የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ከ200 በላይ ስማርት ቅርንጫፎችን በመላ ሀገሪቱ በመክፈት ወደ ዲጂታል ባንክ መሸጋገሩን አስታወቀ፡፡
ዕረቡ ጥቅምት 20 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ባንኩ ያስተዋወቀው አዲሱ አገልግሎት ደንበኞች ከወረቀት ንክኪ ነጻ በሆነ መንገድ ለዚህ አገልግሎት የተዘጋጁ ታብሌቶችን በመጠቀም አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል ነው።
በባንኩ ስማርት ቅርንጭፎች ወረቀት ላይ መሰረት ካደረገው ልማዳዊ አሠራር ወጣ ባለ አኳኋን፣ እንደ ገንዘብ ማስገባት፣ ማስወጣትና ማስተላለፍ ያሉ አገልግሎቶችን ደንበኞች ዲጂታል በሆነ መንገድ ማግኘት የሚችሉበትን አሠራር እንደሆነም ገልቷል፡፡
ከ 13 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ያሉት ባንኩ የዲጂታል አገልግሎቱን ለማሳደግና በዲጂታል ፈጠራ ልቆ ለመገኘት በርካታ በፈጠራ የታገዙ አገልግሎቶችን ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ለመድረግ በዲጂታሉ መስከ እየሰራ እንደሚገኝም ገልቷል፡፡
ባንኩ በሀገር ውስጥ በዲጂታል ወደፊት በመቅደም የደንበኞችን ተደራሽነትና እርካታ በመጨመር አካታች የፋይናንስ አገልግሎት ሥርዓትን በመፍጠር ላይ እገኛለውም ብሏል፡፡