በአላህ ስም እጅግበጣም አዛኝ በሆነ እጅግ በጣም መሀሪ በሆነ
ከሰማይ የወረዱ ሰማያውያን መፅሃፍ
በጥራዝ መልክ የሚገኙ መፅሃፍት
የተከበረው ቁርኣን.. የመጨረሻው መፅሃፍ
የተውራት /ኦሪት/ መበረዝ
የኢንጂል /ወንጌል/ መበረዝ
የተከበረው ቁርኣን የቀደሙትን መፅሃፎች እውነትነት ስለማረጋገጡ
ወደ እውነት የሚያደርሰው መንገድ
ከሰማይ በወረዱት መፅሃፍት ማመን (አል-ኢማን ቢኩቱብ አስ-ሰማዊያ) ከስድስቱ የእምነት ምሶሶዎችን (አርካን አል-ኢማን) ውስጥ በሶስተኛ ደረጃ የተጠቀሰ ነው። በዚህ ጽሁፍ ይህንን አበይት የእምነት ክፍል በዝርዝር እንመለከታለን።
አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ወደ መልእክተኞቹና ነቢያቶቹ ወህይ ያደረጋቸው /በራእይ የገለፀላቸው/ የሆኑ ምክሮችና ትምህርቶች አሉ። ከነኚህም መካከል በመፅሀፍ መልክ የተጠረዙ ያሉ ሲሆን ከነኚህም ውጭ እኛ የማናውቃቸው የሆኑ አሉ። ሁሉም ነቢይ የተላከበትን መልእክት ወደ ህዝቦቹ አድርሷል። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ
كَانَ النَّاسُ أُمَّةً وَاحِدَةً فَبَعَثَ اللَّهُ النَّبِيِّينَ مُبَشِّرِينَ وَمُنْذِرِينَ وَأَنْزَلَ مَعَهُمُ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ لِيَحْكُمَ بَيْنَ النَّاسِ فِيمَا اخْتَلَفُوا فِيهِ [٢:٢١٣]
“ሰዎቹ ሁሉ አንድ ሕዝብ ነበሩ፤ (ተለያዩ)። አላህም ነቢያትን አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች አድርጎ ላከ። ከእነርሱም ጋር መጻሕፍትን በሰዎቹ መካከል በዚያ በርሱ በተለያዩበት ነገር ይፈርድ ዘንድ በእውነት አወረደ።” (አል-በቀራህ 2፤ 213)
فَإِنْ كَذَّبُوكَ فَقَدْ كُذِّبَ رُسُلٌ مِنْ قَبْلِكَ جَاءُوا بِالْبَيِّنَاتِ وَالزُّبُرِ وَالْكِتَابِ الْمُنِيرِ [٣:١٨٤]
“ቢያስተባብሉህም ከአንተ በፊት በግልጽ ተዓምራትና በጽሑፎች፣ በብሩህ መጽሐፍም የመጡት መልክተኞች በእርግጥ ተስተባብለዋል።” (ኣሊ ዒምራን 3፤ 184)
በጥራዝ መልክ የሚገኙ መፅሃፍት
1. በነቢዩ ሙሣ (ዐ.ሠ) ላይ የወረደው ተውራት /ኦሪት/
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ
إِنَّا أَنْزَلْنَا التَّوْرَاةَ فِيهَا هُدىً وَنُورٌ يَحْكُمُ بِهَا النَّبِيُّونَ الَّذِينَ أَسْلَمُوا لِلَّذِينَ هَادُوا وَالرَّبَّانِيُّونَ وَالأَحْبَارُ بِمَا اسْتُحْفِظُوا مِنْ كِتَابِ اللَّهِ وَكَانُوا عَلَيْهِ شُهَدَاءَ [٥:٤٤]
“እኛ ተውራትን በውስጥዋ መምሪያና ብርሃን ያለባት ስትኾን አወረድን። እነዚያ ትዕዛዝን የተቀበሉት ነቢያት በእነዚያ አይሁዳውያን በኾኑት ላይ በርሷ ይፈርዳሉ። ሊቃውንቱና ዐዋቂዎቹም ከአላህ መጽሐፍ እንዲጠብቁ በተደረጉትና በርሱም ላይ መስካሪዎች በኾኑት (ይፈርዳሉ)።” (አል-ማኢዳህ 5፤ 44)
وَمَا قَدَرُوا اللَّهَ حَقَّ قَدْرِهِ إِذْ قَالُوا مَا أَنْزَلَ اللَّهُ عَلَى بَشَرٍ مِنْ شَيْءٍ قُلْ مَنْ أَنْزَلَ الْكِتَابَ الَّذِي جَاءَ بِهِ مُوسَى نُوراً وَهُدىً لِلنَّاسِ تَجْعَلُونَهُ قَرَاطِيسَ تُبْدُونَهَا وَتُخْفُونَ كَثِيراً [٦:٩١]
“ ‘አላህ በሰው ላይ ምንም አላወረደም’ ባሉም ጊዜ አላህን ተገቢ ክብሩን አላከበሩትም። (እንዲህ) በላቸው፡- ‘ያንን ብርሃንና ለሰዎች መሪ ኾኖ ሙሳ ያመጣውን መጽሐፍ ክፍልፍሎች የምታደርጉት ስትኾኑ ማን አወረደው?’ ” (አል-አንዓም 6፤91)
2. በነቢዩ ዒሣ (ዐ.ሠ) ላይ የወረደው ኢንጂል /ወንጌል/
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ
