ምስለ አድባራት ወገዳማት


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን" "ስለ ቅዱሳን እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል" ሊቁ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱


'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>💁‍♂ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል።  ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል
ቻናሉን ለመቀላቀል ከስር ክፍት የሚለውን
መጫን በቂ ነው።
              'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'> ክፈት        ክፈት               
               ክፈት        ክፈት               
                                                   
ክፈት        ክፈት        ክፈት        ክፈት
ክፈት        ክፈት        ክፈት        ክፈት
                                                    
                                                   
                                                    
                                                    
                                                     
               ክፈት         ክፈት              
               ክፈት         ክፈት


Репост из: 🙏ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬ🙏
    ዘላለም  ሥላሴ   

📣✝️  እንኩዋን ለአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ  ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ  ✝️📣


❝ በሥላሴ ገመድ ፍጹም ታስረናል ፤ ከልባችን በማይነቀል በቅንዋተ ፍቅሩ ተቸንክረናል ፣ እርሱ ወዶናል አይጠላንም። እኛም በእምነት ይዘነዋል አንተወውም። ❞

     [  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ  ]

❝ እምነታችንም እንዲህ በባሕርይ በመለኮት አንድ ፤ በአካል ፤ በገጽ ሦስት ብለን ነው፡፡ እነዚህ በቅድምና የነበሩ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ አስቀድመን መላልሰን እንደ ተናገርን ቀዳማዊ ወልድ ሰው ስለ መሆኑና ስለ ቅድስት ሥላሴ የምናምነው እምነት ይህ ነው ፤ ከተማሩ ከሚያስተምሩ ተስፋን ከሚያስረዱ ቅዱሳን ሊቃውንት ለምዕመናን ሁሉ ገልጠን የምናስተምረው ፤ እውነተኛ ሃይማኖትን ከሚያስተምሩ የሰማይ አምላክ ከሾማቸው ከሐዋርያትም ሲያያዝ የመጣልን እጅ ያደረግነው እምነት ነው፡፡ በንጹሕ ልቡና በአፋችንም በልባችንም በዚህ ሃይማኖት እንመን ፤ ያለ ጥርጥርም በበጎ ግብር በቅን ሕሊና እናስተውል ፤ በዚህ እንድንድን መንግሥተ ሰማያትንም እንድንወርስ እንረዳለን፡፡ ❞


  
🗓 ሃይማኖተ አበው  🗓


ጥር ፯ [ 7 ]

ሕንጻ ሰናዖርን ማፍረሳቸውና ቅዳሴ ቤታቸው በዓል ይከበራል።

የሰናዖርን ሕንጻ ያፈረሱ ሥላሴ : የኃጢአታችንን ሕንጻም በቸርነታቸው ያፍርሱልን አሜን በእውነት !


✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


Репост из: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
#ድምፅ_መስጠት_ተጀመረ!

#አንቴክስ_ፉድ_ኤይድ_ፕላስ ባዘጋጀው BIWs prize ብፁዕ አቡነ ኤርምያስን የሰላም ዘርፍ እጩ ተሸላሚ አድርጓቸዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ በሰላም ዘርፍ ከአምስት እጩዎች ውስጥ ተክትተዋል የዘርፉ አሸናፊ ከሆኑ #10ሚሊየን ብር ይሸለማሉ!!!

ብፁዕነታቸውን BIWን በማስቀደም ኮድ08 (BIW08) በማስገባት በSMS 9355 ላይ አሁኑኑ ይምረጡ!!! 

ድምጽ መስጠቱ እስከ ሐሙስ ታህሳስ 17/2017 ዓም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይካሄዳል!

በSMS 9355 ላይ BIW08 በማለት ብፁዕነታቸውን አሁኑኑ  ይምረጡ!!!

#10ሚልዮን #አንቴክስ #ፉድኤይድፕላስ #biwsprize #BTM #ብፁዕአቡነኤርምያስ  #ይምረጡ

Vote Abune Ermias now for the BIWs prize!

#AbuneErmias
#10million #BIWS2024 #Prize  #ANTEXETHIOPIA  #ANTEXTEXTILE  #FOODAIDPLUS #BESHATUTOLEMARIAMMULTIMEDIA


Репост из: 🙏ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬ🙏
🗓🌴
ከአንድ የሾላ ዛፍ ሥር ስትቃርም የነበረችን አይጥ ከነነፍሷ ለመያዝ ከወደሰማይ የነበረው አሞራ ቁልቁል ተምዘግዝጎ ይወርዳል። ሙከራው ለጥቂት በሚባል ሁኔታ ተሳክቶ የአይጧን ጭራ ይይዛል።

