🗞 ስለ ዓረፋ ቀን ዱዓእ ሁለት ነጥቦች
✍ አቡጁነይድ ሳላህ አሕመድ
[1] በኢድ ዋዜማው የዓረፋ እለት ዱዓእ ተቀባይነት እንዳለው የሚዘክሩ ሀዲሶች ሀጅ ላይ የሌሉ ሰዎችንም ይመለከታሉን??
የአላህ መልእክተኛ «ከዱዓዎች ሁሉ በላጩ (የኢድ ዋዜማ) የአረፋ ቀን ዱዓ ነው...» ማለታቸውን ቲርሚዚይ ከአብዱላህ ኢብኑ ኡመር የዘገቡ ሲሆን፤ ሌሎች ተመሳይ ይዘት ያላቸው ሀዲሶችም ይገኛሉ።
ታዲያ የዓረፋን እለት በዱአዕና በዚክር ያሳለፈ ሰው ታላቅ ክብርና ምንዳን የሚያገኘው ሀጅ ላይ ሲሆን ብቻ ነውን? በእርግጥ በዚህ እለት ክብር ባለው የዓረፋ ምድር የተገኘ ሰው የጊዜንም የቦታንም ክብር ተጎናፅፏልና በተሻለ ሁኔታ ላይ መገኘቱ እንዲሁም ዱአው ተቀባይነት ለማግኘት የቀረበ መሆኑ አያጠራጥርም። ይሁንና ሚዛን በሚደፋው የኡለማዎች አቋም መሰረት፤ እነዚህ ከአረፋ እለት ክብር ጋር ተያይዞ የዱአ ተቀባይነትን የተመለከቱ ሀዲሶች በማንኛውም ቦታ የሚገኙ ሙስሊሞችን ይመለከታሉ። በመሆኑም በሀጅ ስራ ላይ የሌሉ ሰዎችም በዱዓ ሊበረቱ ይገባል።
ታላቁ አሊም ሸይኽ ሳሊህ አልፈውዛን በዚህ እለት የሚባሉ በሀዲስ የተላለፉ ዱአዎችን አስመልክቶ ሀጅ ላይ ላሉ ሰዎች መሆኑን ተጠይቀው ተከተዩን መልሰዋል¹ «በምላሻችን እንደገለፅነው፤ ይህ ለሁጃጆችንም ይሁን ሌሎችን የተመለከተ ጥቅል መልእክት ነው። ነገር ግን ሀጅ ላይ ላሉ ሰዎች ይበልጥ የተገባ ነው። ምክኒያቱም ሁጃጆች በዚህ እለት በዓረፋ ምድር በኢህራም ውስጥ ስለሚገኙ ከሌሎች በበለጠ ዱዓቸው ተቀባይነት ለማግኘት የቀረበ ነው። ስለዚህም የዓረፋን እለት በሀጅ ተግባር ላይ የሌሉ ሰዎች እንዲፆሙት ተደንግጓል። እለቱ ብልጫ ያለወወ ስለሆነም አላህን በማስታወስ፣ ማርታን በመለመን እና ዱዓ በማድረግ ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ፤ ሁጃጆችንም በኢባዳ ይካፈሏቸዋል ማለት ነው።» ከሸይኹ ድረገፅ የተወሰደ የድምፅ ፈትዋ
[2] በዓረፋ እለት ሁጃጆች በአረፋ ምድር እንደሚሰባሰቡት ለዱዓና ለዚክር መሰባሰብ "ታዕሪፍ"ን በተመለከተ፤
ይህ ተግባር አንዳንድ ሰለፎች እንደፈፀሙት የተረጋገጠ ነው። ከነሱም መካከል ኢብኑ አባስ ይገኙበታል፤ ኢማሙ አህመድም ባይተገብሩትም እንደሚቻል ተናግረዋል።
ነገር ግን ያወገዙትና ከቢድአ የመደቡትም አሉ። የኡለማዎቻችንን ማብራሪያዎች ስንፈትሽ ተከታዮቹ ድምዳሜዎች ላይ ያደርሱናል፤
1) "ታእሪፍ"ን መተግበር በራሱ ችግር የለውም። ተግባሩን እንደሱና ወይም ሙስተሀብ ነገር መውሰድ ግን አይገባም። ጉዳዩ የኢጅቲሀድ መስአላ ነውና ተግባሩ የሚወገዝ ተግባር አይሆንም። የፈፀመውም ሰው ቢድአ ሰራ አይባልም።
2) ታእሪፍ ስንል ከምድረ አረፋ ውጭ ባሉ የየሀገሩና የየከማው መስጂዶች መሰባሰብን የተመለከተ እነጂ ለዚህ ብሎ ጉዞ ማድረግ አይፈቀድም። አላህ የአረፋን ምድር ለዚህ ቀን ኢባዳ መሰባሰቢያ እንደመረጠው በየሀገሩ አንዳንድ ቦታዎችን፣ መስጅዶችንና ቀብሮችን በመምረጥ ወደነሱ ጉዞ አድርጎ መሰባሰብ በፍፁም አይፈቀድም። ይህ የነብዩ መስጂድንም ይሁን በይተልመቅዲስን ያካትታል።
3) ይህ መሰባሰብ ጩኸትና ሱና ያልሆኑ የጋራ አምልኮዎች ከታከሉበት ቢድአ እንደሚሆን አያጠራጥርም። በተመሳሳይ መልኩ ኢባዳ ያልሆኑ ግጥሞችና መንዙማዎችን ለዚህ መለያ ማድረግ ጥፋት ነው።
እነዚህን ነጥቦች በዝርዝር ለመረዳት የሚያስችሉ ማብራሪያዎችን ከኡለማዎች ድርሳናት እንደሚከተለው እናያለን።
ቀሪዉን የፅሁፍ ክፍል ተከታዩን ሊንክ በመከተል ያንብቡት
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=10160553120869684&id=682494683
__
📮የአቡጁነይድ መልዕክቶች
t.me/abujunaidposts