በረመዳን ወር ቴልቪዥን እና ቪዲዮ መመልከት ፆምን ያጓድላልን?
መልስ - አንድ ሠው የሚያዳምጠው ወይም የሚመለከተው ነገር ከተፈቀዱ ነገሮች (ሙባሀት) ከሆነ ምንም ችግር የለውም ፆምመአ ላይ እንከን አይሆንም፡፡ ሆኖም ግን ፆመኛ ሰው ጊዜውን ወደ አላህ ሊያቃርበው በሚችል ነገር ብቻ ነው ማሳለፍ ያለበት፡፡ ቁርዓንን ያነባል አላህን ያወድሳል ወዘተ...
አላህ ሀራም ያደረገውን ነገር ማዳመጥ ወይም መመልከት ግን ፆምን እንደሚያጓድል ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ የዚህም ምክንያት ፆም የተደነገገበት አላማ የአላህን ፍራቻ (ተቅዋን) መላበስ ነው፡፡
قال تعالى{يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُواْ كُتِبَ عَلَيْكُمُ الصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ} البقرة : 183
«እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደተደነገገ ሁሉ በናንተም ላይ ተደነገገ። ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡»አልበቀራህ 183
አላህ በዚህ አንቀፅ ፆም በግዴታነት የተደነገገበት አላማ ተቅዋ መሆኑን ገልፆዋል፡፡
عن أبي هريرة رضي الله عنه قال قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: (من لم يدع قول الزور والعمل به فليس لله حاجة في أن يدع طعامه وشرابه) صحيح البخارى
የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል ‹‹መጥፎ ንግግርን እና መሀይምነትን ያልተወ ሰው አላህ ዘንድ ምግብና መጠጥ መተው ቦታ የለውም (ቡኻሪ ዘግበውታል)
በዚህ መሠረት ማንኛውም ፆመኛ የሚሠራው ሀጢዓት ፆሙ ላይ ተፅዕኖ አለው፡፡
ከዚህም ውስጥ አንዳንድ ሠዎች እንደሚያደርጉት ከምግብ ከመጠጥና ከስጋዊ ተራክቦ ይቆጠቡና በአላህ ላይ ያምፃሉ፡፡ አንዳንዱ ሱሁር ከበላ በኋላ ይተኛና የፈጅርን ሠላት ያሣልፋል የሚነሣው ፀሃይ ከወጣች በኋላ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ የዓስርን ሠላት ሣይሰግድ ይተኛና በኢፍጣር ሰዓት ተነስቶ አራት ጊዜ ጎንበስ ቀና ይላል፡፡ ጥቂትን እንዲ አላህን አያድስም፡፡ አንዳንድ ሠዎች ደግሞ ሠዎችን ያማሉ በንግድ ወቅት ያጭበረብራሉ ብዙ ወንጀሎችንም ይፈፅማሉ፡፡ ይህን ሁሌ የሚያደርጉት ፆመኛ ሆነው ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ የሚፈፅሙን ሀራም ተግባር የፆማቸውን ምንዳ እንደሚቀንሠው ጥርጥር የለውም፡፡ ምናልባትም ምንዳውና ሀጢአቱ እኩል ይሆኑና የፆሙን ምንዳ ያጣሉ፡፡
ለሙስለሊም ወንድሞች እና እህቶች የማስተላልፈው ምክር፤ አላህ በእነርሱ ላይ እርም ካደረጋቸው ነገሮች እና ተግባሮች ፆማቸውን እንዲጠብቁ እና ይህን የተባረከ ወር አላህን በመታዘዝ እንዲያሳልፉት ነው፡፡ እርም ነገሮችን ከመተው እና ግዴታዎችን ከመፈፀም ረገድ ራሳቸውን የሚያንፁበት ታላቅ እድል ነው፡፡ ወቢላሂ ተውፊቅ!
ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ኡሰይሚን
@abujunaidposts