: አካሏ ግን ከዛፋ ሥር ካለ ጉድጓድ ገብቶ በልቀቀኝ ዐይነት መታገል ጀምራለች ጉልበቷን ያልተማመነችው አይጥ አሞራውን ለማጃጃል ጥበብ የተሟላ ንግግሯን ተጠቀመች።

: በዚህ መሰረት "አያ አሞራ! የእኔን ጭራ የያዝክ መስሎህ ከሾላው ሥር ጋር ስትታገል መንቁርህ እንዳይሰበር። ይልቅስ የሾላውን ሥር ልቀቅ አትልፉ"አለችው።

:  ቂላቂሉ አሞራም የያዛትን የአይጥ ጭራ ለቀቀ ይባላል

🦅🦅🦅🦅🦅🦅🦅🦅🦅🦅🦅
🇺🇿🇺🇿🇺🇿🇺🇿🇺🇿🇺🇿🇺🇿🇺🇿🇺🇿
እኛ ክርስቲያኖች ብልህ ልንሆን ይገባል ጠላት ዲያቢሎስ ሊያጠቃን ሲያደባ የአባቶችን ጥበብ በመጠቀም ልናመልጥ ይገባናል
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
የጥበብ አምላክ እግዚአብሔር ማስተዋልና ጥበቡን ያድለን


ለባለ✝️ ማህተቦች ሼር ያድርጉ⁉️
📣📣📣📣📣📣📣
#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ
📣📣📣📣📣📣📣


Репост из: 🙏ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬ🙏
🗓ዛሬ ማለትም
#ዕለት:- ማክሰኞ
#ቀን:- ታኅሣሥ ፰ ፳፻፲፯ ዓ.ም

በቅድስት ቤተክርስቲያናችን


አርባዕቱ እንሰሳ(ኪሩቢል) ፣ ሊቀ ነቢያት ፣ ሐዋርያዉ ማትያስ ፣ ካህኑ ዘካርያስ ፣ አባ ኪሮስ ፣ ቅድስት አመተ ክርስቶስ

አክብረን እና አስበን እንውላለን።

📣📣📣
✔️ የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው። ምሳ ፲፤፯

✔️  መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል መዝ.፻፳፮፥፮


✔️ "ቅዱሳን በዓለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን? ፩ኛ ቆሮ ፮:፪
የመላዕክት ፣ የቅዱሳን ፣ የሰማዕታት ተራዳይነት እና በረከት ከሁላችንም ጋር ይሁን

📣📣📣📣📣📣📣
📣#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ📣
📣📣📣📣📣📣📣


🗓#በዙሪያችን_ካሉ

በዙሪያችን ካሉ ድንቅ ምስክሮች
በእምነት በምግባር ከፀኑት እናቶች
ከፍ ብላ ታየች በገድሏ ብዛት
ንዕድ ክብርት ነች አርሴማ ቅድስት/2/


ሀብትና ንብረቷን ውበቷን የናቀች
ንግስት መባልን በእምነት የተወች
የኢየሱስ ክርስቶስ የስሙ ምስክር
የቅድስት አርሴማ ልዩ ነው የሷ ክብር
/2/
#አዝ
እግዚአብሄር ፅናቷን የመሰከረላት
በቤቱ በቅፅሩ መታሰቢያ አላት
የወንጌሉን ብርሀን ለዓለም ያበራች
ሰማዕቷ አርሴማ ለኛ አማላጅ ነች/2/
#አዝ

ይሔው በዚ ዘመን እግዚአብሄር ገለጣት
ለረድኤት በረከት ምክንያት አደረጋት
አክሊል ተጎናጽፋ ታይታለች በክብር
ዛሬም ለልጆቿ በረከቷ ይደር/2
/
#አዝ
እንደተናገረው ጌታችን በቃሉ
በእኔ የሚያምኑ ድንቅን ይሰራሉ
ደዌ እንዲርቅለት ፈውስን የተጠማ
ከደጇ ላይ ይውደቅ ይበላት አርሴማ/2/

           ሊቀ-መዘምራን
     ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
📣📣📣📣📣📣📣
📣#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ📣
📣📣📣📣📣📣📣




Репост из: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
🗓 ነገ ማለትም
#ዕለት:- ረቡዕ
#ቀን:- ታኅሣሥ ፪  ፳፻፲፯ ዓ.ም

በቅድስት ቤተክርስቲያናችን
ሐዋርያዉ ታዴዎስ ፣ ሠለስቱ መዕት ፣ ቅድስት አትናስያ ፣ አቡነ እንድርያኖስ ፣ ቅድስተ ዜና ማርቆስ ፣ አባ ጉባ

አክብረን እና አስበን እንውላለን።

📣📣📣
✔️ የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው። ምሳ ፲፤፯

✔️  መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል መዝ.፻፳፮፥፮


✔️ "ቅዱሳን በዓለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን? ፩ኛ ቆሮ ፮:፪

የመላዕክት ፣ የቅዱሳን ፣ የሰማዕታት ተራዳይነት እና በረከት ከሁላችንም ጋር ይሁን።

#ድምፀ_ተዋህዶ


Репост из: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
✨አንድ ትእቢተኛና ልብ አውልቅ ተማሪ
መምህሩን ሊሳለቅባቸው አሰበና "የኔታ ገሀነም በየት በኩል ነው ?"

