Addis Maleda - አዲስ ማለዳ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


ዜና ከምንጩ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ቀውስ እያስተናገዱ ያሉ ጦርነቶች አሁንም መፍትሄ እያገኙ አይደለም።

በክልሎቹ የሚፈጸሙ ከህግ፣ ከሞራልና ከሰብአዊነት የተፋቱ አያሌ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፤ የሚሊዮኖች ህይወት በሰቆቃ ውስጥ እንዲያልፍ እያደረገ ይገኛል፡፡

በዚህ አስከፊ ሁኔታ ውስጥ የመንግስት ምላሽ እንዴት ይታያል? የፖለቲካ ሊህቃንስ ምን ይላሉ? የሚሉና መሰል ጉዳዮችን ያነሳንበት አዲስ ማለዳ የትንታኔ ፕሮግራማችንን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ፡፡

https://youtu.be/-w_gklkCjZA


“ለነዳጅ ማስገቢያ የሚውል የውጭ ምንዛሬ የንግድ ባንኮችን እንዲሰጡ ማድረግ ከሌለ ሀብት ላይ እንደመውሰድ ይቆጠራል”- የፋይናስ ባለሙያ

👉 “ለነዳጅ ማስገቢያ የሚውል የውጭ ምንዛሬ የግል ባንኮች ላይ የሚያመጣው ምንም አይነት ተጽዕኖም ሆነ ጉዳት የለም” የምጣኔ ሃብት ባለሙያ

ሀሙስ ህዳር 12 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከህዳር ወር ጀምሮ የንግድ ባንኮች ለነዳጅ የሚወጣውን ወጪ ከፍተኛ ድርሻ መጋራት አለባቸው ሲል ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡

ኢትዮጵያ በአመት ከፍተኛ ወጪ ለነዳጅ ማስገቢያ ይወጣል በዚህም በባለፈው አመት የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በአጠቃላይ ከ64ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ማውጣቱን ገልጾ እንደነበር እንዲሁ ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም የዘርፉ ባለሙያዎች በርካታ ሀሳቦችን እየሰጡ ሲሆን ለባንኮች ከፍተኛ ጫና እንሚፈጥርባቸው እና በቂ ጥናት ሳይደረግ የተወሰነ ውሳኔ እንደሆነ የሚከራከሩ እንዳሉ ሁሉ ይህ ነው የሚባል ችግር አያመጣም የሚሉም አልጠፉም ፡፡

አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የባንክ ባለሙያው ሙሀመድ አሰፋ እንደገለጹት በርካታ ባንኮች አሁን ያሉበት ሁኔታ ደንበኞቻቸውን እንኳን በበቂ ሁኔታ የሚያስተናግዱበት አቅም ላይ አይደለም ያሉት ይላሉ፡፡

“ባንኮች በበቂ ሁኔታ የተጣለባቸውን ውሳኔ ሊያሟሉ የሚችልበት አቅም ሳይጠና እና ምን ያህል ድርሻ አስተዋጽኦ ሊያደርጉ እንደሚገባ ግልጽ ባልሆነበት መንገድ ውሳኔ ማስተላለፍ ባንኮች አሁን ካሉበት ሁኔታ ጋር ተመጣጣኝ ያልሆነ ውሳኔ ነው” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ወደ ውጪ የመላክ እና የውጭ ምንዛሬ የመሰብሰብ አቅም እየተዳከመ ያለበት ሁኔታ መሆኑ በተጨማሪም በየጊዜው የሚወጡ መመሪያዎች የባንኮችን እንቅስቃሴ የሚገድቡ መሆኑ ሁኔታውን እንደሚያባብሰው አስታውቀዋል፡፡

በእነዚህ ችግሮች እና ብዙ መስተካከል ባለባቸው ክፍተቶች ውስጥ ይህን ውሳኔ ተግባራዊ ማድረግ እና ባንኮች ግዴታ ለነዳጅ ማስገቢያ የውጭ ምንዛሬ ለነዳጅ አስገቢዎች እንዲሰጡ ማድረግ ከሌለ ሀብት ላይ እንደመውሰድ ይቆጠራል በማለት ገልጸዋል፡፡

