በትግራይ ክልል የወንጀል ድርጊት በ68 በመቶ መጨመሩ ተገለጸ
ሐምሌ 19 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ እየተፈጸሙ ያሉ ህገወጥ ድርጊቶችና የወንጀል ተግባራት ከባለፈው ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነጻጸሩ በ68 በመቶ መጨመራቸው ተገልጿል፡፡
የመቀሌ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ በሪፖርቱ እንዳስታወቀው በዚህ ዓመት የተፈጸሙ ወንጀሎች ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸሩ በአንድ ሺህ ስምንት መቶ አርባ አንድ አሃዝ ብልጫ አሳይተዋል፡፡
የቢሮ ምክትል ሃላፊ ኢንስፔክተር ገብረጨርቆስ ገ/መስቀል ባለፈው ዓመት በከተማዋ የተፈጸሙ የወንጀል ድርጊቶች አሃዝ 2 ሺህ 8 መቶ 95 የነበረ ሲሆን በተያዘው ዓመት ግን ወደ 4 ሺህ 7 መቶ 35 ማሻቀቡን ነው በማብራሪያቸው የጠቆሙት፡፡
የከተማዋ ከንቲባ ይትባረክ አምሃ በበኩላቸው አሁን ላይ በከተማዋ ከሚታየው የሰላምና ጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ከፍተኛ በጀት በመመደብ የህግ ማስከበር ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን በመግለጽ ይህ ግን ሊሳካ የሚችለው የህዝቡ ድጋፍ ሲታከልበት ነው ብለዋል፡፡
ከድህረ ጦርነት ማግስት ግድያ፣ እገታና መሰል ወንጀሎች የተበራከቱበት የትግራይ ክልል ከፍተኛ በተባለ የሰላም እጦት ውስጥ እንዳለ የሚታወቅ ነው፡፡
ከሰሞኑም የክልሉ መንግስት ባወጣው መግለጫ እየተተገበሩ ያሉ የህግ ማስከበር ተግባራትን ፖለቲካዊ አውድ ለመስጠት የሚሞክሩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሲል ማስጠንቀቁ የሚታወስ ነው፡፡