وَقَفَّيْنَا عَلَىٰ آثَارِهِم بِعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ التَّوْرَاةِ وَآتَيْنَاهُ الْإِنجِيلَ فِيهِ هُدًى وَنُورٌ وَمُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ التَّوْرَاةِ وَهُدًى وَمَوْعِظَةً لِّلْمُتَّقِينَ [٥:٤٦]
“በፈለጎቻቸውም (በነቢያቶቹ ፈለግ) ላይ የመርየምን ልጅ ዒሳን ከተውራት በስተፊቱ ያለውን አረጋጋጭ ሲኾን አስከተልን። ኢንጂልንም በውስጡ ቀጥታና ብርሃን ያለበት በስተፊቱ ያለችውን ተውራትንም የሚያረጋግጥ ለጥንቁቆችም መሪና ገሳጭ ሲኾን ሰጠነው።” (አል-ማኢዳህ 5፤ 46)
3. በነቢዩ ዳውድ (ዐ.ሠ) ላይ የወረደው ዘቡር
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ
وَآتَيْنَا دَاوُدَ زَبُوراً [١٧:٥٥]
“ዳውድንም ዘቡርን ሰጥተነዋል።” (አል-ኢስራእ 17፤ 55)
4. በነቢዩ ኢብራሂም እና በነቢዩ ሙሣ (ዓ.ሠ) ላይ የወረዱት ፅሁፎች /ሱሁፍ/
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ
أَمْ لَمْ يُنَبَّأْ بِمَا فِي صُحُفِ مُوسَىٰ ﴿٣٦﴾ وَإِبْرَاهِيمَ الَّذِي وَفَّىٰ ﴿٣٧﴾ أَلَّا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ ﴿٣٨﴾ وَأَن لَّيْسَ لِلْإِنسَانِ إِلَّا مَا سَعَىٰ ﴿٣٩﴾ وَأَنَّ سَعْيَهُ سَوْفَ يُرَىٰ ﴿٤٠﴾ ثُمَّ يُجْزَاهُ الْجَزَاءَ الْأَوْفَىٰ ﴿٤١﴾ وَأَنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ الْمُنتَهَىٰ ﴿٤٢﴾
“ይልቁንም በዚያ በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ ባለው ነገር አልተነገረምን? በዚያም (የታዘዘውን) በፈጸመው በኢብራሂም (ጽሑፎች ውስጥ ባለው አልተነገረምን?) (እርሱም ኃጢያት) ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢኣት አትሸከምም። ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም። ሥራውም ሁሉ ወደ ፊት ይታያል። ከዚያም ሙሉውን ምንዳ ይመነዳዋል። መጨረሻውም ወደ ጌታህ ብቻ ነው።” (አን-ነጅም 53፤36-42)
قَدْ أَفْلَحَ مَن تَزَكَّىٰ ﴿١٤﴾ وَذَكَرَ اسْمَ رَبِّهِ فَصَلَّىٰ ﴿١٥﴾ بَلْ تُؤْثِرُونَ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا ﴿١٦﴾ وَالْآخِرَةُ خَيْرٌ وَأَبْقَىٰ ﴿١٧﴾ إِنَّ هَٰذَا لَفِي الصُّحُفِ الْأُولَىٰ ﴿١٨﴾ صُحُفِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ ﴿١٩﴾
“የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ። የጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ። ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ትመርጣላችሁ። መጨረሻይቱ (ሕይወት) በላጭ ሁል ጊዜ ዘውታሪም ስትኾን። ይህ በፊተኞቹ መጻሕፍት ውስጥ ያልለ ነው። በኢብራሂምና በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ።” (አል-አዕላ 87፤ 14-19)
ከአቢ ዘር (ረ.ዐ) እንደተዘገበው ለአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)፡-
“በኢብራሂም ላይ የወረዱ ፅሁፎች ምን ይመስሉ ነበር? በማለት ጠየቅኳቸው። እርሣቸውም ‘ሁሉም ምሣሌዎች ናቸው።’ በማለት መለሱ።
በቀጣዩ ክፍል የምናየው ይሆናል ኢንሻአላህ
✍ሀዩነኝ የኡስታዜ አቡሀይደር ተማሪ
https://t.me/KatetagiwuMangad