“መንግስት የመብት ጥሰት የፈጸሙትንም ሆነ ያስፈጸሙትን መጠየቅ ይኖርበታል” ኢሰመኮ
አርብ ጥር 16 ቀን (አዲስ ማለዳ) መንግሥት በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች በመካሄድ ላይ በሚገኙት የትጥቅ ግጭቶች፣ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊነት ሕጎች ጥሰት የፈጸሙ እና ያስፈጸሙ ኃላፊዎችን እና አባላትን እንዲሁም የታጣቂ ቡድኖች አባላት ተጠያቂ ለማድረግ መንቀሳቀስ ይኖርበታል ሲል ኢሰመኮ አሳስቧል፡፡
የሰብአዊ መብቶች ደረጃን የሚያሟላ የወንጀል ምርመራ እና የክስ ሂደት እንዲጀመር፤ እንዲሁም በግጭቶቹ በሰው ሕይወት፣ በአካል፣ በሥነ-ልቦና እና በንብረት ላይ ያደረሱትን ጉዳት በማጣራት ተጎጂዎች እንዲካሱ እና መልሰው እንዲቋቋሙ እንዲያደርግ ሲል ኮሚሽኑ በመግለጫው ጠይቋል፡፡
በአማራና በኦሮሚያ ክልል “ከወቅታዊ ጉዳዮች” ጋር በተያያዘ በሚል የተያዙና ተአማኒ ክስ ያልቀረበባቸው ታሳሪዎች እንዲሁም በማስገደድ የተሰወሩና ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ የታሰሩ ሰዎች ሁሉ በአፋጣኝ ከእስር እንዲለቀቁ ወይም ጉዳያቸው በመደበኛው የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት እንዲታይ፣ የመንግሥት የጸጥታና የአስተዳደር አካላት በቁጥጥር ሥር የሚውሉ ሰዎችን በመደበኛ ማቆያዎች ብቻ እንዲይዙና የተያዙ ሰዎች ያሉበት ቦታና ሁኔታ ለቤተሰቦቻቸው እንዲገለጽም ብሏል፡፡
ከዚህ ባለፈም የታጠቁ ቡድኖችን ጨምሮ በ3ኛ ወገኖች ከእገታ ጋር በተያያዘ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ፣ከዳኝነት ስራቸው ጋር በተያያዘ ያለፍርድ የታሰሩ ዳኞችና መሰል የፍትህ አካላትም በአፋጣኝ ፍትህ እንዲያገኙ ሲል ጠይቋል፡፡