ውሳኔው ከፍተኛ የገቢ አቅም እና በኢኮኖሚ ልማት ውስጥ ሚና የሚሰጥ ቢሆንም ከውጭ ምንዛሬ ዋጋ ተለዋዋጭነት እና ከአሰራር ውስብስብነት ጋር የተያያዙ ስጋቶችንም እንደሚያስከትል ተጠቁሟል፡፡

በአንጻሩ በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዮናታን ታደሰ የግል ባንኮች ለነዳጅ ማስገቢያ የውጭ ምንዛሬን ማዋጣታቸው ይህ ነው የሚባል ተጽዕኖም ሆነ ጉዳት የለውም ሲሉ ይሞግታሉ፡፡

“የግል ባንኮች ላይ ያለው የውጭ ምንዛሬ ፍሰት ምን አይነት እንደሆነ ሀገር የሚያውቀው ሚስጥር ነው፤ መንግስትም ይህን ስለሚረዳ ነው ይህን ውሳኔ ያስተላለፈው” ሲሉም ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም ሙሉ ለሙሉ እንዲሸፍኑ ሀላፊነት አልተጫነባቸውም እንዳላችሁ ሀብት እና አቅም አስተዋጽኦ አድርጉ ነው የተባሉት ይህ ሂደት ደግሞ ይበልጥ የሚሳተፉበትን መንገድ ስለሚያሰፋው በነጻነት እንዲሳተፉ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ባለሙያው አክለውም ውሳኔው ይተላለፍ እንጂ በምን መልኩ አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ በግልጽ ባልተጠቀሰበት ሁኔታ ጫና ሊያሳድር ይችላል ብሎ መደምደም እንደማይቻል እና ለባንኮቹም በሚመች መልኩ የሚሳተፉበት ሁኔታ ሊቀርብ እንደሚችል ታሳቢ መሆን እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም የአሰራር ችግር እንዳለ እና የውጭ ምንዛሬ እጥረት ሙሉ ለሙሉ የለም ማለት ሳይሆን እንደሚባለው የተጋነነ እንዳልሆነ እና ከሙስና በጠራና በትክክለኛ መንገድ መስራት ቢቻል ክፍተቱን መሙላት እንደሚቻል ባለሙያው ገልጸዋል፡፡




"አንዳንድ ተቋማት ላይ ሰራተኞቻችን ወረፋ ሲይዙ በጥበቃ ሰራተኞች የተደበደቡበት፣ ተገፍትረው የተጣሉበት፣ የታሰሩበት ሁኔታ ተፈጥሯል።" የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን

ዓርብ ህዳር 13 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የአገልግሎት አሰራሩን ለመገምገም እንዲያመች በተሰራው ስራ የተቋማቸው ሰራተኞችን ጨምሮ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተለያዩ እንግልቶችን እንዳሉ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ገልቷል።

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነሩ መኩሪያ ሃይሌ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የኢትዮጲያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እና በስሩ የሚገኙ ቋሚ ተቋማትን የ2017 በጀት ዓመት፣ የሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም በተገመገመበት ወቅት ነው ይህን ጉዳይ ያነሱት ።

ኮሚሽነሩ በኢትዮጵያ በክልሎች እና የመስሪያ ቤት አመራሮች ምንም አይነት መረጃ ሳይኖራቸው በሚንቀሳቀሱ ባለ ድርሻ አካላት፣ የኮሚሽኑ የአቃቤ ህግ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት እና ሌሎችም መዋቅሮች በተካተቱበት በሁሉም ክልሎች ተገልጋይ ተኮር ጥናት መደረጉን ገልፀዋል።

በጥናቱም ጥልቅ ጉዳዮችን ለመረዳትና የበለጠ በማስረጃ የተደገፈ እና አንዳንድ ተቋማት ላይ የኮሚሽኑን ሰራተኞች ጨምሮ ወረፋ ሲይዙ በጥበቃ ሰራተኞች የተደበደቡበት፣ ተገፍትረው የተጣሉበት እና የታሰሩበት ሁኔታ መፈጠሩን አስታውቀዋል።

በበጀት ዓመቱ የሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ወቅት የተገኙ በኢትዮጲያ ሲቫል ሰርቪስ ስር ከሚገኙ ተቋማት ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን፣ በዋነኝነትም የመንግስት ሰራተኞች የክፍያ ማትጊያ እና ማበረታቻ ስርዓት ከመዘርጋት አኳያ ጥናት ለማካሄድ እና ማበረታቻ ሊያገኙ የሚችሉ ጉዳዮችን ለመለየት ታቅዶ ያልተተገበረበት ምክንያት ጥያቄ አስነስቷል።

