«ክርስቶስ ከዚች ገዳም አለ»
⛪️እመ ምዑዝ ፍቅርተ ክርስቶስ ገዳም⛪️
★ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ4ቱም አቅጣጫ የሰገደች ቤተ መቅደስ
★ በልዩ ሁኔታ መካን የሚፈታ ጨጓራን የሚያድን ደዌን የሚያርቅ ድንቅ ቦታ
★እስከ ዕለተ ምፅአት ድረስ የማይፈርስ ቤተ መቅደስ
★የጣልያን ጦር አዛዥ የመሰከረለት
★★★★★★ፃድቋ፣ ሰማእቷ፣ ታአምረኛዋ፣ ደጓ፣ ሀዋርያዊቷ፣ ከፋሌ ባህሯ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ትውልዷ ደ/ጎንደር ደራ ፎገራ አንበሳሜ ከእናቷ ከወንጌላዊት ከአባቷ ከላባ በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ ቀን ታህሳስ 29 በታዘዘ መልአክ አብሳሪነት ተወለደች። ልደታቸው ከጌታችን ጋር ከገጠመላቸው ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ ቅዱስ ላሊበላ፣ ቅዱስ ነአኩተለአብ፣ ከአብረሃ ወአፅብሀ፣ አቡነ አካለ ክርስቶስ፣ አቡነ መዝራእተ ክርስቶስ፣ መስፍን ኢያሱ፣ የገርኣልታው አቡነ ዳንኤል፣ አቡነ አብሳዲ፣ አቡነ ፄዋለፅድቅ፣ ዳግማዊ ቂርቆስ ዘቡልጋ የሷም ልደት ገጥሟል። ስትወለድም በእግሯ ቆማ «በማኅያዊ ቸርነትህ ከጨለማ ወደ ብርሃን ላወጣኸኝ ለአብ ምስጋና ለወልድ ምስጋና ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል» ብላ አመስግናለች። በስእለት ስለተገኘች ስሟን ማርያም ጸዳለ አሏት።
★★★ እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስ በነበረችበት ዘመን አፄ ሱስንዮስ ሁለት ባህሪይ የሚለውን የረከሰ የካቶሊኮች አስተምህሮ የሀገራችን ህዝብ እንዲያምን አውጆ በሀገሪቱ ትልቅ ቀውስ ተከስቶ ከ8 ሺህ በላይ ክርስቲያኖች በግፍ ተጨፍጭፈው ሲያልቁ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ከነ አቡነ ስምዖንና ከሌሎች ቅዱሳንና ቅዱሳት ጋር ተሰልፋ ሰማእትነት ተቀብላ ለሀይማኖቷ ምስክር ሆናለች።
★★★ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን የሃይማኖቷን ፅናት ስላየ ስጋዋ እየተቆረሰ መሬት ላይ እስኪወድቅ ድረስ በብረት በትር አጥብቆ ያስገርፋት ጀመር። በመጨረሻም ምድር እየሰወረቻት ለመግረፍ የማይመቻቸው ቢሆን ከሌሎች ሰማእታት ጋር አንገቷን በሰይፍ አስቆርጦታል። በዚህ ጊዜ ፍፁም ጨለማ ሆኖ ምድርም ተነዋወጠች።
ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን አንገቷን በሰይፍ ቢቆርጧትና በሞት ብታርፍም ነገርግን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ገነትና ሲኦልን አሳይቶ 14 ቀን በሰማያዊት ኢየሩሳሌም ከተቀመጠች በኋላ እንደገና እንደተኛ ወይም ከእንቅልፉ እንደሚነቃ ሰው ከሞት አስነስቶ ወደ ቦታዋ መለሳት።
