እጅህን ተሰበርክና መዳን ከጅለህ ወጌሻ ዘንድ ሄድክ ። ወጌሻው ህክምናውን ሲጀምር የተሰበረውን አጥንት እያዟዟረና እያሸ ህመምህን ይበልጥ ያበረታዋል ። ወጌሻው የተሰበረ እጅህን ነካክቶ ህመምህን የጨመረው ሊጎዳህ ስለፈለገ ነው ? አይደለም ! አንተም እንደዚያ አታስብም ። የሚያሳምምህ ሊጎዳህ ፈልጎ መሆኑን ብታምንማ ገና ሲነካ እብድ የሚያደርግ የተሰበረ እጅህን እንደፈለገ እንዲጨማምቀው አሳልፈህ አትሰጠውም ።
ሀዘን ፣ መከዳት ፣ ብቸኝነት ፣ ብሶት ፣ ማጣት ፣ ችግር ፣ ስቃይ ፣ መከራ ... ህይወትህንና ነፍስህን ሰባብሯታል ። ሰዎች ዘንድ ብርቱ መስለህ ውለህ ለብቻህ ስትሆን ተንሰቅስቀህ የምታነባው ፣ ለወጪ ለወራጁ ፈገግታህን ስትለግስ ቆይተህ ከራስህ ጋር ስትሆን ውብ ፊትህን ሀዘን ጨለማ የሚያወርሰው ድቅቅ ብለህ ስለተሰባበርክ ነው ። ከስብራትህ መዳን ትፈልጋለህ ?
ወጌሻውን አምነህ እጅህን እንደሰጠኸውና ሲያሽህ የተፈጠረውንም ህመም ጥርስህን ነክሰህ እንደታገስከው ወደ አሏህም ተጠጋና ስብራትህን አንድም ሳታስቀር ንገረው ። ሲያክምህና ሲጠግንህ የሚኖረውንም ህመም ጥርስህን ነክሰህ ታገስ ። አሏህ የሚያሳምምህ እንዳልታመምክ አድርጎ ሊያሽርህ ነው ።
ትዕግስት መራራ ነው ' ውጤቱ ግን የማይነጥፍ ጣፋጭ የማር ጅረት ነው !
_____________
@abumahi