"የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ለማፍረስ ወሰነናል መባሉን አውግዘናል"- ፓርቲዎች
ቅዳሜ ጥር 17 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)ዓረና ትግራይ፣ የትግራይ ነጻነት ፓርቲና ባይቶና በጋራ ባወጡት መግለጫ የትግራይ ጸጥታ ኃይሎች የተወሰኑ አዛዦች ጊዜያዊ አስተዳደሩን ለማፍረስ ወሰነናል ማለታቸውን አውግዘዋል፡፡
ፓርቲዎቹ የአዛዦቹ መግለጫ ሥልጣን የመቆጣጠር ወይም ሥልጣን ለሚፈልግ ኃይል ሥልጣን አሳልፎ የመስጠት እንቅስቃሴ ነው በማለት ተቋውሞአቸውን ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ ሳልሳዊ ወያኔ በተናጥል ባወጣው መግለጫ የጸጥታ ኃይሉ አዛዦች ለአንድ የፖለቲካ ቡድን በመወገን የጊዜያዊ አስተዳደሩን ሥልጣን "በኃይል ለመንጠቅ" ሙከራ አድርገዋል በማለት በጽኑ አውግዟል።
ፓርቲው ይሄ አካሄድ የትግራይ ሕዝብ አጣዳፊ የሆኑትን የሰላም አካታች ሲቪል አስተዳደር የመመስረት የቅድመ-ጦርነት አስተዳደራዊ ወሰኖችን የማስመለስና ስደተኞችንና ተፈናቃዮችን ወደቀያቸው የመመለስ ዓላማዎችን አደጋ ላይ ይጥላል ብሏል።
ፓርቲው በትግራይ ለተፈጠሩት ችግሮች ዘላቂው መፍትሄ በፖለቲካ ፓርቲ ሽኩቻ ውስጥ ራሱን የማያስገባ ኹሉን አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር እንደገና ማቋቋም እንደሆነም ጠቁሟል።
በአንጻሩ ጥር 15ቀን 2017 ዓ.ም " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠውን መግለጫ የሚቃወም መግለጫ አውጥቶ እንደነበር ይታወሳል።
"የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን" በሚል ያወጡት መግለጫ የ " ነሃሴው ህወሓት ህዝቡን እና ሰራዊቱ ለመበታተነ የሰራው ክፋት ውጤት ነው " በማለት የገለጸ ሲሆን " የነሃሴው ህወሓት ህዝብን እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ያልተቀበለው ጉባኤ በማካሄድ ነባሩን ህወሓት እንዲዳከም ሰርቷል " ሲል በአቶ ጌታቸው የሚመራው ህወሓት ፤ " ወታደራዊ አምባገንነት ታግሎ ዴሞክራሲያዊ እና ህዝባዊ መንግስት የጨበጠ ህዝብ ወደ ኋላ አይመለስም " ብሎ ነበር፡፡