የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ከጃል ሰኚ ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ
እሁድ ህዳር 22 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የነበሩት ጃል ሰኚ ነጋሳ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ የሰላም ስምምነት ስለመፈራረማቸው አዲስ ማለዳ ሰምታለች።
ጃል ሰኚ ነጋሳ መንግሥት ያቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ነው ከአቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር የሰላም ስምምነቱን የፈረሙት ተብሏል፡፡
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት÷ የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለመጡት ምስጋና ማቅረባቸው ተሰምቷል።