በተውሂድ ብትፀና ምንም ቢያምር ስራህ
አትዘንጋ ልመና እዝነቱን ከጌታህ
አማላጅ ያሻሃል ነገር ሊገራልህ
የነቢዩንﷺ ምልጃ እንዲያጎናፅፍህ
ከወዲሁ ለምነው ተግተህ በሱጁድህ
① ነቢዩﷺ ለኡመታቸው ሻፊዕ ወይም አማላጅ ሆነው ጌታቸው አላህን እንዲማፀኑት የተፈቀደላቸው የምልጃ ዓይነቶች በርካታ ናቸው። ከነዚያ መካከል ሌሎች ሙእሚኖችና ሷሊሆች የሚጋሩት ያለ ሲሆን ለርሳቸው ብቻ የተሰጡ የሸፋዓ ወይም የምልጃ ዓይነቶች ኣሉ።
እነርሱም:-
አንደኛው:-
"ሸፋዐቱል ዑዝማ" ወይም ታላቁ ምልጃ በመባል የሚታወቀው የምልጃ ዓይነት ነው።
ይህ የምልጃ ክስተት ነገ የቂያሙ ዕለት ሰዎች ሁሉ በፍርዱ ሜዳ ተገኝተው ፍርድ እንዲሰጣቸው ሲጠባበቁና ፀሃይ በስንዝር ርቀት ቀርባ እንደየወንጀላቸው በላቦቻቸው ተጠምቀው መከራቸውን ሲያዩ ጌታቸው አላህ ከዚያ እንግልት ይገላግላቸው ዘንድ አላህን እንዲማፀኑላቸው ነቢያችንንﷺ ሲለማመጡ እሳቸውም አለይሂ አሰላቱ ወሰላም እንዲያማልዱ ተፈቅደላቸውና ለጌታቸው አላህ ሱጁድ ወርደው ሲለምኑት ጥያቄያቸው ምላሽ ያገኘበት የምልጅ ክስተት ነው።
ይህንኑ ክስተት አላሁ ሱብሃነሁ ወተዓላ በ"ሱረቱል ኢስራእ: 79" ላይ ጠቁሞታል።
ሁለተኛው:-
ማንኛው ሰው በስራው ብቻ ጀነት አይገባምና ለጀነት የሚያበቃ እድል ያገኙ ሰዎች ባጠቃላይ የመግቢያ ፈቃድ ያስፈልጋቸዋልና ነገ የቂያም ዕለት የጀነት ሰዎች ወደ ጀነት ይገቡ ዘንድ አላህ እንዲፈቅድላቸው አላህን የሚማፀኑበትና የሚለምኑበት የምልጃ ዓይነት ነው።
ሶስተኛው:-
ነቢዩﷺ ለካፊሩ አጎታቸው ለአቡጣሊብ አማላጅ ሆነው በኩፍሩ ሰበብ ይቀጣበት የነበረውን የእሳት ቅጣት ለሳቸው ባደረገው ወገኝተኘነትና ድጋፍ ሰበብ ቀነስ እንዲደረግለት የተወሰነበት ክስተት ነው።
እነዚህ ሶስቱ የምልጃ አይነቶች ለነቢያችንﷺ እንጂ ለማንም የተፈቀዱ አይደሉም።
[AhmedSiira: Feb 02/2007]
Edited & posted: 08/01/24