ካዕባ ላይ ምራቅህን ትተፋለህ ?
____________________________
አሁን ከካዕባ ፊት ቆመህ ቢሆን ካዕባ ላይ ምራቅህን ትተፋ ነበር ? የካዕባን ክብር በማይመጥን መልኩስ ትሰድበውና ልታረክሰው ትሞክር ነበር ?
እርግጠኛ ነኝ አንተም ሆንክ የትኛውም ብናኝ የምታህልን እምነት በልቡ የያዘ ሙስሊም ይህንን አያደርግም ። ኧረ እንደው ማድረጉ ቀርቶ እንዲህ ያለ ሰይጣናዊ ተግባር በሀሳቡ እንኳ ውል አይልበትም ።
ታድያ ምነው ከካዕባ የበለጠ ክብር ያለው ፍጥረት ላይ የተለያዩ በደሎችን ለመፈፀም እጃችንና ምላሳችን ቀለላቸውሳ ?! ከካዕባ በላይ ክብር ያለው ማን እንደሆነ ግር ብሎሀል ? እንግዲያውስ ረሱል ﷺ ይመልሱልህ
رأيتُ رسولَ اللَّهِ صلَّى اللَّهُ عليْهِ وسلَّمَ يطوفُ بالكَعبةِ ويقولُ ما أطيبَكِ وأطيبَ ريحَكِ ما أعظمَكِ وأعظمَ حرمتَكِ والَّذي نفسُ محمَّدٍ بيدِهِ لَحُرمةُ المؤمنِ أعظَمُ عندَ اللَّهِ حرمةً منْكِ مالِهِ ودمِهِ وأن نظنَّ بِهِ إلَّا خيرًا
በሆነ አጋጣሚ ረሱል ﷺ ካዕባን ጠዋፍ እያደረጉ እንዲህ አሉት '' ምንኛ አምረሃል መዐዛህም ምንኛ አምሯል ፣ ምንኛስ ተልቀሃል ክብርህም ምንኛ ተልቋል ...የሙሀመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ አሏህ ዘንድ አንድ ሙዕሚን ከአንተ የበለጠ የተከበረ ነው የእርሱ ገንዘቡም ደሙም ( አሏህ ዘንድ ከአንተ የበለጠ የተከበረ ነው ) ፣ ( አንድ አማኝ ) በመልካም እንጂ በሌላ ( በክፉ ) ላንጠረጥረውም ( ክብሩ ከአንተ ልቋል ) ''
[ በቀላል አተረጓጎም ወደ አማርኛ የተመለሰ ]
" السلسلة الصحيحة " رقم : 3420 و " صحيح الترغيب والترهيب " رقم 2441 ]
ዛሬ እንደቀልድ በተውረግራጊ ምላሳችን ከፍ ዝቅ የምናደርጋቸው ፣ ክብራቸው ያለ ርህራሄ የምንገፋቸው ፣ ባልተረጋገጠ መረጃ ላይ ተንተርሰን አሉባልታ የምንነዛባቸው አማኝ ወንድምና እህቶቻች አሏህ ዘንድ ከካዕባ የበለጠ የተከበሩና ውድ ናቸው ።
የካዕባን ክብር ለመዳፈር ብትሞክር ከአሏህ ዘንድ ምን ሊጠብቅህ እንደሚችል ማወቅ ከፈለግክ '' የአብረሃን '' ታሪክ በሱረቱ አል~ፊል ላይ መመልከት ይበቃሀል ። አሏህ ዘንድ ከካዕባ የበለጠ ክብር የተሰጠውን ሙዕሚን አሳዝነህ ደግሞ ምን ሊገጥምህ እንደሚችል አስበው ...
መልዕክቱ አብዝቶ ሴት እህቶችን ይመለከታል
___________________________
join || https://www.facebook.com/profile.php?id=100079028036202