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከሞት ካስነሳት በኋላ በየገዳማቱና በየአድባራቱ እየዞረች ያቀናቻቸው ብዙ ገዳማት አሉ።
ለአብነትም በተሰአቱ ቅዱሳን አንዱ በሆኑት አባ ጉባ ተመስርቶ የነበረውንና በግራኝ ጠፍቶ የነበረውን ታላቁን የራማ ኪዳነምህረት ገዳምን ያቀናችው ያቋቋመችው እንዲሁም የወንድ የሴት ብላ ስርአት የሰራችው እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ናት።
★★★ እናታችን ከተከታዮቿ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም እየሄደች ሳለ መንገድ ላይ በላአይተ ሰብ (ሰውን ወይም የሰው ስጋ የሚበሉ) ይዘዋቸው 60 የሚደርሱ አገልጋዮቿን ለመብላት አይናቸውን በጉጠት አውጥተው 4 ወራት በጨለማ ቤት ውስጥ ዘጉባቸው። ሰይጣንንም ያመልኩ ስለነበር ከ 4 ወራት በኃላ በአል አድርገው ለመብላት ከእሳት ውስጥ ጨመሯቸው ነገር ግን ጌታችን በቸርነቱ ጠብቋቸዋልና እነ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ምንም አልሆኑም። ያንጊዜም ሰው በላዎቹ «እናንተ ሰዎች ምንድን ናችሁ?» ብለው ጠየቋቸው። ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም ክርስቲያን መሆናቸውንና የሥላሴ ህንፃ የሆነውን የሰውን ልጅ መብላት እንደሌለባቸው ብታስተምራቸው «ምን እንበላለን» አሏት። እርሷም ከራማ ኪዳነ ምህረት ይዛው የመጣችውን ስንዴ ዘርታ በአንድ ቀን አድጎ ታጭዶ ተወቅቶ ተፈጭቶ ተጋግሮ ለምግብነት ደርሷል ቅድስት እናታችንም ቀምሳ ብታቀምሳቸው እንደ ማር እንደወተት የጣፈጠ ሆነላቸው ከዚያም እንዲያ እያደረጉ እንዲበሉ አድርጋ አስተምራም አስጠመቀቻቸው ስድስት አብያተ ቤተ ክርስቲያናትን አሰርታላቸው ወንጌልን፣ ስንክሳርን፣ ሃይማኖተ አበውን፣ ግንዘትን፣ መዝሙር ዳዊት፣ አርጋኖንን ሁሉ በእጇ ፅፋ አስቀመጠችላቸው።እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ የከበረች ሀዋርያዊት መሆኗን ከዚህ እንረዳለን።
★★★በእውነት ፍቅሯ ይደርብንና አምላክን የወለደች በድንጋሌ ስጋ በድንጋሌ የፀናች ክብርት እመቤታችን ድንግል ማርያም ተገልጣላት በልጇ ምክንያት የደረሰባትን ሀዘኖች አውላታላታለች። የፈለገችውን እንድታደርግበት በእጇ ያለውን መስቀል ለቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ሰጥታታለች። በዚህም መስቀል እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስ ባህር ከፍላ ደቀ መዛሙርቶቿን አሻግራለች። የአባታችን የአቡነ ኤዎስጣጤዎስ ገድል በማንበብና በመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል እርዳታ ባህሩን በአፅፏ ተሻግራ ወደ ሀገረ ናግራን ሄዳለች። እንዲሁም በበትረ መስቀሏ እንደ አቡነ ዘርአብሩክ ባህር ውስጥ የሰጠሙ የደቀ መዛሙርቶቿን መፅሀፍት ምንም ሳይሆኑ ማውጣት ችላለች። የእናታችንን ገድል ዘርዝረን እንጨርስ ብንል ጊዜ አይበቃንም ስለዚህ ★★★ስለገዳሙ ጥቂት ልበላችሁ
