ብዙዎች የሚያውቋትና የሚወዷት ፡ ይህ ቀረሽ በማይባል ቁንጅናዋ ብቻ ነው ።
ማርሊን ሞንሮ ፡ የአሜሪካንን ፕሬዝደንት ሳይቀር በውበቷ ያማለለች ፡ ሺህዎች ከምር በፍቅር የወደቁላት. .. ሚሊዮኖች ደግሞ እስከዛሬ ድረስ ውድድ የሚያደርጓት የምትገርም ድምጻዊትና አክትረስ ነበረች ።
....
አስገራሚው ነገር ፡ አብዛኛው የማርሊን ሞንሮ ወዳጆች የሚያውቁት የላይ ውበቷን እንጂ ከዚህ የተዋበ ሰውነት ውስጥ ያለውን የሚገርም ብስለትና ምሁርነት አያውቁም ።
.......
ነገር ግን ማርሊን ፡ በመኖሪያ ቤቷ በሚገኘው ከ400 በላይ የተመረጡ መፅሀፍትን የያዘ ላይብረሪ ውስጥ እያዘወተረች .. የነ ዶስቶቭስኪን ፡ የአልበርት አነስታይን ፡ ሲግመንድ ፍሮይድ ፡ ሊዮ ቶልስቶይ መፅሀፎችን ስታነብ የምትውል ( Avid Reader ) የምትባል አንባቢ ሴት ነች ።
ማንም ከሚያስባት በላይ ምሁርና በሳልነቷ ፡ በቁንጅናዋ ተሸፍኗል ።
ማርሊን ሞንሮ ፡ ውብ እና ምሁር ሴት ብቻም አይደለችም ። ለሰው እድገት የቻለችውን ሁሉ የምታደርግ ደግ ሴትም ነበረች ።
....
ማርሊን ከነበሯት ጥቂት የሴት ጓደኞች መሀከል አንዷ ፡ የሶል ንግስት ትባል የነበረው ኤላ ፊትዠራልድ አንዷ ናት ፡ እና ኤላ ታዋቂነቷ ጎልቶ ከመውጣቱ በፊት በተለይ በ1950 ዎቹ በነበረው የዘር መድልኦ ምክንያት ፡ በትላልቅ ክለቦች መዝፈን አስቸጋሪ ሆኖባት ነበር ።
....
በዚህ ወቅት ፡ ማርሊን ጥቁሯ ጓደኛዋ ኤላ ፊትዠራልድ በሆሊውድ በሚገኘው ሞካምቦ ክለብ እንዳትዘፍን መከልከሏን ሰማች ። እና በጊዜው ትልቅ ወደነበረው ወደዚህ ክለብ ባለቤት ስልክ ደወለች ።
እንደምናለህ ጌታው ፡ ማርሊን ሞንሮ ነኝ
ሰውየው ደነገጠ
እኔምልህ ሚስተር .. ጓደኛዬ ኤላ ፊትዠራልድ በአንተ ክለብ ውስጥ መዝፈን እንድትችል እንድትፈቅድላት ነበር የደወልኩልህ ።
...
የናይት ክለቡ ባለቤት ምንም እንኳን ማርሊን ሞንሮን ቢያደንቃትም ፡ በጊዜው ባለው ሁኔታ ምክንያት ለኤላ ፊትዠራልድ መድረክ ለመስጠት እንደሚቸገር አለሳልሶ ነገራት ።
...
ማርሊን ሞንሮ ይህንን ምላሽ ከሰማች በኋላ ፡ በአንድ ነገር እንስማማ አለችው
" በምን "
ኤላ ፊትዠራልድ በአንተ ክለብ ውስጥ እንድትዘፍን ከፈቀድክላት. .. እሷ በዘፈነች ቁጥር አንተ ክለብ እየመጣሁ እዝናናለሁ ፡ ምን ይመስልሀል አለችው
ሰውየው የሰማውን ማመን አቃተው
ማርሊን ሞንሮን የሚያህል ትንሽ ትልቁ የሚወዳት እጅግ ዝነኛ ሴት እሱ ክለብ አዘውትራ መጣች ማለት ፡ ለእሱም ሆነ ለክለቡ እጅግ በጣም ትልቅ ነገር ነው ።
እና ወዲያውኑ ምላሽ ሰጣት
ጓደኛሽ ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ዝግጅቷን ማቅረብ ትችላለች ሲል ፡ በጥቁርነቷ ምክንያት መድረክ ለተከለከለችው ድምጻዊት ፈቀደላት ።
....
በቆንጅዬዋ ፡ ማርሊን ሞንሮ ጥረት በታላቁ ሞካምቦ ናይት ክለብ መዝፈን የጀመረችው ኤላ ፊትዠራልድ ዝናዋ መግነን እና ታዋቂ መሆን ጀመረ ።
@Amazing_Fact_433