አንድ ወጣት ከትምህርት ቦታው ይጠፋል። ሲጠባበቀው ቆየና ወደ ትምህርት ቦታው የተመለሰ ቀን ጠየቀው።
"ወዳጄ ሆይ! የት ሆነህ ነው እስከዛሬ ያልመጣኸው?" ሲል ጠየቀኝ። ይላል
"ባለቤቴ ሙታብኝ እሷን እየደፈንኩ እና በሷ ጉዳይ ተወጥሬ ነው።" ብዬ መለስኩለት
ሰዒድ: "ታድያ አትነግረንም ነበርን? ቢያንስ እኮ መጥተን እንኳ እናፅናናህ ነበር።" አለኝ
አስከትሎም: "እሺ አሁንስ ሌላ ለማግባት ያሰብከው ነገር አለን?" አለኝ
"ኣ…ኢ…ኢ እኔ እኮ ከሦሥት ዲርኸም ሌላ የሌለኝ ሰው ነኝ ማን ይድረኛል?" አልኩት።
ሰዒድ: "ሱብሃነላህ!! ሱብሃነላህ!! ሦሥት ዲርኸም አንድን ሙስሊም አትሰትርም ማለት ነው??" አለኝ በመገረም
"ማን ይድረኛል??" አልኩት
"እኔ!!" አለኝ
"ያቺ መሪዎች እና ሚኒስትሮች እየጠየቁ የተከለከለችዋ የሰዒድ ኢብኑ ሙሰይብ ልጅ!?" አልኩት
"እኔ እድርሃለው።"
አለኝና እዛው ከመስጂድ አካባቢ የነበሩ ሰዎች ጠርቶ ሰበሰባቸውና
"እከሊት የእከሌ ልጅ: የእከሌ ልጅ ለሆነው እከሌ በሁለት ዲርኸም ድረነዋል!!" ብሎ ኒካህ አሰረልን።
በዚህ ጊዜ በደስታ የምከንፍ እየመ ሰለኝ ስፈናጠር ወደ ቤቴ ሄድኩኝ። የመግሩብ ወቅት ደረሰ፤ ጾመኛ ነበርኩኝና ለማፍጠር ዳቦዬ ምናምን ይዤ ቁጭ እንዳልኩ የቤቴ በር ተንኳኳ
"ማን ነው?" ስል
"ሰዒድ ነኝ።" የሚል ምላሽ ሰማሁ
አእምሮዬ ላይ የማውቃቸው ሰዒዶች ሁሉ ተመላለሱብኝ; ሰዒድ ኢብኑ ሙሰይብ ሲቀር፤ ምክንያቱም ሳውቀው አርባ ዓመታት በሙሉ ከቤቱ ወደ መስጂድ: ከመስጂድ ወደ ቤቱ ሲመላለስ እንጂ ሌላ ቦታ አይቼው አላውቅም ነበር።
ተነስቼ በሩን ስከፍተው ሰዒድ ኢብኑ ሙሰይብ ነው
በውስጤ "በቃ ሀሳቡን ቀይሮ ነው" አልኩኝ
"በዚህ ሰዓት ለምን መጣህ? ብታስጠራኝ እኮ እኔ እመጣልህ ነበር።" አልኩት
"ኣ…ኣ…ይ የአንተ ዐይነቱ እኮ ወደ እሱ ይመጣል እንጂ እሱ እንዲመጣ አይጠራም።" አለኝ
"እንግዲያውስ ድረንሃል: የዛሬዋ ምሽት ሚስትህ እኔጋ ሆና ላጤ ሆነህ ላሳድርህ ስላልፈለኩ ይዤልህ መጥቼ ነው።" ብሎ ከኋላው ጥቁር ለብሳ ቆማ የነበረችው ወደ ቤት ገፈተራት።
በድንጋጤ መሬት ላይ ወደቀች።
"بارك الله لك وبارك عليك
እቺ ሚስትህ ናት" አለኝና ትቶን ሄደ።
ስመለከታት የውበት ማማ የተላበሰች ሴት ናት። በአላህ እምላለሁ ዐይኔ ከእሷ በፊት እንደዚህ ያለ ውበት ዐይታ አታውቅም።
እየሮጥኩኝ ወጥቼ ጎረቤቶቼን ጠራኋቸው "ሰዒድ ኢብኑ ሙሰይብ ልጁን ድሮኛል: ይኸው አሁን ከመሸ ነው ይዟት የመጣው: ሄጄ ለእናቴ እስከምነግራት ገብታችሁ አጫውቷት።" ብያቸው ወደ እናቴ ሄድኩኝ።
ለእናቴ ሄጄ ስነግራት
"እኔ መጥቼ ሦሥት ቀናት ድረስ ሞሽሬያት እስከምሰጥህ ድረስ ብትጠጋት ፊቴ በፊትህ ላይ ዕርም አድርጌብሃለው: እኔ እስክመጣ እንዳትነካት" አለችኝ።
እናቴ መጥታ ሦሥት ቀናት ሞሽራ አስዋበቻትና ገባሁኝ: "ወላሂ ዐይኔ እንደሷ ያለ ውብ ዐይቶ አያውቅም።"
ከተናገረች ያማረ ንግግር ነው የምትናገረው: ዝም ካለችም ያማረ ዝምታ ነው ዝም የምትለው።
ከእሷ ጋ አብሬ አንድ ወር ቆየሁኝ: ከሷ ያየሁት ነገር የለም; ቀን መጾም እና ለይል መስገድ ቢሆን እንጂ። ከወር በኋላ ወደ ሰዒድ ሄጄ ትምህርቴን ለመቀጠል ፈለኩኝ።
"ወዴት ነው ምቴደው?" አለችኝ
"ለመማር ወደ ሰዒድ" አልኳት
"አርፈህ ተቀመጥ!! የሰዒድ ዒልም በአጠቃላይ እኔጋ አለ፤ እሱ የሚሰጥህ እኔ እሰጥሃለሁ።" አለችኝ
ሆኖም ከአንድ ወር በኋላ ወደ ሰዒድ ሄድኩኝ: መቀመጫው ላይ ሆኖ ሲያየኝ ፈገግ አለ። ሁሉም ሰው ጨርሶ እስኪወጣ ድረስ ግን ምንም አላናገረኝም።
የነበረው ሰው ጨርሶ ከወጣ በኋላ መጥቼ ከፊት ለፊቱ ተቀመጥኩኝ።
"እንግዳችሁ እንዴት ናት?" አለኝ
"በጣም ደስስስ በሚል ሁኔታ" አልኩት።
"እንግዲያውስ የማያስደስትህ ነገር ካገኘህ ዱላህን …………:"
አለኝና ሀያ ሺህ ዲናር በእጄ አስጨበጠኝና
"አንተ እና እሷ ለጉዳያችሁ ተጠቃቀሙባት።" ብሎ ተሰናበተኝ። ይላል።
ታሪኩ አበቃ
ምንጭ
📚[سير أعلام النبلاء ترجمة سعيد ابن مسيب /ج٤/ ص٢٣٤]
ታሪክህን መርምር: ዕውቀትህን ጨምር!
🪴https://t.me/kewollotita