በአንድ ወቅት ጣልያን ሀገራችንን እንደወረረ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማትን እያወደመ መነኮሳትን እየገደለ እናታችን ገዳም ይደርሳል መነኮሳትም ሰማእት ለመሆንተዘጋጅተው ሲጠብቁ የጦር አዛዡና ሰራዊቱ የገዳሙን ክልል አልፈው መግባት አልቻሉም የገዳሙ ክልል ላይ ሲደርሱ በተአምር እግራቸው ተሳሰረ መቆምም መቀመጥም ሳይችሉ ቀሩ የጦር አዛዡም «ክርስቶስ በዚህ ገዳም አለ» ብሎ ሃምሳ ጠገራ ብር ሰጥቶ ተመልሷል
★★★ስለገዳሙ ስናወራ እናታችን ቦታው ላይ የብርሃን አምድ ተተክሎ ስላየች ምንታምር ብላ ጠርታታለች። በተጨማሪም ለጌታችን በአራቱም አቅጣጫ እንደሰው የሰገደው ቤተ መቅደስ በአንድ ቀን የተሰራ ሲሆን የተሰራውም በስሚዛ (በሰንሰል) እንጨት፣ በአይጥ ሀረግ፣ በነጠላ ማገር አድርጋ ሰርታ በአንድ ቀን ታህሳስ 16 በእለተ እሁድ ቅዳሴ ቤቱን አክብራለች ይህ ቦታ እስከ እለተ ምፅአት ድረስ እነደማይፈርስ ጌታችን ቃል ኪዳን ገብቶላታል።
★★★በገዳሙ እናታችን ድንጋይ ፈልፍላ የሰራችው ውሃ ማጠራቀሚያ አለ። በእናታችን የፈለቀ ፀበል ሲኖር እጅግ እጅግ ፈዋሽ የነፍስ የስጋ መድኃኒት ነው።
★ይህ ብቻ አይደለም ከስሩ በእናታችን የተተከለው ቄጤማ መሰል ተክል የስንቱን #መካን (መሀን) ማህፀን ፈትቶ ልጅ በልጅ አድርጓል
★በገዳሙ ውስጥ ያለው ሎሚ ደግሞ #የጨጓራ በሽታን ምንም ያህል የከፋ ቢሆን ለመጨረሻ ጊዜ ደህና ሰንብት ያስብላል።
★እናታችን ደጇ ለሄደ ብቻ ሳይሆን የገድሏን መፅሀፍ አዝሎ አምልክን ለተማፀነ ገድሏን አውርዳ ልጅ ታሳዝላለች።
★በገዳሟ ያለው ሌላኛው ሸንኮራ አገዳ ነው ይህ ታአምረኛ አገዳ ቢበሉት ደዌ ይፈውሳል አድርቀው ቢያጨሱት ቁራኛ መናፍስት ከቤት ያርቃል የመተት መናፍስትን ያስወግዳል።
★ገድሏ ካለበት አጋንንት አይደርስም፣ ደጇን የረገጠ አስራ ሁለት ትውልድ ይማርለታል፣ የገድሏን መፅሀፍ የፃፈ፣ ያፃፈ፣ የተረጎመ፣ በእምነት ሆኖ የሰማ ሀጢያቱ ይቅር ይባልለታል። ላይማር ደጇን አይረግጥም።
★★★በእውነት እጅግ የከበረች ፃድቅ ፅድቋ ለአለም የተረፈ፣ ሰማእት ስለ ክርስቶስ አንገቷን የሰጠች፣ ሀዋርያዊት መፅሀፍትን የፃፈች ያስተማረች ፣ ተአምረኛ ባህር የከፈለች በአንድ ቀን ዘርታ አጭዳ ጋግራ የመገበች ፣ መኖክሲት የመነኮሳት እናት የሆነች የእናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ፀሎቷ በረከቷ ረድኤቷ ይደርብን አሜን።★★★
የገዳሙ አድራሻ :— አማራ ክልል ሰሜን ወሎ (ፍላቂት) ገረገራ ከዛ ትንሽ የእግር መንገድ አለው።
@adbaratwegedamat