ኮሚሽነሩም "በቅርቡ የገንዘብ ሚኒስትር ያሳወቀውን የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ማስተካከያ በማስታወስ የተደረገው የደሞዝ ማስተካካያ ትልቅ እረፍት ይሰጠናል። ኢትዮጵያ የሚመጥናትን የመንግስት ሰራተኛ ሊኖራት ይገባል። ለዚህም ብቃት ወሳኝ ነው። በዚህ ሂደት ጠንክሮ የሚወጣ ይኖራል የሚንገዋለልም እንደሚኖር ታሳቢ ማድረግ ይኖርብናል። ይሁን እንጂ ከፊት ለፊታችን ትልቅ ፈተና እንዳለ መረዳት አለብን" ብለዋል።




#ማስታወቂያ


የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ ካርድ መታገዱ ተሰማ

ዓርብ ህዳር 13 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የሲቪል ማህበረስበ ድርጅቶች ባለስልጣን በሰብአዊ መብት ሥራዎች ታዋቂ የሆኑ ድርጅቶችን በደብዳቤ ማሸጉን አስታውቋል::

መንግስት ካገዳቸው የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ውስጥ “የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) እና ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ እንደሚገኙበት ተጠቁሟል፡፡

የሲቪል ማህበረስበ ድርጅቶች ባለስልጣን  ባለፈው ሳምንት መጨረሻ እና በዚህ ሳምንት ለድርጅቶቹ በተናጠል በላከው ደብዳቤ፣ ድርጅቶቹ ከማንኛውም እንቅስቃሴ መታገዳቸውን አመላክቷል፡፡

ባለስልጣኑ ለእገዳው እንደምክንያት ያቀረበው  የመብት ተቋማቱ ከፖለቲካ ገለልተኛ ሆኖ መሥራት ሲገባቸው ከዓላማው ውጭ በመንቀሳቀስ የአገርና የህዝብ ጥቅምን የሚጎዱ ተግባራት ላይ በመሰማራታቸውና  ከባድ የህግ ጥሰት መፈጸሙን ካረጋገጠ በኋላ እግድ እንዳሳለፈ ዋዜማ ዘግቧል፡፡


የተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት የሳፋሪኮምን የስራ እንቅስቃሴ ገመገሙ

ሐሙስ ህዳር 12 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በዛሬው እለት የተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን አጠቃላይ የስራ ሂደት እና አፈጻጸም ገምግመዋል።

በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና መስሪያ ቤት በተካሄደው በዚህ ፕረሮግራም ላይ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዊም ቫንሄልፑት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመሆኑም ላለፋት ሶስት አመታት ከ6ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ማፍራት መቻሉን እና በ9 የክልል ከተሞች አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ዋና ስራ አስፈጻሚው አስታውቀዋል።

እንዲሁም በኤም ፔሳ የሞባይል ግብይት ከበርካታ ባንኮች ጋር በጋራ በመስራት ላይ መሆኑን እና በተለያዩ አካባቢዎች ለመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የትምህርት መሳሪያ መስጠታቸውን ለምክርቤት አባላቱ ገልጸዋል።

በተጨማሪ ጉልህ የገበያ ሀይል ወይም አንድ የሳፋሪኮም ደንበኛ ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ተጠቃሚ ጋር ለመደወል ተጨማሪ ክፍያ እንዳይከፍል ለማስቻል እንዲሁም ለማስፋፊያ እና የግንባታ ፍቃድ ላይ ከምክር ቤቱ ድጋፍ ተጠይቋል።

የምክር ቤቱ አባላትም በቀረበው ሪፖርት ላይ ሀሳብ አስተያየት ካነሱ በኋላ ለተጠየቀው የድጋፍ እና የፍቃድ ጥያቄ ተወያይተው ምላሽ እንደሚሰጡ ገልጸዋል፡፡


በደራ ወረዳ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ከ43 በላይ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸው ተገለጸ

ሀሙስ ህዳር 12 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ በአንድ አመት ውስጥ ብቻ በታጣቂዎች ግጭት 43 ነዋሪዎች ህይወታቸው ማለፉ ተነግሯል፡፡