አላቸው።የኔታም የውስጡን አውቀው "ልጄ እመንገዱህ ላይ ነህ ......"አሉት ይባላል

✨#ድምፀ_ተዋህዶ✨


Репост из: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
🗓ድጓ ከምን ያድናል❓🧠
አንድ መናፍቅ  ታላቁን የድጓውን መምህር የናቀ መስሎት "የኔታ ድጓ ከምን ያድናል "ሲል ጠየቃቸው እሳቸውም ቀበል አድርገው "እንዲህ ከማለት ያድናል" አሉት ይባላል።
↗️#ድምፀ_ተዋህዶ ↗️


Репост из: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
~ኅዳር 21~

እንኳን-ለቅድስት_ጽዮን_ድንግል_ማርያም አመታዊ በአል በሰላም አደረሳችሁ🙏🙏

  ~ኅዳር ሃያ አንድ ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች ~።

በዚህች_ቀን:-
✞ ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን።

✞ ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት በማሰብ።

✞ በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ። አገለገለ። ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ የተቀኘላት በማሰብ።

✞ ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተመቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ የቀደሙ ነብያት ስለእመቤታችን በተለያየ አምሳል ያዩበት ለምሳሌ፦ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ ቀዳማዊ ምኒሊክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገድ እስራኤል የበኩር ልጅ ጋር ሊቀ ካህናቱን  አዛሪያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች። በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታልና ይህንንም በማሰብ፤

✞ በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግስት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ አዋጅ የታወጀበትን በማሠብ፤

✞ አብርሃ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተ መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት በመሆኑ፤

✞ በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥል ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሀይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ፤

በእነዚህ ምክንያቶች በመላው ኢትዮጵያ በተለይም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን።

#ድምፀ_ተዋህዶ


Репост из: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
የቀድሞው ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ ወደ ቀደመው የአባቱ ቤት ወደሆነችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት መቅደስ ተመልሷል
***

በተ*ዶሶ እንቅስቃሴ ላይ የነበረው የቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዘማሪ የነበረው ሐዋዝ ተገኝ

ቀድሞ ያገለግልባት ወደነበረችው ቅድስት እና ንጽሕት ወደሆነችው ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ መቅደስ በንሰኃ ጥምቀት ተመልሷል።

እግዚአብሔር ይመስገን !!!

#ድምፀ_ተዋህዶ


Репост из: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
የበጎነት መልስ ከእርሱ ነው።
-
ከጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8.00 ሰዓት ጀምሮ  ባጋጠመኝ ድንገተኛ ህመም ምክንያት በሃሌ ሉያ ፣በቤጂንግ ፣በውዳሴ እና በዘበብ ሆስፒታሎች እኔ ለማትረፍ በተደረገው ህክምና ላሳችሁት በጎነት ከእኔ ከታናሹ የሚከፍላችሁ ምንም የለኝ በጎነታችሁን የማይረሳ እርሱ እግዚአብሔር ያክብሪልኝ እያልኩኝ ብፁዓን አባቶቼ እና ወዳጆቼ ሁላችሁም ያለማቋረጥ ስልክ ስትደውሉ የማነሳበት ሁኔታ ላይ ስላልነበርኩኝ ነው ይቅርታ እየጠየኩኝ ነገር ግን ጸሎታችሁ ደርሶልኝ ሃይል አገኝቻለሁ የልጄ አምላክ ረድቶኝ ቀና ብያለሁ።
-ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን።
መምህር ኤርምያስ ወ/ኪሮስ ከ ፌስቡክ ገፅ የተወሰደ


