የቀድሞዋ የኢንግላንድ ንግስት የነበሩት ፡ ንግስት ኤልዛቤት በየጊዜው የተለያዩ እንግዶችን ጋብዘው በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ያናግራሉ ።
...
እና በባኪንግሐም ህግ መሰረት ማንኛውም ሰው ልክ እግሩ ቤተመንግስቱ ሲገባ ጀምሮ የሚመራው በእልፍኝ አሳላፊዎች ነው ።
አሳላፊዎቹ እየመሩት ይገባል ፡ የሚቆምበትንና የሚቀመጥበትን ቦታ ሁሉ የሚያሳዩት እነዚህ የቤተመንግስት ሰወች ናቸው ። የአሳላፊዎቹን ትእዛዝ መስማት ጨዋነትም ጭምር ነው ።
....
እነዚህ የቤተመንግስት አሳላፊዎች ከንግስቲቱ ጋር የሚግባቡበት ቋንቋ አላቸው ።
ንግስት ኤልዛቤት ካለፉ በኋላ ይፋ ከተደረጉት ከነዚህ መግባቢያ ምልክቶች መሀል አንደኛው የንግስቲቱ ቦርሳ ነው ።
....
እናም ንግስቲቱ ከእንግዳው ጋር እየተነጋገሩ እያለ ፡ አይናቸው ከእንግዳው ሳይነቀል በክንዳቸው ላይ የያዙትን ቦርሳ ወደ ሌላ ክንዳቸው ካዞሩት .....
" ከእንግዳው ጋር ማውራት የሚገባንን በሙሉ አውርተናል አሰናብቱት " የሚል መልእክት ስለሚኖረው ይህንን በትኩረት የሚከታተሉት አሳላፊዎች ፡ የውይይቱ ሰአት ማብቃቱን ለእንግዳው በዝግታ ይነግሩታል እንግዳው ንግስቲቱን ተሰናብቶ ይወጣል ።
.....
በቤተመንግስቱ ለእራት የተጋበዙ እንግዶች ካሉ ደግሞ ረጅሙ ገበታ ይቀርብና ተበልቶ ተጠጥቶ ሲያበቃ ንግስቲቱ ቦርሳቸውን በዝግታ ጠረጴዛው ያስቀምጣሉ ።
ትርጉሙ ገበታውን አንሱት የራት ፕሮግራሙ ተጠናቋል ማለት ነው ።
....
ንግስቲቱ የሆነ ቦታ ሄደው ጉብኝታቸውን መጨረሳቸውን ለማሳወቅ ሲፈልጉም በተመሳሳይ ቦርሳቸውን ብድግ አድርገው ያስቀምጣሉ ።
በዚህ ሰአት ረዳቶቻቸው መሄድ እንዳለባቸው ይነግሯቸውና ስፍራውን ለቀው ይወጣሉ ።
ልክ እንደዚሁ ፡ ንግስቲቱ ጣታቸው ላይ ያለውን ቀለበት ፡ በአንድ እጃቸው እየነካኩ ፡ በዝግታ ማሽከርከር ከጀመሩ ወይም ጓንታቸውን ካወለቁ ፡ እነሱ ብቻ በሚያውቁት መግባቢያ ፡ የሆነ መልእክት እያስተላለፉ ስለሆነ ረዳቶቻቸው በፍጥነት መጥተው ትእዛዙን ይፈፅማሉ ።
.....
በዚያ ምንም ነገር ያለጥናት አይደረግም ፡ እያንዳንዷ እንቅስቃሴ ትርጉም አላት ....
ይህ ሁሉ ሲሆን ግን. . ተመልካች ወይም እንግዳው የሚረዳው ፡ ትእዛዞቹ ሁሉ የሚመጡት ከአሳላፊዎቹ እንደሆነ ነው ።
በዚህ አይነት መልኩ የእንግዳውን ክብር ሳይነካ ፡ በሚስጥራዊ መግባቢያ እንግዶቻቸውን ተቀብለው በስርአትና በክብር ይሸኛሉ ።
@Amazing_Fact_433