በተደጋሚ የሰላ እጦት የሚያጋጥማት ወረዳዋ በተለይም የታጠቁ ሃይሎች በሚያደርሱት ዝርፊያና የንብረት ውድመት ምክንያትም ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደገባች ተደጋግሞ ይገለጻል፡፡

በተለይም ከ2015 በኋላ በመንግስት ሃይሎች፣ መንግስት ኦነግ ሸኔ ብሎ በሚጠራው አካል እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተደረጉ ከፍተኛ ውጊያዎች ወረዳዋን ወደ አሳዛኝ የግጭት ማዕከልነት ቀይሯታል፤ በዚህም የበርካታ የአከባቢው ነዋሪዎች ህይወት ተቀጥፏል፣ ማህበረሰቡን ለከፍተኛ ቀውስ ዳርጓል።

ከሰሞኑም በወረዳዋ አንድ ወጣት በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደል የሚሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ወጥቶ በብዙዎች ዘንድ ቁጣ መቀስቀሱ አይዘነጋም ፡፡


የትግራይ ክልል የፖለቲካ ውዝግብ ከሁለቱ ተፋላሚዎች ባለፈ የክልሉን ሊህቃን ለሁለት የከፈለ ሆኗል፡፡

የህዝቡን እሮሮ ለመስማት አለመፍቀድ ፣የስልጣን ሽኩቻ ውስጥ መግባትና መሰል ሂደቶችን ማስተናገድ የክልሉ ነባራዊ ሃቅ ከሆነም ሰነባብቷል፤ የሚሉት አቶ ክብሮም በርኸ በክልሉ ያለው ቀውስና እያጋጠመ ያለውን ፖለቲካ ውድቀት በሚመለከት ከትዝብታቸው አጋርተዋል፡፡

ሙሉ ቃለ-ምልልሱን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ
https://youtu.be/pe-OjWSO2jk?si=1-aD15_hy2rYnrXr


"የመንግስት ተቋማት ፊት ለፊት የሚገኙ የመርካቶ ነጋዴዎች ላይ ብቻ ነው ቁጥጥር ያደረጉት” ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ማክሰኞ ህዳር 10 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የመንግስት ተቋማት ቁጥጥራቸውን ፊት ለፊት የሚገኙ የመርካቶ ነጋዴዎች ላይ ብቻ ማድረጋቸውን እንደ ትልቅ ክፍተት አግኝተነዋል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

ከንቲባዋ ይህን ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አራተኛ ዓመት የስራ ዘመን፣ አንደኛ መደበኛ ጉባኤ የበጀት ዓመቱን የሶስት ወራት የስራ አፈፃፀም በቀረበበት ወቅት ነው።

በጉባኤው በዋነኝነት ጥያቄ ካስነሱ ጉዳዮች መካከልም፣ በመርካቶ ገበያ ከሰሞኑ በደረሰኝ ከመገበያየት ጋር የተነሱ አለመግባባቶች ነበር።

ከንቲባዋ መርካቶን ዳግም ለማልማት ከመነሳታችን በፊት የተለያዩ ጥናቶች አከናውነናል ያሉ ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ መርካቶ የሀገሪቱ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ ከመሆኑ ጀርባ የህገ ወጥ ንግድ መሸሸጊያ ሆኖ በማግኘታችን ነው ብለዋል።

ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት የመንግስት ተቋማት ቁጥጥራቸውን ፊት ለፊት የሚገኙ የመርካቶ ነጋዴዎች ላይ ብቻ ማድረጋቸው እንደሆነ ነው የጠቆሙት።

" ሲነጋ ግብረ ሐይሎች እንዳያገኘን በሚል፣ በሌሊት ትልልቅ ተሸከርካሪዎች ተሰልፈው እቃ ጭነው ለመሄድ ጥረት ይደረጋል። ይህ ሀገርን ይጎዳል። ግብር መክፈል መርህ እስከሆነ፣ ችግሮቻችንን እያሳዩን እና የሚሰርቀውን ለእኛ አሳልፈው እየሰጡ እነርሱም ግድታቸውን መወጣት ነው ያለባቸው።" ሲሉ አስጠንቅቀዋል