Репост из: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
ለመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት ድርጅት የተገነባው  ዘመናዊ ስቱዲዮ   በቅዱስ ፓትርያርኩ ተመረቀ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በማኅበራት ምዝገባና ቁጥጥር መምሪያ እውቅና የተሰጠው "ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር "ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ሥርጭት ድርጅት ያስገነባው ዘመናዊ ስቱዲዮ  በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት'  ቡራኬ ተመረቀ።
በመዝግጅቱ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ' የባሕርዳና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች ከመላው ዓለም ለ43ኛው ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባ የተሰባሰቡ ልዑካን ተገኝተዋል ።
ስቱዲዮው አንድ ዘመናዊ ስቱዲዮ ማሟላት የሚገባው ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያሟላ ሲሆን ግዙፍ 8k ስክሪን የተገጠመለት ሲሆን በተጨማሪም በስቱዲዮው የተለያዩ ቀረጻዎችን ማከናወን የሚያስችሉ ገጽታዎች እና የግንኙነት ካሜራ ተሟልቶለታል። የስቱዲዮ መቆጣጠሪያ ክፍል ያለው ሲሆን ግንባታው ባለፉት ከ2 ዓመታት በላይ የወሰደ ሲሆን ዘመናዊ መሣሪያዎች ከውጪ ሀገራት ተገዝተው ተገጥመውለታል።
በፍኖተ ጽድቅ ማኅበር መስራች መጋቤ አእላፍ ጸጋዬ ደበበ ሙሉ ወጪ የተገነባው ይኸው ስቱዲዮ ድርጅቱ በሚያሠራጫቸው ይዘቶች የፕሮዳክሽን ጥራት ለመጨመር ከፍተኛ አስተውጽኦ እንደሚያመጣ ተገልጿል።

#ድምፀ_ተዋህዶ


Репост из: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
እንኳን ለጻድቁ አባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደርሳቹ❗️

ጥቅምት 5-ኑሮአቸው እንደሰው ያይደለ በምድረ በዳ እንደመላእክት የኖሩትና በዝቋላ ተራራ ባለው ባሕር ውስጥ 100 ዓመት ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ሰዎች ምሕረትን የለመኑት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታላቅ ቃልኪዳን የተቀበሉበት ዕለት ነው፡፡ 

አባታችን አራት ሺህ እልፍ እየሰገዱ፣ 300 ጊዜ የቀኝ 300 ጊዜ ደግሞ የግራ ፊታቸውን በድንጋይ እየመቱ፣ መዝሙረ ዳዊትን እየደገሙ፣ 15ቱን መኅልየ ነቢያት፣ መኅልየ ሰለምንንና ውዳሴ ማርያም እየጸለዩ ለኃጥአን ምሕረትን ሲለምኑ ዕንባቸው እንደ ውኃ ይፈስ ነበር፡፡ ጌታችንም ‹‹በተወለድሁባት፣ በተጠመቅሁባትና ከሞት በተነሣሁባት ዕለት እልፍ እልፍ ነፍሳትን እምርልሃለሁ›› የሚል ቃል ኪዳን ሰጣቸዉ

አምላካችን በቃል ኪዳናቸው ይማረን


✝️#ድምፀ_ተዋህዶ ✝️


Репост из: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
“አሁን ባለን የአስተዳደር ክፍተቶችና በውስጣችን ያሉ ግልጽነት የጎደላቸው አሠራሮች ለአገልግሎታችን እንቅፋት እየሆኑብን ነው”ሲሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ገለጹ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት 43ኛው ዓለም አቀፍ መደበኛ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ለተገኙ ተሳታፊዎች መልእክት አስተላልፈዋል።

ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አሁን ባለን የአስተዳደር ክፍተቶችና በውስጣችን ያሉ ግልጽነት የጎደላቸው አሠራሮች ለአገልግሎታችን እንቅፋት እየሆኑብን ነው። በዚህ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን የሚታየውን  ችግር ለመፍታት በጥናት ላይ የተመሠረተ መፍትሔ ማምጣት ይገባል ሲሉ አፅዕኖት ሰጥተዋል፡፡

ቅዱስነታቸው ጨምረው እንደገለጹት ቅዱስ ሲኖዶስ ተግባራዊ እንዲሆን የወሰነውን የቤተ ክርስቲያን የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ ውጤታማ ለማድረግ ሁላችንም በትብብር መሥራት ይገባናል ብለዋል።

በዛሬው ዕለት የተጀመረው 43ኛው አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ከሀገር ውስጥ እና ውጪ ከሚገኙ አህጉረ ስብከቶች፣ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራት እና ገዳማት እንዲሁም ከተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራት የተወከሉ ተሳታፊዎች በተገኙበት እየተከናወነ ይገኛል።

#ድምፀ_ተዋህዶ


Репост из: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
"በሰማይ የምትኖር ሆይ፥ ዓይኖቼን ወደ አንተ አነሣሁ፤ እነሆ፥ የባሪያዎች ዓይኖች ወደ ጌታቸው እጅ እንደ ሆኑ፥ የባሪያይቱም ዓይን ወደ እመቤትዋ እጅ እንደ ሆነ፥ እንዲሁ እስኪምረን ድረስ፡ ዓይናችን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ነው'' መዝ. 122:1-3

#ድምፀ_ተዋህዶ

▫️https://t.me/dmtse_tewaedo



Показано 19 последних публикаций.