አባት ልጁን ሊመግብ አስቦ ከጎኑ ቁጭ አደረጋትና ብርትኳን መላጥ ጀመረ ። ልጅ ለመብላት ጓጓችና ብርትኳኑን ለመቀበል እጇን ሰደደች ፣ አባትም '' ትንሽ ታገሺ ለአንቺው ነው የምልጠው '' አላት ። ልጅ መብላት ጓጉታለችና አልሰማ ብላ ለሁለተኛ ጊዜ ብርትኳኑን ከአባቷ ልትነጥቅ እጇን ላከች '' አባትም ግድ የለሽም ትንሽ ብቻ ታገሺ እየላጥኩ ያለሁትኮ ለራስሽ ነው ደግሞ ብሰጥሽም መላጥ ስለምትችዪ ትቸገሪያለሽ እስከነ ልጣጩ ብትመገቢው ደግሞ በጣም ይመርሻል እናም ትንሽ ጠብቂ '' አለ ። ልጅ አልታገስ ብላና በአባቷ አዝና ለቅሶዋን አስተጋባች ።
ወዳጄ , አንተስ ከፈጣሪህ ጋር ያለህ ሁኔታ ምን ይመስላል ? አሏህ የፃፈልህ ሲሳይ ትክክለኛ ጊዜውን ጠብቆ ተሽሞንሙኖ እስኪመጣ በትዕግስት ትጠብቃለህ ወይንስ ልክ እንደ ህፃኗ ትዕግስት አጥተው ከሚያማርሩትና ከሚወራጩት ነህ ?
ሁላችንም የየራሳችን ብርትኳን አለን ። የአንዳዳችን ቶሎ ተልጦ ሲመጣ የሌሎቻችን ደግሞ ለመልላጥ ተራውን እየጠበቀ ነው ። ታድያ አንታገስምን ?!
__________________
𝘑𝘰𝘪𝘯 @abumahi