ሲቪል ሰርቪስ በአንድ ብሔር ቁጥጥር ስር ነው መባሉን እና በፌዴራል የመንግስት መስሪያ ቤቶች ኢትዮጵያን የሚመስል የሰራተኞች ድልድል እንዲኖር በረቂቅ አዋጅ መቅረቡ ትክክል አይደለም ሲሉ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በፓርላማ ሰፊ ክርክር አድርገዋል፡፡

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ከዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ጋር በፓርላማ ያደረጉትን ፍጥጫ ከስር ባለው መስፈንጠሪያ ተጠቅመው በአዲስ ማለዳ ይከታተሉ

https://youtu.be/RzdONqXRWUE?si=QnxYL1re4_0Ah4Ik






በትግራይ ክልል አለ የተባለው አለመረጋጋት ሰዎች ወደ ክልሉ እንዳይመጡ ሆን ተብሎ የሚደረግ ሴራ ነው ተባለ

ማክሰኞ ህዳር 10 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በትግራይ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ተኩስ ተከፍቶ እንደነበር እና አለመረጋጋት መኖሩን በተለያዩ የማህበራዊ ድህረገጾች እና የዜና ምንጮች ሲነገር መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በተለይም በትግራይ ክልል የማዕከላዊ ዞን አስተዳዳሪ ሰለሞን መዓሾ ባሳለፍነው እሁድ ማለትም ህዳር 08 ቀን 2017 ከአክሱም ወደ መቀሌ እየተጓዙ ባሉበት ወቅት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተኩስ እንደተከፈተባቸው መግለጻቸው ይታወቃል፡፡

መኪናቸው ላይ ተኩስ እንደተከፍተባቸው የገለጹት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ከአክሱም ወደ መቐለ ሲመለሱ ማይቅነጣል ፈላፍል በተባለ ቦታ ሲደርሱ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በተሽከርካሪ ውስጥ እሳቸውን ጨምሮ ሶስት ሰዎች እንደነበሩ እና በማንም ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም ተኩሱን የከፈቱባቸው አካላት እነማን እንደሆኑ ኮሚቴ ተቋቁሞ እንዲጣራላቸው ለክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር ጥያቄ ማቅረባቸውን አሳውቀዋል፡፡

አስተዳዳሪው ከትግራይ ክልል አመራር መከፋፈል በኋላ በአቶ ጌታቸው ረዳ ከሚመራው 16 ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዱ ሆነው የቀጠሉ ናቸው፡፡

በአንጻሩ የመግደል ሙከራ ተቃጥቶባቸዋል የተባለው አካባቢን የሚያስተዳድሩት አቶ ገብረ ተክለሃይማኖት በበኩላቸው “በማይ ቅነጣል ወረዳ ጉዳዩ አልተፈፀመም፤ መረጃው ከእውነት የራቀ ነው” ብለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በክልሉ ያለው እንቅስቃሴ ምን ይመስላል ስትል አዲስ ማለዳ በአካባቢው ከሚኖሩ ምንጮች መረጃውን ለማጣራት የሞክራች ሲሆን እነዚህ ምንጮች በማዕከላዊ ዞን አስተዳዳሪዉ አቶ ሰለሞን መዓሾ መኪና ላይ ተኩስ መከፈቱን መስማታቸውን ጠቅሰዉ ከዚህ ውጪ በተለያዩ ማህበራዊ ድህረገጾች እንደሚናፈሰው በክልሉ ሁከትም ሆነ የተለየ ተኩስ አለመኖሩን ገልጸዋል፡፡

በትግራይ ክልል በድምቀት የሚከበረውን አመታዊ የፂዮን ማርያም ሀይማኖታዊ ክብረ በዓልን ተከትሎ እና ከሰሞኑ በነበሩ ዝግጅቶች ምክንያት ከተለመደው በዛ ባለመንገድ የፖሊስ ሀይሎች በአካባቢው ላይ ከመታየታቸው ውጪ ምንም አይነት አዲስ ነገር እንደሌለ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተጨማሪም በዓሉን ተከትሎ በርካታ ሰዎች ከተለያዩ ክልሎች እና አካባቢዎች የሚመጡ ስለሆነ እና አንደኛው የቱሪስት መስህብ በመሆኑም ባልተረጋገጠ መረጃ ሆንተብሎ ሰዎችን ለማስቀረት የሚደረግ ሀሰተኛ መረጃ ስለመሆኑም የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡











Показано 20 последних публикаций.